የሚያጓጓ ትዳር
بسم الله الرحمن الرحيم المقدمة إن الحمد لله، نحمده ونستعينه ونستغفره، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمداً عبده ورسوله، صلي الله عليه وعلى آله وأصحابه ومن تبعهم بإحسان إي يوم الدين وسلم تسليناً كثيراً. أما بعد:
አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
ለዛሬ
የሚያጓጓ ትዳር
ከፍል ሁለት
🎁 ለመሆኑ ጋብቻ ለምን ያስፈልጋል?🎀
ቁጥር 1
በክፍል አንድ እንዳሳለፍ ነው የተወሰነ የጋብቻ ጥቅምን ለማየት ሞክረን ነበር።
በዚህ እርዕስ ደግሞ ጥቅሞቹን በግልፅ በማብራራት ላይ እናተኩራለን።
መቼም የጋብቻ ጥቅምን በሚገባ ስንረዳ ነው የሚያጓጓ ትዳርን የምንናፍቀው።
ለዚህም ነው ኢስላም በጋብቻ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ቅስቀሳ ያደረገውና ያነሳሳው እንዲሁም ጋብቻን እንዲወደድ ያደረገው ግለሰብ፣ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ በአጠቃላይ በጋብቻ ውስጥ ያለውን ጥቅም እንዳገኝ በማሰብ ነው።
አላህ ሱበሀነ ወተዓላ በዚህ በተዋበ የጋብቻ ህይወት ውስጥ ብዙ ተቆጥረው የማያልቁ፣ እንደ ማር የሚጣፍጡ፣ የፀጋ በረከቶችን ስላደረገበት ይህን በረከት የሰው ልጅ እንዲቀምስ ለማድረግ ሲባል ነው ኢስላም ሙሉ ትኩረት የሰጠው።
በጥቅሉ ስለ ጋብቻ ይህን ያህል ካልን የጋብቻ ጥቅሞችን አንድ ሁለት ብለን የተወሰኑትን እንመልከት።
ሀ, #የሰው_ልጅ_የዘር_ሀረግ_እንዲቀጥል_ለማድረግ _………
√የሰው ልጅ የዘር ሀረግ እንዳይቋረጥ ዘርን ለማብዛት የሚያስችል ምርጡ ዘዴ ወይም የህይወት ጎዳና አማራጭ የሌለው የተቀደሰው ጎዳና ጋብቻ ብቻ ነው። የምድር ጌጦች ሰዎች እንደመሆናቸው መጠን ምድር ሰውን ትፈልጋለች። ከዚህም አኳያ የሰው ልጅ የራሱን አምሳል እየተካ እስከ ፍፃሜ ቀን ድረስ ለምድር አስተዋፅኦ የሚያደርግበት መስመር ጋብቻ ብቻ ነው።
ይህንኑ ሀሳብ ነብዩ መሀመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም በአንድ ሀዲሳቸው ሲገልፁት ብለው የሰው ልጅ ጋብቻ በማድረግ መባዛት እንዳለበትና የሰው ዘር ሀረግ እንዳይቋረጥ አብክረው ይመክራሉ።
ኢማሙ አህመድና ኢብኑ ሂባን በዘገቡት ሀደስ ላይ በማለት ጋብቻ ውስጥ ሊገኝ የሚችለውን የመባዛትን ጥቅም ቁልጭ አድርገው አሳይተዋል።
በመሰረቱ የዘር መብዛት በራሱ ግለሰባዊ፣ ማህበራዊና፣ጠቅላላ ህዝባዊ (ኡማዊ) ጥቅም እንዳለው ቀደም ሲል በነበረው ህዝብ ውስጥ ከመታወቁም የተነሳ እንዲህ ይባል ነበር [የበላይነት ለብዙሃን ነው] በማለት በዝቶ የታየው አካል ማህበረሰብ ትልቅ ክብር ይሰጠው ነበር፣ከዚህም አልፎ ይፈሩ እንደ ነበር ታሪክ ያስተምረናል።ከዚህ አንፃር ለጋብቻ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል።
በጋብቻ ሰበብ ከሚገኘው ጥቅም አንዱ የዘር ሀረግ ማስቀጠል ሲሆን በልጆች ሳቢያ ሊገኙ የሚችሉ ጥቅሞችን ኢማሙል ጋዛሊ የተባሉት ታላቅ አሊም ( አል ዚዋጀል ኢስላሚ አስሰኢድ) በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ዘርዝረዋል። ትርጉማቸውን እነሆ
√ የሰው ልጅ የዘር ሀረግ እንዳይቋረጥ በማድረግ የአላህን ውዴታ ማግኘት፣
√ረሱል ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በህዝብ ብዛት ከአንቢያዎች የበላይ እንዲሆኑ በማድረግ የረሱል ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን ውዴታ ማግኘት፣
√ መልካም ልጅ ወልዶ ከመልካም ልጅ የሚገኘውን ዱዓ በማግኘት በህይወትም ሆነ በሞት ተጠቃሚ መሆን
√ ልጆች በልጅነት ከሞቱ ለወላጅ የቂያማ ቀን (ሸፈዓ) አማላጅ ስለሚሆኑ ይህንን ጥቅም ማግኘት፣
√ የራስን ፍሬ በአይን በማየት የሚገኝውን ደስታ በልጆች ማግኘት፣
√ በተለይ ወላጆች ወደ እርጅናው የእድሜ እርከን ሲደርሱ ጧሪ ቀባሪ የሚሆን ልጅ ለማግኘት ያስችላቸዋል።
ከብዙ በትቂቱ ጋብቻ ካሉት ጥቅሞች መካከል እነዚህ ነበሩ።
ኢንሻአላህ
ክፍል ሁለት ቁጥር 2 ይቀጥላል።
https://t.me/LoveOfMarriage
🔻🔻🔻
ለወዳጀዎ ሼር ያድርጉት