°•°ቢስሚከ ነህያ °•°


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


🦋አዋቂ ወይም ተማሪ አለያ አድማጭ ሁን
አራተኛን ግን አትሁን ትጠፋለህና

(ነብዩ ሙሐመድ ሰዐወ)
አጭርና አስተማሪ ፅሁፎችን
@HAYAttuna
ለሀሳብ @Maabde

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




ጥሩ ጥቆማ ለዱንያም ለአኺራም
دعاء يوم الجمعة المستجاب
ጁሙዓ ቀን  ዱዓ ተቀባይነት ሚያገኝባት አንዲት ወቅት አለች
  ይበልጥ ምትጠረጠረው ደሞ ከአስር እስከመግሪብ ባለው ወቅት ነው።
ታድያ ምን ትጠብቃለህ እጅህን ወደ ላይ ለማንሳት

አሁን ⌚ ሰዓቱ ያስጨነቀህን እንዲሳካልህ ምትፈልገውን ነገር ለአላህ ምትነግርበት ግዜ ነው

      @HAYAttuna
      @HAYAttuna

JOIN


በኔ ላይ አንድ ሶለዋት ያወረደ አላህ በሱ ላይ 10 ሶለዋት ያወርድበታል
 (مَنْ صَلَّى عَلَيَّ وَاحِدَةً، صَلَّى الله عَلَيْهِ عَشْرًا))


ያአላህ አስባቹታል እኛ በውዱ ነብያችን ላይ 1 ሶለዋት ስላወረድን ብቻ አላህ በኛ ላይ አስር ሶለዋት ሲያወርድብን
ምን አይነት እርካታ ይሰማን ይሆን ምን አይነት ደስታስ ይሰማን ይሆን ማንስ እኛን ሊጎዳን ይችል ይሆን ጌታችን አላህ በኛ  ሚስኪን ባርያዎቹ ላይ ሶለዋት እያወረደብን ሳለ

እኛ 10 ሶለዋት ብናወርድ በሀቢባችን ላይ አላሁ ተአላ በኛ ላይ 100 ያወርድብናል
100 ብናወርድ 1000 ያወርድብናል ሱብሀነላህ

ሓያ እንግዲ ያጀመዓ ወደ ሶለዋት ዛሬ ጁሙዓም አይደል ምላሳችንን በሶለዋት ስትራፖ እናሲዛት

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى محمد وَعَلَى آلِ محمد كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ علَى محمد وَعَلَى آلِ محمد كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

         @HAYAttuna
         @HAYAttuna

JOIN


ያሸባብ ይህ ወጣትነታችንን ጎልማሳነት ሳይመጣ በፊት እንጠቅምበት
ምክንያቱም ነገ አላሁ ተዓላ ፊት ወጣትነትህን በምን አሳለፍከው የሚል ትልቅ ጥያቄ አለብን እንንቃ እንጂ ያሸባብ ለነገ ጥያቄው መልስ ሚሆነንን ስራ ሰራ ሰራ እናርግ እንጂ ሶላት ጀመዓ መስገዱ :ቂያመ ለይሉ :ነዋፊል ፆሞች :ሶለዋት ዚክሩ: እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም
ካልሆነ ይህን ወጣትነታችንን በሞት እናጣዋለን አልያም ደሞ የወጣትነታችን ግዜ አልፎ የምንቆጭ ነው ምንሆነው ያኔ የእግር ሰዓት ቢሆንብን ወደ ወጣተነታችን አንመለስም

=ወጣትነትህን ነፍሲያና ሸይጧን ይፈልጉታል
=ወጣትነትህን አላህም ደሞ ይፈልገዋል ደሞም አንድ ቀን ይጠይቅሀል
  
ለማን እየሰጠህ እነደሆነ ራስህን መርምር

ወጣትነታቸውን አላህ በሚፈለገው መልኩ ከሚያሳልፉትና ለነገ ጥያቅያቸውም ጥሩ የሆነን መልስ ይዘው እሱን ከሚገናኙት ምርጥ ባሮቹ አላህ ያድርገን

            @HAYAttuna
            @HAYAttuna

join


"በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መባልና መደረግ ያለባቸው ነገሮች!"

