" ሀገረሠላምን ማሸነፍ ቀላል ነው አስለቅሰዋለሁ።"- ለተከታታይ ሁለት ጊዜ የEFTC MMA Fight አሸናፊው ጆኒ
የኢትዮጵያ የፍልሚያ ዘርፍ መነቃቃት ለእረፍት አልባ የፍልሚያ ፍላጎቶች ሲጋብዝ፤ በፍልሚያው ገንዘብና ዝናን የሚቀናጁት አትሌቶች አንዳቸው ሌላቸው እየወረፉ በመጋበዝ ተጠምደዋል።
በዚህም የአድዋ ፍልሚያ ምሽት 01 እና 02 አሸናፊው የብራዚል የትግል ስፖርት ከፍተኛ ባለሞያና አሰልጣኙ ዮሐንስ ስለሺ (ጆኒ) በኢትዮ ፍልሚያ ምሽት በተጋጣሚው ለተረታው ማስተር ሃገረሰላም(ቦንጆ) ንቀት አዘል ጥሪ (callout) አቅርቧል።
ጆኒ በዚህ ጥሪው ቦንጆን ያሸነፈው ቢኒያም ሽብሬ "ከእሱ ከመፋለም ሃገር ጥሎ በመጥፋቱ" እንደ ሁለተኛ አማራጭ የተቀመጠውን "ዝቅ ብለን" ለመጥራት ተገደናል በማለት ንግግር ጀምሯል።
በዚህም ቢኒያም ጥሩ አቅም እንዳለው ቦንጆ ማምኑ ልክ አለመሆኑን በመጥቀስ "አንተን ማሸነፍ ቀላል ነው፤ በመፋለሚያ አጥሩ ውስጥ አስለቅሰሃለው፤ ለቅሶው የደስታም የሀዘንም ሊሆን ይችላል እሱ ያንተ ምርጫ ነው፤ ግን ታለቅሳለህ" ሲል ማስፈራሪያ አዘል መልእክት አስተላልፏል።
ጆኒ "ይፋዊ የፍልሚያ ጥሪ ነው" ባለው በዚህ መልእክቱ ማስተሩ ሃገረሰላም ውል እንዲፈርም ጥያቄ አቅርቦ በኢትዮ ፍልሚያ ምሽት በቢኒያም ላይ የረባ ዱላ ማሳረፍ አልቻልክም ሲልም ጥረቱን አሳንሷል።
ጆኒ "ቢኒያም ከሀገር ወጥቷል" ቢልም ቢኒያም በሰጠው ምላሽ በአዲስአበባ እንደሚገኝ ትናንት አስታውቋል። ሃገረሰላም ከቢኒያም ጋር በነበረው ፍልሚያ ያሳየው ብቃትና የስፖርት ስነምግባር በብዙሃን መወደዱ ይታወሳል።
SHARE | @FN_SPORTS