#ጥቂት_ስለ_ነጃሺ!!
✍#አስሐመተ_ኢብኑ_አብጀር ይባላል ሙሉ ስሙ።
አባቱ ደግሞ የሐበሻ ንጉስ ነበር።የአስሐማ አባት ከእሱ ውጭ ሌላ ልጅ የለውም።አንድ ፍሬ ብቻ ነበር።
የአስሐማ አጎት ደግሞ 12 ልጆች ነበሩት።
✍የሐበሻ ባላባቶች ነገር መሰንጠቅ ጀመሩ።ይሄ ንጉስ ያለው ልጅ አንድ ብቻ ነው።በህይዎት እያለም የሚረዳው ልጅ የለውም።ከሞተም በኋላ ንግስናውን ልጁ ስለሚይዝ ሐገሪቱን አደጋ ላይ ይጥላታል።ስለዚህ ንጉሱን ገድለን ወንድምዮው ይንገስ።ከዛ እሱ ቢሞትም ጠንካራ ልጆች ስላሉት እነሱ ዙፋኑን ይረከባሉ ተባባሉ።
✍በዚህም ሐሳባቸው ፀና።የነጃሺን አባት ገደሉትና ንግስናውን ለነጃሺ አጎት አስረከቡ።
በዚህ ወቅት ነጃሽ ገና ልጅ ነበር።አጎቱ በአባቱ ምትክ ንግስናን ተቀበለና ህፃኑን ነጃሺን አስጠጋው።በፍቅር ይንከባከበው ጀመር።
✍አስሐማ(ነጃሺ)ብሩህ አእምሮ ያለው አርቆ አሳቢ፣አእምሮው በእውቀት የታጨቀ፣ፀባየ ሰናይ ውብ ልጅ ሲሆን አጎቱ ወደደው።በጣም ያቀርበውና ይንከባከበው ጀመር።
ከልጆቹ በላይ ለነጃሺ ቦታ ይሰጠው ጀመር።
✍ይህንን ሁኔታ የተመለከተቱት የሐበሻ ባላባቶች ስጋት ላይ ወደቁ።ይሄ ሰውየ ልጆቹን አደለም በንጉስነት የሚሾመው።ይህንን የወንድሙን ልጅ አስሐማን የሚሾም ይመስላል።
አስሐማ ከተሾመ ደግሞ እኛ አለቀልን።የአባቴ ገዳዮች ናቸው ብሎ ቅድሚያ ስልጣኑን እኛን በመግደል አሐዱ ይላል ተባባሉ።ስለዚህ እንግደለው የሚል ሐሳብ አመጡ።
✍ለአጎቱ ይህንን ልጅ ካልገደልክ እኛ ስጋታችን ጨምሯል።ልጁንም በጣም አቅርበኸዋል ስለዚህ ሸግተናልና ግደል አሉት።
አጎትዮው አላደርገውም አለ።አባቱን ገደላችሁ ዛር ደግሞ ልጁን ልትገድሉ አላቸው።
✍አልገድልም ካልክ ከሐገር አስወጥተህ የትም ጣለው አሉት።በዚህ ሐሳብ አጎትዮው ተስማማ።
✍ለግላጋው አስሐማ(ነጃሺ)ከሐገር ተባረረ።በለጋ እድሜው በሐበሻ ሹማምንቶች አባቱን ያጣው ነጃሺ አሁን ደግሞ በነዚሁ ግፈኞች ጫካ ተወረወረ!!
✍እሱ ከሐገር እንደተባረረ አላህ ታዓምሩን አሳየ!!
ሐገሪቱ አይታው በማታቀው ዳመና ተሸፈነች።ሐገር የሚያንቀጠቅጥ ንፋስ።
ጥቁር ዳመና ገና ሲመለከቱት ሽንት ሽንት የሚያሰሰብል።በዛ ላይ ትንትግ ትንትግ የሚል መብረቅ።
የሚስገመገም ነጎድጓድ፣እድም እግው እያለ ሰውን ጭንቅ ውስጥ የሚከት ትዕይንት ተከሰተ።
አንድ ጊዜ የተምዘገወገው ነጎድጓድ ከሐበሻው ንጉስ ቤተመንግስት ላይ አረፈ። #የሐበሻው_መሪ የነጃሺ አጎት በመብረቅ ሞተ!!
✍ሐገሪቱ ሜዳ ላይ ቀረች።የንጉሱ ልጆችም እዚህ ግቡ የሚባሉ አደሉም።ነግስናው ደግሞ ማንም ተነስቶ አይዘውም በዘር ስለሚሄድ።
ውጥንቅጡ ወጣ።
✍የውጭ ጠላቶች ወደ ሐገሪቱ አሰፈሰፉ።ሊቀራመቷት ጥፍራቸውን አወጡ።
ኧረ የመሪ ያለህ ይባል ጀመር።
✍ያንን የጣላችሁትን ልጅ ፈልጉ ተባለ።ቆላ ደጋው ነጂሺን ፍለጋ ተሰማራ።በመጨረሻም አገኙት።
አሽሞንሙነው ወስደው የክብር ዘውዱን ጫኑለት!!!
✍#ንጉስ(ነጃሺ)የሚባል ማዕረግ ተሰጠው።
በዙልም የጨቀየችውን ሐገር ወደ ፍትህ ማማ ያዘልቃት ጀመር።ሐገሪቱን ሊቀራመቱ ያሰፈሰፉት ጠላቶችም በነጃሽ ቀንዳቸው ተሰበረ።
✍የኢስላምና የሙስሊሞች ባለውለታ #አስሐማ(ነጀሺ),በዚህ መልኩ ነበር ንግስና ላይ የወጣው!!
ከወደዳችሁት #ሼር
@Loveyuolema @Loveyuolema