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም

             ሰኞ 6/7/1446 ዓ.ሂ

       


የወተቱ ነገር ……

መቼም ስለዛ ወተት ታሪክ ሳትሰማ የቀረህ አይስለኝም። ስለዛ እሳት ላይ ተጥዶ ፣ጠባቂ አጥቶ፣ ገንፍሎ ፣ራሱን አቆሽሾ በዙሪያው ያለውን እንዳቆሸሸውና ወደ ነበረበት የወተትነት ማእረጉ ለመመለስ አዳጋች ወደነበረው የወተት ታሪክ ዳግም ላስታውስህ ወደድኩ ።

  አንድ ሰው ወተት  መጠጣት አሰኘውና ከሱቅ ገዝቶ መጥቶ እሳት አንድዶ ይጥደውና ወደ ሌላ የቤት ወስጥ ስራ ያመራል። በዛም ይጠመድና ወተቱን ይዘነጋዋል
ድንገት ትዝ ይለውና ወደ ጣደው ወተት ሲያመራ ወተቱ ገንፍሎና ዙሪየው ያለውን ሁሉ አበላሽቶ ይጠብቀዋል ። በዚህም ነገር   የተበሳጨው ይህ ሰው በቁጭትና በንዴት ውስጥ ሆኖ አንገቱን አቀርቅሮ በትካዜ ተዋጠ ።
አይገርምም? ?

አው አይገርምም

ምክንያቱም ምንም የሚገርም ነገር የለውማ
ወተቱን ገዝቶ ያመጣውኮ እስኪፈላ ጠብቆ ሊጠጣው ነበር ።
ነገር ግን ቸል በማለቱ የዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገባ።

የማወራህ  ስለ ወተቱ አይደለም ወዳጄ

ነገር ግን ይህን ምሳሌ አርጌ ላስጨብጥህ የምፈልገው  አንድ ቁም ነገር ስላለ ነው ።
እሱም ምን መሰለህ
የአንድ ትውልድ መሰረቱ ህዝብ ነው  የህዝብ ምሰሶው ደግሞ ቤተሰብ ነው ። 
አንድ ቤት ሲገነባ መሰረቱ ጥልቅና ጠንካራ ከሆነ የሚገነባው ቤትም የዛን ያክል ዘላቂና ጠንካራ ይሆናል ።
መሰረቱ ያልተስተካከለ ቤት  ዘላቂነት ስለማይኖረው  ወድቆ ጉዳት ማድረሱ አይቀሬ ነው ።
ልክ እንደዚው ቤተሰብም የአንድ ትውልድ መሰረት ነው ።
ልጅ ቤተሰብን ሆና ያድጋል አናትን አባትን እህትን ወንድምን በዙሪያው ያለውን ከባቢ አየቃኘ ያድጋል። ኃላም ያየውን የቃኘውን ይኖራል  ትውልድም የሆናል።
አሁን ወደመሰረቱ ለመልስህ

ለዚህ ትውልድ መበላሸትም ይሁን መስተካከል ዋናውን ድርሻ የሚወስደው ወላጅ ነው።
አንድ ወላጅ ልጅን ሲወልድ ከመውለድ ባለፈ ትልቅ ሀላፊነት ይጠብቀዋል ። ሊጠብቀው ሊንከባከበው ይገባል። ልጁ በዲኑ ጠንካራ እንዲሆን ሰላት አሰጋገድን እየሰገደ ሊያሳየው ይገባል ። ፆምን ፣ሰደቃን፣ በጎ ተግባራትን ሁሉ ከትእዛዝ ባለፈ እየተገበረ ሊያሳየው ግድ ነው።
በዋናነት አላህ ሱብሀነሁ  ወተአላ መፍራት ሊያስተምረው ይገባል። የአላህ ቃል እንዲወድ ቀርቶ በማስቀራት ከተከለከሉ ክልከላዎች ነፍሲያን በማቀብ የአላህን ምንዳ መከጀልን ማሰተማር ይገባዋል ።
ሴት ልጅ የወለዱ እንደሆነ ደሞ እሷን ጠብቆና ተንከባክቦ ለትልቅ ደረጃ ማብቃት ሌላ ራሱን የቻለ ትልቅ ምንዳ አለው ። ሀያእ (አይናፋርነት፣ጥብቅነት)ን እንድትላበስ በማድረግ ሰላት መስገድን፣ ቁርአን መቅራትን፣
ሂጃብ በስርአት ማድረግን ከመናገርና ከማዘዝ ባለፈ እናት ተግብራ ለልጇ ልታሰያት ግድ ነው ።
ያ ሲሆን ትውልድ መሰረቱ ጠንካራ ይሆንና ጥሩ ከባቢ ይፈጠራል።
ያ ካልሆነ ግን ቀደም ሲል ያነሳሁልክ የባለ ወተቱ ሰውዬ ታሪክ ይሆንና በወላጅ የተጀመረው  ስህተት ለትውልድ  ኪሳራ ይሆናል።
መሞትን ፣ወደ ቀብር መግባትን፣ (በርዘኽ) ወደ ሚባለው አለም መሄድን፣ እዛም ወስጥ ከነኪር እና ሙንከር ጋር መፋጠጥን ፣ከዛም ፍጡራን ሁሉ ወደ አላህ ፊት ቀርቦ ሂሳብ መደረግን ፣ ዱንያ ላይ እንደነበረው ቆይታ ሂሳብ ተደርጎ ዘውታሪ የሆነ አለም መኖርን ።ይሄ ሁሉ ለነገር የሰው ልጅ  እንደሚጠብቀው   ያላስተማረ ወላጅ በርግጥም ልጁን ችላ እንዳለው ይታሰባል ።
ወላጅ ልጁን ከመመገብ ከማልበስ አካዳሚክ እውቀትን ብቻ ከማስተማር ባለፈ ይህን የህይወት ስንቅ ሊያስተምረው ይገባል።
ያ ሲሆን ቤተሰብ ትልቁን ሚና ተጣ ይባላል ።
ትውልድም ከኪሳራ ይድናል ።
ሴት ልጅ ሂጃብ ግዴታዋ ነው መሰተሪያዋ መጠበቂያዋ ነው ። ጠንቅቃ የተገበረቸው እንደሆነ በዚህም በዚያኛውም አለም ትርፋማ ያድርጋታል ።
ከሁሉም የሚበልጠው ደግሞ አላህን መፍራቷ ነው።
ወንድ ልጅም እንደዛው ነው ።ዝንባሌውን መከተል ሲያቆም ፣ አላህን በልቡ ማላቅን ሲያዘወትር ምድር ላይ የሚኖረው ቆይታ ያማረ ይሆናል ።

