"የኢትዮጵያ ህግ ጥምር ዜግነትን ስለማይፈቅድ፣ በአውሮፓ የሚጫወት አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማግኘት ሲል የተወለደበትን ወይም ያደገበትን ሀገር ዜግነት እንዲተው ይጠየቃል። ይህ ደግሞ ለተጫዋቾቹ በፍጹም የሚታሰብ አይደለም።
ምክንያቱም የውጭ ሀገር ፓስፖርታቸውን ከተዉ በአውሮፓ ሊጎች እንደ ውጭ ሀገር ተጫዋች ስለሚቆጠሩ በስራቸው እና በሙያቸው ላይ ትልቅ እንቅፋት ይፈጥርባቸዋል።
ለዚህ መፍትሔው ሌሎች ሀገራት የተጠቀሙበትን አሰራር መከተል ነው።
ለምሳሌ እንደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ህንድ ያሉ ሀገራት ጥምር ዜግነት ባይፈቅዱም፣ ለስፖርተኞቻቸው ልዩ አሰራር ዘርግተዋል። ይኸውም ለተጫዋቾቹ የService Passport ወይም የስፖርት ፓስፖርት መስጠት ነው። ይህ ማለት ተጫዋቹ የያዘውን የውጭ ሀገር ዜግነት ሳይተው፣ በውድድር ወቅት ሀገሩን ወክሎ እንዲጫወት የሚያስችል ልዩ የጉዞ ሰነድ መስጠት ማለት ነው።
ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢሚግሬሽን እና ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር ተቀናጅቶ መስራት አለበት። ፌዴሬሽኑ አሳማኝ አሰራር እና መመሪያ አዘጋጅቶ ለመንግስት በማቅረብ ልዩ ፈቃድ ማውጣት ይችላል። በተጨማሪም በአውሮፓ የሚጫወቱ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን መረጃ አደራጅቶ የሚይዝ የመረጃ ቋት (Database) እና የቅርብ ስካውቲንግ አሰራር ያስፈልገናል። ከእነሱ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቀድሞ በመነጋገር ለሀገራቸው እንዲጫወቱ ማድረግ ይቻላል።"
( ጋዜጠኛ ኤርሚያስ በላይነህ 7ኛ ፖድካስት ላይ ከተናገረው )
SHARE | @FN_SPORTS