የቱሉ ዲምቱ መስጊድ ጥሪ
የዛሬ ሦስት ዓመት ረመዳን ላይ ለመስገድ ጠጠር በበዛበት ኳስ በዶ ሜዳ ላይ ብንሞክር በደንብ አስከባሪዎች ተባረርን። አዝነንም ከፊሎቻችን ሦስት ኪሎ ሜትር ያህል ርቀን ዓለም ባንክ ሠገድን። የዛሬ ሁለት ዓመት የድንኳን መትከያ ቦታ አንዱ ብሎክ ጀርባ ተፈቅዶልን ከንፋስ ጋር እየተናነቅን ጨረስን። የተፈቀደው ለ30 ቀናት ስለነበረ በ31ኛው ቀን ድንኳኑ ፈረሰና ተበተንን። ያኔ በጣም አዘንኩ። አምናም እንደዚሁ በድንኳን መስገድ ተፈቀደ። እሱም ቢሆን ያለቀው ከንፋስና ከዝናብ ጋር በመፋለም ነው። አንዳንድ ቀን ኢትዮጵያዊነትን መብት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሲሆን ባህር ላይ ሆኖ እንደመስገድ የሚታሰብ ነው። ዘንድሮ ቦታ ተፈቅዶ የቆርቆሮ መስጅድ ተቀልሷል። ውስጡ አፈር ሲሆን ለመቆምም ሆነ ለስጁድ አይመችም። በዚህ ረገድ የሚማረር የለም። ግን ብዙ ችግር አለ። የቁርዓን፣ የኪታብ፣ የምንጣፍ፣ የሮቶ፣ የሌሎችም ብዙ ቁሳቁሶች ችግር አለ። ስለዚህ የምትችሉትን ሁሉ የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉ። ለሚዘረጉም ንገሩልን። በናንተ ትብብር የዘንድሮን ረመዳን ደስ ብሎን እንድናከብረው ተባበሩን።
ልጆቼና ወዳጆቼ፣ ያለ ዛሬ አልጠየቅሁም አሁን ግን እባካችሁ ጥሪው እንዲዳረሰ ሸር አድርጉት? ስለተባበራችሁ ምንዳችሁን ከአላህ ታገኛላችሁ።
••••••••••••
ማገዝ የምትችሉ
Teshome Berhanu Kemal ብላችህ በፌስቡክ አናግሩዋቸው
ምንጭ ዛውያ ቲቪ
@Loveyuolema