ሁላችንም ራሳችንን እንፈትሽ ፣ዙሪያችንን እንቃኝ።
ከምን ጎዜውም በላይ ወደ አላህ እንመለስ ዱኣ እናድርግ ።

አላህ ከተፀፃቾች ያድርገን
አሚን

@HAYAttuna

JOIN


«اللَّهمَّ  صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،

     


በወርሃ ረጀብ የመጀመሪያው መሥራት ያለብህ ነገር፤ ወንጀል መፈፀምን ማቆም ነው‼

የረጀብ ወር ወንጀል በወርሃ ረመዿን ኑርህን ያጠፋዋል። የኢማን ጥፍጥናህን ይቀንሰዋል። ገና ከወዲሁ ነፍስያህን ከወንጀል በማቀብ ለረመዿን አዘጋጃት። ሶላት ኢቃም ከተባለ በኋላ እየተሰገደ እየሮጠ ሂዶ የሚደርስ ሰውና ቀድሞ ሂዶ ቀብሊያ ሱንናዎችን ሰግዶ፣ በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባለውን ዱዓእ አድርጎ፣ ኢቃም ሲባል ረጋ ብሎ ተነስቶ የሚሰግዱ ሰዎች እኩል የመረጋጋት መንፈስ እንደናይኖራቸው ሁሉ፤ ገና ከረጀብ ጀምሮ ነፍሱን ከወንጀል አቅቧት፣ ኸይር ሥራ እያለማመዳት ለረመዿን ያዘጋጀና ልክ «ረመዿን ነገ ነው!» የተባለ ምሽት ጀምሮ የሚዘጋጅ ሰው እኩል ውጤታማነት ላይኖራቸው ይችላል። ነፍሱን ቀድሞ ስላላለማመዳት አንዳንድ ጊዜ ተንሸራቶ በረመዿንም ወንጀል ሊፈፅም ይችላል። አላህ ይጠብቀንና!

ዛሬ ረጀብ 01, 1446 H.C. ነው። ረመዿን ድፍን 2 ወራት ይቀሩታል።

በረጀብ ወር የሚፈፀም የተለዬ ሶላት፣ ጾም ወይም ልዩ ዒባዳህ የለም። ረጀብ ነፍስ ይበልጥ ከማይበደልባቸው አላህ እርም ካደረጋቸው 4 የአመቱ የተከበሩ ወራት መካከል አንዱ ስለሆነ፤ በዚህ ወር በፍፁም ወንጀል ላይ ልትወድቅ አይገባም
ሸይጧን ሲወሰውስህ፤ አዑዙ ቢላህ ብለህ ራስህን ካለህበት ቦታ ተንቀሳቅሰህ ቀይር።  አላህ ያግዘን‼


