እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ…!
"…ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ? ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ህማም ተወለደ። ሰብአሰገል ሰገዱለት። አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት። ንጉሥም ነውና ወርቅ አመጡለት። ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነው ሞቱም ከርቤ አመጡለት። እርሱ ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኚልን።
"…ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ፤ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ፤ የተደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች፤ በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ፤ እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለእርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
"…በዓለ ጌናን ስናከብር በኀዘን በመከራ፣ በጭንቅ፣ በራብና በጥም፣ በሰቀቀን፣ በስደት፣ በወኅኒ ቤት፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ደኛ፣ በፅኑ ህመም ተይዘው፣ በየቤቱ፣ በየጎዳናው፣ በየሆስፒታሉና በፀበል ስፍራዎች ሁሉ ያሉትን፣ ከሞቀ ቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው በየጥሻው የወደቁትን በማሰብ፣ በመንከባከብ፣ በመጠየቅ፣ በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይሁን። ሀገራችን ኢትዮጵያንና ጎረቤቶቿን፣ መላውንም ዓለም ሁሉ ሰላማዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ያድርግልን። አሜን።
"…እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለአምላካችንና ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን‼
https://t.me/jonnyart24