=== ኢማን
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ በሆነው ፅሁፌን እጀምራለሁ፡፡
✍🏽ሼይኽ አል-ኢስላም ኢብን ተይሚያህ (ረሂመሁሏህ) ኢማነን በተመለከተ አኢማዎች በተለያየ ገለፃ እንደገለጹትና የሁሉም ዋና እይታቸው በሙርጂኣዎች ቢድዓ ላይ ምላሽ መሥጠት ነበር፡፡
እንዲህ ብሏል ፦
" ከዚህ ርዕስ ውስጥ የሠለፎች ንግግር ና የሱና ሊቃውንቶች በኢማን ላይ ያላቸው ተፍሲር በተመለከተ:- አንዳንዴ "እሱ(ኢማን) ንግግርና ተግባር ነው" ይላሉ፡፡ አንዳንዴ " ንግግር ፥ ተግባርና ኒያ ነው" ይላሉ፡፡ አንዳንዴ "ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያና ሱና መከተል ነው" ይላሉ፡፡ አንዳንዴ " በምላስ መናገር ፥ በቀልብ ማመን ፥ በሰውነት መተግበር ነው" ይላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ትክክለኛ (ፍቺ) ነው፡፡ እዚህ ጋር ሠለፎች "ኢማን ንግግርና ተግባር ነው" በሚለው ትርጉማቸው የሚፈልጉበት "" ንግግር ፦ የቀልብ ንግግርና የአንደበት ንግግር "" ተግባርም ፦ የቀልብ ተግባር እና የሰውነት ተግባር"" ነው የሚፈልጉበት፡፡
*ኢዕቲቃድን* ማመንን ሽቶበት የተናገሩት *ንግግር* በሚለው በጉልህ የምናውቀው ንግግር እንጂ ሌላ የሚያስረዳ ነገር የለውም ብለው ወይም ይህን ፈርተው *በቀልብ ማመን* የሚለውን ጨመሩ፡፡
"ኢማን ንግግር፥ ተግባር ፥ ኒያ" ያሉት ደግሞ *ንግግር* የሚለው ማመንና በምላስ መናገርን አብሮ ይይዛል አሉ፡፡ ነገርግን *ተግባር* የሚለው ከርሱ ኒያ እንደሚያካትት ስለማያስረዳ *ኒያ* ብለው ጨመሩ፡፡
*ሱና መከተል* ብለው የጨመሩት ደግሞ ሌሎች ባጠቃላይ አሏህ ዘንድ ተወዳጅ ሊሆኑ አይችሉም ሱና በመከተል እንጂ ብለው ነው፡፡
(ንግግርና ተግባር ሲባል) እነሱ ሁሉንም አይነት ንግግርና ተግባር አይደለም የፈለጉበት፡፡ ነገር ግን የፈለጉበት በሸሪዓ የተደነገጉ ንግግርና ተግባራት ነው፡፡ ነገር ግን ዋና አላማቸው እነዚያ ኢማንን *ንግግር ብቻ ነው* የሚሉ ሙርጂኣዎች ላይ መልስ መሥጠት ነበር ግባቸው ፡፡ ንግግርና ተግባር ነው በማለት መለሱላቸው፡፡
°እነዚያ አራት አይነት(ክፍል) አድርገው የፈሰሩትም ምን ፈልገውበትም እንደነበር አስቀምጠዋል፡፡ ልክ ሰህል ቢን ዐብዱሏህ አት-ተስተሪይ "ኢማን ምንድነው?" ተጠይቆ ነበር፡፡ እንዲህ አለ ፦
"(ኢማን) ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያ ፥ ሱና ነው፡፡ ምክንያቱም ኢማን ፦ ንግግር ብቻ ከሆነ ያለምንም ተግባር እሱ #ኩፍር ነው፡፡ ንግግር ፥ ተግባር ብቻ ከሆነ ኒያ ሳይኖረው እሱ #ኒፋቅ ነው፡፡ ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያ ከሆነ ያለ ሱናህ ይህ #ቢድዓ ነው፡፡ " ብሏል፡፡
📚መጅሙዕ አልፈታዋ፡ 7/170
👆ይመሥላል የሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ ንግግር፡፡
☝️🏽ወቢላሂ አት-ተውፊቅ
•════•••🌺🍃•••════•
https://t.me/joinchat/AAAAAE34J4iQQtaqDuVOsA