‏( وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ )


«اللَّهمَّ  صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،

     


«اللَّهمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،

     


በአላህ ካዝና ውስጥ ብዙ ኸይሮች፣ ብዙ በረከቶች ፣ ብዙ ሰርፕራይዞች አሉ።
ቀጣዩ ሰርፕራይዝህ/ሽ

ዑምራ ሊሆን ይችላል፣
ኒካሕ ሊሆን ይችላል፣
እርግዝና ሊሆን ይችላል ፣
ልጅ ሊሆን ይችላል ፣
ሀብት ሊሆን ይችላል ፣
ሐጅ ሊሆን ይችላል ፣
መኪና/ ቤት ሊሆን ይችላል ፣
ዓፊያ ሊሆን ይችላል ፣
ምርቃት ሊሆን ይችላል ፣
ተውባ ሊሆን ይችላል ...

ማን ያውቃል ። እስቲ ተመኙ። በአላህ ላይ መልካም አስቡ። ዱዓ አድርጉ፣ ኢስቲግፋር አብዙ። ተማምናችሁ ጠብቁ።
አላህ ብዙ አለው።
، استغفرو 💛🌼.

@HAYAttuna

JOIN


«اللَّهمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،

      @HAYAttuna

JOIN


ከሐጃዬ ሓጃችሁ ይቅደም። ክፉ አያግኛችሁ።


አንድ ሰው  በኢስላማዊ ሚዲያ ስለታየ፣ የእስልምና ተቆርቋሪ አክቲቪስት ስለሆነ፣ ወይም ሒጃብ ስለለበሰች ብቻ  ሞዴል ተደርጎ አይያዝም። ሲጀመር ዲን ከኪታቡ እንጂ ከሰው አይወሰድም፣ እገሌ ይህን አድርጓል ተብሎም ከዲኑ አስተምህሮ ዉጭ የሆነ ነገር አይደረግም። ሐላል አላህ ያደረገው ነው፣ ሐራምም እንዲሁ ። እንጂ ሰዉማ ለነፍሱ አምሮት ሲል ስንቱን ሐራም ሐላል አድርጓል መሠላችሁ!!።
አሁን ላይ በተለይ ነሺዳና ሙዚቃ ከቁርአንና ሐዲሥ በላይ መደመጣቸው እጅጉን አሳሳቢ ሆኗል።

ሰዉን መከተል ካለባችሁ በሚዲያ የምታዩትንና የምትሰሙትን ሰው ሳይሆን አላህን ፈሪዎቹን፣ የተግባር መምህራንን እና የሥነምግባር አስተማሪዎቹን ተከተሉ።

@HAYAttuna

JOIN


«اللَّهمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،

      @HAYAttuna

JOIN


የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«በጁምዓ ሌሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ፣ በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድለታል።»

ኢማሙ አልባኒ ሐዲሡን ፦ " ሐሰን " ብለውታል።

اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلَّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ

      @HAYAttuna

JOIN

         🌸መልካም ጁምዓ🌸


‏اللهم يسر أمورنا وفرج همومنا واستر عيوبنا وأصلح أحوالنا واغفر لنا ولوالدينا وتوفنا وأنت راض عنا يا أرحم الراحمين


ሐምሌን ተስፋ አድርገህ ነበር፤
ነሐሴን ገና ከጅምሩ ተደነቃቀፍክ፤
መስከረም እንዳሰብከው አልሆነልህም፤
ጥቅምት ጭራሽ ሌላ ችግር ገጠመህ፤
ህዳር ፈተናህ በ፣
ታህሳስስ ምን ይዞ ይሆን??

ባይሆን አትማረር፣ አሁንም ተስፋህን ሰንቅ።

ወዳጄ
እየጣርክ እየለፋህ ባይሳካ አላህ ከወደደው ውጭ ምን ታመጣለህ?
እውነቴን እኮ ነው የምልህ እስቲ ምን ታመጣለህ?

በሁሉም ሁኔታህ ውስጥ አልሐምዱ ሊላህ በል።

ኢላሂ ሆይ በዲናችን አትፈትነን፤ ፈተናህም የቁጣህ አይሁን  እንጂ የዱንያ ፈተና ሁሉ ቀላል ነው።
ጌታዬ ሆይ የማንችለውን አታሸክመን፣
በማንችለውም አትፈትነን።

@HAYAttuna

JOIN


«اللَّهمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،

      @HAYAttuna

JOIN

Показано 20 последних публикаций.