ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት ጀምራለች ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት መጀመሯን የአውስትራሊያው የስትራቴጂክ ፖሊሲ ጥናቶች ኢንስቲትዩት ባወጣው ሪፖርት ጠቆመ።
ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት ቻይና ከ44 ቁልፍ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ውስጥ በ37ቱ ከምዕራባዊያኑ ቀዳሚ ደረጃን መያዟን አረጋግጧል።
ሰው ሠራሽ አስተውሎ፣ የኤሌክትሪክ ባትሪ፣ ሰው አልባ አውሮፕላን፣ የኑክሌር ኃይል፣ የሮቦት ሳይንስ እና የሕዋ ምርምር ቻይና ከፍተኛ ዕድገት ያሳየችባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ናቸው ተብሏል።
በሳይንሳዊ ምርምር ስመ-ጥር የሆኑ 10 ተቋማት ሁሉም ቻይና ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።
አሜሪካ እና አውሮፓ በወሳኝ የቴክኖሎጂ ዘርፎች በቻይና እየተቀደሙ መሆናቸውን ይኸው የአውስትራሊያ የፖሊሲ ምርምር ተቋም አሳውቋል።
ቻይና አሁን ላይ በሚታወቁ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሚፈጠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችም የበላይነት ለመያዝ ሩቅ አሳቢ ዕቅድ እንዳላትም ተገልጿል።
የቻይና ግስጋሴም ሀገሪቱን በቅርቡ የቴክኖሎጂ ልዕለ-ኃያል ሊያደርጋት እንደሚችልም ተጠቁሟል።
አልጀዚራ እንደዘገበው አሜሪካ እና ቻይና በበረታ የቴክኖሎጂ ፉክክር ውስጥ ገብተዋለ። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow