የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
___
በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Medical Laboratory Science, Midwifery, Pharmacy, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Optometry እና Human Nutrition ሙያዎች ተመርቃችሁ ከሚያዚያ 2 – 4/2017 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ
http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration Number) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0115186275/0115186276 ላይ በመደወል ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
- ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከ29/08/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ክልል ተቆጣጣሪ አካላት በመሄድ የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ሁኔታዎች በሟሟላት የሙያ ፈቃድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የስም ፊደል ግድፈት ያለባችሁ ተመዛኞች ሙሉ በሙሉ የስም ትርጉም ለውጥ ከሌለው በስተቀር ከዲግሪያቸው ጋር በማመሳከር የምትስተናገዱ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Website:
moh.gov.etFacebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter:
x.com/fmohealthYouTube:
youtube.com/@FMoHealthEthiopiaTiktok:
tiktok.com/@mohethiopiaTelegram:
https://t.me/M0H_EThiopia