ወተት ላይ ዉሃ መጨመር?
አሚሩል ሙእሚኒን ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረድየላሁ አንሁ) አንድ ለሊት ላይ ወጣ ከዛም አንዲት ሴት ለልጇ እንዲህ ስትል ሰማት
“ወተቱ ላይ ዉሃ ጨምሪበት”
ልጅቷም “እንዴት ወተት ላይ ዉሃ እጨምራለሁ አሚረል ሙእሚኒን ከልክሎ ሲያበቃ?” አለች፡፡
እናትም “አሚረል ሙእሚኒን አሁን ይህን አያውቅም (አያየንም)” አለች፡፡
ልጅም “ኡመር (ረድየላሁ አንህ) ባያውቅ የኡመር አምላክ ያውቃል” አለች፡፡
ምንጭ ሲየር ኡመር ኢብን አብድል አዚዝ ገፅ 23
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ልችቷን ኡመር ባያያት እንኳን ወተት ላይ ውሃን እንዳትጨምር ያደረጋት ምን ይመስላችኋል?
መልሱም የአላህ ስምና መገለጫዎች (በባህሪያቱ) ጠንቅቃ ማወቋ፣ ሙሉ የሆነን እምነት ማመኗም ነው፡፡ ለምሳሌ ልጅቷ ካመነችባቸው ከአላህ መገለጫ ባህሪዎች ውስጥ እዚህ ታሪክ ላይ የተጠቀሰው አላህ ሁሉን ተመልካች መሆኑን ነው፡፡ ይህም ለአላህ ተመልካች የሚለው ስሙን የሚያስገነዝብ ነው፡፡
ዛሬ መንግስታት ስንት አዋጆችን እንዲፈፀሙላቸው ያወጣሉ የሚፈፅመው ጥቂት ነው፡፡ ማጭበርበር በዛ፡፡ በኮምፒውተር ቢታገዙም አሁንም ማጭበርበሩ ስልቱ በጣም በረቀቀ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ግን የትም ቦታ ላይ መሪዎች ባያዩንም አላህ ያየናል ብለው አላህን ፈርተው ከተከለከሉት ነገር ይቆጠባሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው የእውነተኛው ዘመን የማይሽረው ሃይማኖት ሰውን የማነፅ ብቃት ነው፡፡
ከዚህ የምንረዳው ፍጡራን እውነተኛ ፈጣሪያቸውን ሲያውቁ ሲፈሩትና ሲጠነቀቁት፣ እውነተኛውን ብቸኛ ሃይማኖት ሲከተሉ፣ ለአለማት እዝነት የተላኩትን መልክተኛ ሙሉ ለሙሉ ሲቀበሉ ወደ እንዲህ አይነት ፈሪሃ አላህ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ እውቀትን እንዲጨምርን፣ ቀጥተኛውን መንገድ የተከተሉትን እነዛን ምርጥ ትውልዶች አስተምህሮት ተከታይ እንዲያደርገን ደጋግመን እንለምነው፡፡ ምክንያቱም ያለ እውቀት አላህ አይመለክም፡፡ እንደ መንገድም ብቸኛዋ የሀቅ መንገድ የሰለፉነ ሷሊሂን ጎዳና ናትና አላህ በእሷ ላይ ያፅናን፡፡
አላህ ሆይ! እውቀትን ጨምርልን፣ ቀጥተኛውን መንገድ ምራን
•════•••🌺🍃•••════•
https://t.me/joinchat/AAAAAE34J4iQQtaqDuVOs