አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሱዳን ጦር የፈጸመው የአየር ጥቃት ግልፅ የጦር ወንጀል ነው አለ
የሱዳን ጦር ኃይል ይህን ጥቃት ያደረሰው በሰሜን ዳርፉር ግዛት ካብካብያ በተባለችውና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ቅጥጥር ሥር በሆነች ከተማ ላይ መሆኑንም የድርጅቱ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪቃ ሃገራት ዳይሬክተር ታይገር ቻጊታ አስታውቀዋል።
ቻጊታ አክለውም፤ ሲቪሎች የተሰባሰቡበትን የገበያ ስፍራን በቦምብ ማጋየት ያለውን የጦር ወንጀል ማሳያ እንደሆነም አመልክተዋል። በአካባቢው በርካታ ወታደሮች መኖራቸውም ድርጊቱን ለመፈጸም እንደ ማስረጃ ሊቀርብ አይችልምም ነው ያሉት።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወታደራዊ አውሮፕላኖች በካብካቢያ ሳምንታዊ የገበያ ቀን ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት በርካታ ሲቪሎች በተሰበሰቡበት ሰዓት ቦምብ ባዘነቡት ቦምብ በርካቶች መገደላቸውን ከከተማዋ የዐይን ምስክሮች መረጃዎች እንደደረቱትም አስታውቋል። ከሟቾቹ 15ቱ ጥቃት ሸሽተው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉና ወደ ካብካብያ የተሰደዱ ሲቪሎች መሆናቸውንም ገልጿል።