ወጣቱ ወዳጄ ሆይ…ለእህቴም!
የኢንተርኔት ዘመን ፈተናው ብዙ ነው። ሳትፈልግ የማትፈልገውን ሆነህ ራስህን ታገኛለህ። በዚህ አማላይ የሶሻል ሚዲያ ዘመን ሊተዋወቅህ የሚፈልግህ ሰው ሁሉ ንፁህ ልብ ይዞ የሚቀርብ እንዳይመስልህ፡፡
እርግጥ ነው ካንተ ሊያተርፍ የሚቀርብህ እንዳለ ሁሉ፤ እንደ እባብ ባንተ ላይ ተጠምጥሞ ሊጥልህ የሚቀርብህም አለ፡፡
አንዳንዱ ሰው የሚቀርብህ ዋናው ሸይጧን፤ አሊያም ደግሞ የሰው ሸይጧንም ልኮት ይሆናል፡፡ ያንን ሰው መጣል አልቻልኩም ጣልልኝ ብሎት፡፡
እና አንዳንዴ ሳታውቅ የዚህ ዓይነት ተልዕኮ ባለው ሰው እጅ ላይ ልትወድቅ ትችላለህ፡፡ ሳይፈልግህ የፈለገህ፤ ሳይወድህ የወደደህ የሚመስል ሰላይ ይመጣብሃል፡፡ በጊዜ ሂደት ሆነብሎ አታች እንድትሆን ያደርግሃል፡፡ ከዚያ ዉስጥህ መሸርሸሩን ሲያውቅ ድንገት ከአጠገብህ ዘወር ይላል፡፡ ወደማትፈልገው መንገድ በስንት ውትወታ ከመራህ በኋላ መሀል መንገድ ላይ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ከዚያ እህእ ስትለው መልሶ እንደማያውቅህ ሰው እህእ ምን ላርግልህ ይላል፡፡
እንዲህ የወደቁ ብዙ ናቸው።ነቃ በል ነግሬሃለሁ፡፡ ሱንና የለበሰ ሁሉ ዲነኛ መስሎህ እንዳትበላ፡፡ ከሚያምሩ ኒቃቦችና ፂሞች ጀርባ ስንት ጉድ አለ መሰለህ፡፡ ከሱናና ዋጂቡ መገለጫ ባሻገር አሻግረህ ተመልከት፡፡ አቀራረብህን ቆጥብ፣ አታችመንትህን ቀንስ፡፡
ብዙ የዋህነት ይጎዳሃል፡፡ ጥቂት የዋህነትን ያዝና ብዙ ጥንቃቄን ምረጥ፡፡ ሰው ሁሉ የከተማ ሰው በሆነበት ዘመን የገጠር ልጅ አትሁን፡፡ በፍየል ዘመን በግ ከመሆን ተጠንቀቅ፡፡ ከወደቅክ በኋላ ሰው ስላንተ ምንም ጉዳይ የለውም ስልህ፡፡ አንተ ትልቁ ሰውዬ ብትወድቅ የዛሬ ሰው ምንም ዑዝር አይሰጥህም፡፡ በመጨረሻም ሊል የሚችለው ግዙፉ ዋርካ ወደቀ! ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ! ነው፡፡
ወዳጄ … የአንዳንድ ሰው ሴራው ከሸይጧንም በላይ ሆኗል፡፡ በገዛ እጁ ገዝግዞ ጥሎህ አያዝንልህም፡፡ ትንሽ ፈቅ ብሎ ቆሞ ይስቅብሃል፡፡ ጉድ ሠራሁት ይላል፡፡ ደግሞ የሴት ተንኮል መብዛቱ፡፡ የወንዱም እንደዚያው፡፡
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇
@Lewetatoch_mekir