ፖሊስ የባለሀብቱን ገዳይ እና አስገዳይን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገለጸ
ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው አትሌቶች መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሆኑትን፤ አቶ ቢረሳው ምናለ ፈንታ በመግደል እና በማስገደል ወንጀል የተጠረጠሩትን ሦስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ ታሕሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ከሥራ መልስ ወደ ቤታቸው በማምራት በራቸው ላይ ቆመው የመኪና ጥሩምባ እያሰሙ በር እስኪከፈትላቸው እየጠበቁ በነበረበት ወቅት ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ሦስት ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን ገልጿል፡፡