#ሰው_እንዴት_ይሄንን_ሁሉ_መከራ_አልፎ_ሰው_ይሆናል?
***
👉15 ስደተኞች በአንዲት ትንሽ ጀልባ ላይ
👉11 ቀናትን ያለ ምግብና ውሃ በሜዲትራኒያን ባህር እምብርት
👉1 ብቻ ተራፊ ሰው - እርሱም የዚህ ታሪክ ታሪክ ባለቤት ነው!
👉12 ዓመታትን ያለ ፍላጎቱ በትጥቅ ትግል ያባከነበው መሀመድ እንዴት ብቻውን ተረፈ? ምን በልቶ ህይወቱን አቆየ? አሁንስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?
“የኢብራሂም አስክሬን የባህሩን ወለል እንደነካ በመጀመሪያ ከውሃው ንቅንቃቄ ጋር አብሮ ወዲያ ወዲህ ይዋልል ጀመር፡፡ ከዚያም ቀስ በቀስ በዝግታ በጀልባዋ ዙሪያ ክብ ሰርቶ ወደነበረበት ተመለሰ፡፡ አሁንም ፍጥነቱን እየጨመረ እንደገና ጀልባዋን ደግሞ ዞራት፡፡ ሁላችንም አስፈሪውን ትርኢት እያስተዋልን መተከዝና መደነቅ ጀመርን፡፡ ኢብራሂም ትቶን ለመሄድ የደፈረ አይመስልም፡፡ ወይንም የእኛንም መጪ እጣፈንታ በቅኔ እያሳየን መሰለን፡፡ ትርዒቱ እጅግ አስፈሪ ነበር፡፡
ልክ እንደ አስማታዊ ነገረ ስራ በጀልባዋ ዙሪያ በተሽከረከረ ቁጥር አይናችንም አስክሬኑን ተከትሎ ይዞራል፡፡ ወርደን እንዳንገፋው አቅም የለንም፡፡ ያለን አማራጭ መጨረሻውንማየት ብቻ ነበረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎች የእሽክርክሪት ትርዒቱቀጠለ፡፡ ሁላችንም አዕምሯችን የተነካ መሰለን፡፡ ሳናውቀው እኛንም ያዞረን ጀመር፡፡ ዳንኤል የተሳሰረ አንደበቱን እንደምንም አስገድዶ “ሂድ ኢብሮ! እባክህ ሂድ! በቃ ሂድ… ቻው ወንድሜ!” አለ ከደረቅ ለቅሶ ጋር፡፡
ወዲያው አስክሬኑ የሚዞርበትን ክበብ እያሰፋ ሄዶ ከጀልባዋ መራቅ ጀመረ፡፡ ምህዋሩን እያሰፋ ሄዶ በዝግታ ተሰወረ፡፡ ሁላችንም በሀዘን ተውጠን እስከመጨረሻው በዓይናችን ሸኘነው፡፡”
በእርግጥ ለማመን ይከብዳል! ብዙዎች ባያምኑም ታሪኩ እውነተኛ ነው። ቢቢሲ፥ ስካይ ኒውስ፥ ዘ ጋርዲያን እና አልጀዚራን ጨምሮ ከ15 በላይ ዓለማቀፍ ሚድያዎች የመሀመድን ታሪክ ዘግበውት ዓለም ተነጋግሮበታል። የሰው ልጅ ምንያህል ብርቱ ፍጥረት እንደሆነ ገልቦ ያሳያል።
ድካምና ብርታት፥ ውሳኔናጸጸት፥ ሞትና ትንሳኤ የተዋሃዱበት ታሪክ ነው። የጦርነት፥ የትጥቅ ትግል፥ የስደት፥ የሀገር ክህደት፥ የይቅርታ፥ የእንደገና ጅማሬ ታሪኮች በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ያልፋሉ። ሰው እንዴት ይሄንን ሁሉ መከራ አልፎ ሰው ይሆናል?
የሰሙት እንባቸውን በመዳፋቸው ሰፍረዋል። ያዘኑለትም ያዘኑበትም ነበሩ። የፈረዱለትም ፈረዱበትም ብዙ ናቸው። እሱ ግን “ወደ ፈተና አታግባኝ” በሉ ይላል። ስጋ ሲፈተን፥ ነፍስ ከሞት ጋር ስትጋፈጥ ሁሉም ሰው ሁሉንም ያደርጋልና “አትፍረድ” ባይ ነው።
ዓለምን ያነጋገረውና ያስደነገጠው የመሐመድ ዓደም ኦጋ ታሪክ በሆሊውድ ደረጃ በፊልም ከመውጣቱ በፊት “አትፍረድ” በሚል ርዕስ በአማርኛ ለአንባቢያን ቀርቧል።