✅ ረመዳንን ለመቀበል የሚረዱ 10 ነጥቦች
ባለፈው ለማስታወስ እንደተሞከረው ረመዳንን ለመቀበል መጀመሪያ አላህን በመፍራት ውስጥን ማጥራት በጣም አስፈላጊ ነው ። አሁን ደግሞ አላህ ካለ ረመዳንን ለመቀበል የሚያዘጋጁ 10 ነጥቦችን እናያለን ። እነዚህ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው : –
አንደኛ – አላህ በጤና በሰላም እንዲያደርሰን ዱዓእ ማድረግ
ከነብዩ በዚህ ዙሪያ የተወራ ሐዲስ ቢኖርም የሐዲስ ሊቃውንቶች ደዒፍ ነው ያሉት ስለሆነ ትቼዋለሁ ። ነገር ግን ሰለፎች አላህ እንዲያደርሳቸውና እንዲቀበላቸው ዱዓእ ያደርጉ እንደነበር ተረጋግጧል ።
ሁለተኛ – ረመዳን በመምጣቱ መደሰት
የአላህ መልእክተኛ ሶሓቦቻቸውን ረመዳን በመምጣቱ እንዲህ በማለት ያበስሩ ነበር : –
" የተባረከው የረመዳን ወር መጣላችሁ, መፆሙን አላህ ፅፎባችኋል ( ግዴታ አድርጎባችኋል ) በርሱ ውስጥ የጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ ………" ።
ኢማሙ አሕመድ ዘግበውት ሸይኽ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል ።
ሶስተኛ – ከረመዳን ለመጠቀም መቁረጥና ፕሮግራም ማውጣት
አብዛኛው ሰው ለዱንያዊ ጉዳዩ ፕሮግራም ያወጣል ነገር ግን የአኼራውን ጉዳይ በዘፈቀደ ይሰራል ያውም ዲን አለው ከተባለ ። ብልጥ ማለት ለሚቀጥለው ሀገር የተዘጋጀ ማለት ነው ። በዝግጅቱ ውጤታማ ለመሆን በፕሮግራም መመራት ግድ ነው ። ከዚህ ውስጥ አንዱና ዋነኛው የረመዳንን ወር ቀኑና ማታውን ለመጠቀም ፕሮግራም ማውጣትና ወስኖ መቀበል ብልጠት ነው ።
አራተኛ – ስለረመዳን ህግጋቶች መማር
ሙስሊም የሆነ ሰው አላህን በእውቀት ላይ ሆኖ ሊገዛው ግድ ይላል ። ለዚህ ነው አላህ መልእክተኛውን መጀመሪያ እወቅ ያላቸው ። በመሆኑም አንድ ሙስሊም አላህ በሱ ላይ ግዴታ ያደረገበትን ዒባዳ በእውቀት ላይ ሆኖ መፈፀም ግዴታው ነው ። በጅህልና በሚሰራው ስራ ዑዝር የለውም ። ምናልባት ከአቅሙ በላይ ሆኖበት ካልሆነ በስተቀር ። ዐሊም ባለበት በራሱ ስንፍና ያለእውቀት አበላሽቶ ቢሰራ ከመጠየቅ አይድንም ።
የትኛውንም ዒባዳ ስንሰራ ጠይቀን ተምረን አውቀን መሆን አለበት ። የረመዳን ፆም ህግጋቶችን መማር ለምሳሌ የሚያበላሹትን ፣ አጅሩን የሚቀንሱትን ፣ ቀዳእ የሚያስፈርዱና እንዲሁም ለማፍጠር የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎችና የመሳሰሉትን ማወቅ ግዴታ ነው ።
አምስተኛ – ተውበት አድርጎ መዘጋጀት
ረመዳንን ለመቀበል ከማንኛውም ወንጀል ተውበት አድርጎ መመለስና መፀፀት ዳግም ላለመመለስ ቁርጥ ያለ አቋም መያዝ ያስፈልጋል ። አላህ ዘንድ ያለን ፀጋና ቱሩፋት እሱን በማመፅ ለማግኘነት ማሰብ ሞኝነት ነው ። አንድ ሙስሊም በረመዳን ወንጀሉ ተምሮ ምህረት ለማግኘት ወደ አላህ በሁለመናው መመለስ ይኖርበታል ። አላህ ወደርሱ የተመለሰን ይቀበላል እጥፍ ድርብ ምንዳም ይሰጣል ።
አላህ ካለ ይቀጥላል : –
https://t.me/Khalid_Islamawi_Studio