የሕብረት ባንክ የደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት በሥሩ ለሚገኙ ቅርንጫፎችና ሠራተኞች የዕውቅና ምስክር ወረቀት አበረከተ
በሕብረት ባንክ የደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ባለፉት ስድስት ወራት የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ቅርንጫፎችና ሠራተኞች በዲስትሪክቱ ቢሮ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የዕውቅና ምስክር ወረቀት አበርክቶላቸዋል፡፡
በዕውቅና ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ተ/ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ መልካም ውጤት ላይ ለመድረስ የሁሉም የጋራ ጥረትና ትጋት እንደሚያስፈልግ ገልፀው የተገኘው ውጤት እጅግ የሚያኮራ በመሆኑ ለዚህ ውጤት መምጣት አስተዋጽኦ ያደረጉትን የዲስትሪክትና የቅርንጫፍ ሰራተኞችን አመስግነዋል፡፡
በእውቅና መስጠት ፕሮግራሙ ላይ በተቀማጭ አሰባሰብ፣ በውጭ ምንዛሬ አፈፃፀም፣ በወለድ ነፃ አገልግሎት እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ሂሳብ ላስከፈቱ ሠራተኞች የዕውቅና የምስክር ወረቀት በወ/ሮ ጽጌርዳ ተስፋዬ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!