🔰🔰 #የሀይማኖት_ንፅፅር
#ክፍል_አንድ 1⃣
👳♀ #ሴት_ልጅ_በኢስላም_እይታ ☪
✡የሰው ልጅ ምድር መኖር ከጀመረ አንስቶና የፈጣሪ ህግጋቶች ከወረዱለት ጀምሮ ሴት ልጅ ልክ እንደ ሰብአዊ ፍጡር ከወንድ ጋር በኩል እይታ ትታይ ነበር!፡፡ ከዘመናቶች ቡሃላ ግን የፈጣሪ ህግጋቶችና መመሪያዎች በመበረዛቸው ምክንያትና ሰይጣናዊ የኑሮ ዘይቤ በመስፋፋቱ ምክንያት ሴትን ልጅ ልክ እንደ ሰብዓዊ ፍጡርነት መቀበል #ይቀር ጀመር፡፡ አንዳንዶቹ ሰብዓዊ ፍጡነርቷን ቢቀበሉም ወንዶችን ለማገልገል እንደተፈጠረች አድርገው ይቆጥሯት ጀመር። ግን ምስጋና ይገባውና ኢስላም ዳግም አንሰራርቶ ሴትን ከእንዲህ ዝቅጠት ዓይነቱ አስተሳሰብ ነፃ አወጣ። ሰብዓዊ ፍጡርነቷን አፀና። ኃላፊነቷን የመሸከም፣ የተጠያቂነት እና በሥራዋም ጀንነትን የመጎናፀፍ ብቃት እንዳላት አረጋገጠ። የተከበረች ሰብዓዊ ፍጡር እንደሆነችም አወጀ። ልክ ከወንዱ ጋር እኩል የሰብዓዊ መብቶች ተጋሪ መልሶ አደረጋት። ሁለቱም የአንድ ግንድ ቅርንጫፎች ናቸውና። ወንድማማቾች ናቸውና። የአንድ አባትና የአንድ እናት ልጆች!። የሐዋና የአደም ክፋዮች!። በአፈጣጠር እኩል ናቸውና። በኃላፊነትና ተጠያቂነት እኩል ናቸው። በምንዳና ፍጻሜም እኩል ናቸው። ቁርኣን ይህን በማስመልከት ሲናገር፡-
★“እናንተ ሰዎች ሆይ! ያን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን፤ ከርሷም ተጣማሪዋን የፈጠረውንና ከነኝህ ከሁለቱ በርካታ ወንዶችንና ሴቶችን ያበዛውን
ጌታችሁን ፍሩ። ያን በርሱ (የጋራ መብቶቻችሁን) የምትጠያየቁበትን አላህን ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ ተጠንቀቁ)። አላህ እናንተን ዘወትር
ተጠባባቂ ነውና።” (አን-ኒሳእ 4፤ 1)
✡በመሆኑም የሰውን ልጆች ባጠቃላይ- ሴቶችንም ወንዶችንም- አምላካቸው የፈጠራቸው ከአንዲት ነፍስ
ነው። ይህችም ነፍስ ምሉዕነትን ትጎናፀፍ ዘንድ ተጣማሪዋን አደረገላት። ይህንንም በሌላ አንቀጽ እንዲህ ገልጾታል፡-
★“እርሱ ያ ከአንድ ነፍስ የፈጠራችሁ፤ ከርሷም ተጣማሪዋን -ይረካበት ዘንድ- የፈጠረ (አምላክ) ነው።” (አል-አዕራፍ 7፤ 189)
✡ከዚህች አንድ ቤተሰብ ውስጥ በርካታ ወንዶችንና ሴቶችን አስገኘ። ሁሉም የአንድ አምላክ ፍጡሮች ናቸው። የአንድ አባትና የአንዲት እናት ልጆች። እናም በወንድማማችነት ተሳስረዋል። ይህም በመሆኑ አንቀፁ የሰው ልጆች አምላካቸውን እንዲፈሩ፤ የዝምድና ትስስራቸውንም እንዲጠብቁ አዘዘ፡-
★“ያን በርሱ (የጋራ መብቶቻችሁን) የምትጠያየቁበትን አላህ ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ ተጠንቀቁ)።” (አን-ኒሳእ 4፤ 1)
✡በሌሎች አናቅጽ መልዕክት መሠረት ወንድ የሴት ወንድም ነው። ሴትም የወንድ እህት ናት። የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) ይህን አስመልክተው ሲናገሩ፡-
➊“ሴቶች የወንዶች እህቶች ናቸው።” (አህመድ፣ አቡዳዉድ፣ ቲርሚዚና ዳረሚይ ዓኢሻን ዋቢ በማግረግ ዘግበውታል።)
✡በመለኮታዊ ትእዛዙ፣ በአምልኮዎችና በሃይማኖታዊ አጀንዳዎችም ሴት ልጅ ከወንድ እኩል መሆኗን ቁርኣን ሲያስተምር፡-
★“ሙስሊም ወንዶችና ሙስሊም ሴቶች፣ አማኝ ወንዶችና አማኝ ሴቶች፣ ታዛዥ ወንዶችና ታዛዥ ሴቶች፣ እውነተኛ ወንዶችና እውነተኛ ሴቶች፣
ታጋሽ ወንዶችና ታጋሽ ሴቶች፣ አላህን ፈሪ ወንዶችና አላህን ፈሪ ሴቶች፣ መጽዋች ወንዶችና መጽዋች ሴቶች፣ ጿሚ ወንዶችና ጿሚ ሴቶች፣ ብልቶቻቸውን (ከዝሙት) ጠባቂ ወንዶችና ሴቶች፣ አላህን በብዛት የሚያወሱ ወንዶችና ሴቶች አላህ ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን አዘጋጅቶላቸዋል።” (አል-አሕዛብ 33፤ 35)
✡በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ኃላፊነቶች ቁርኣን ሁለቱንም ጾታዎች እኩል ያደርጋል።
★“የወንድና የሴት አማኞች ከፊሉ የከፊሉ ረዳት ናቸው። በመልካም ያዛሉ። ከክፉ ይከለክላሉ። ሶላትንም ደንቡን አሟልተው ይሰግዳሉ። ዘካንም
ይሰጣሉ። አላህንና መልዕክተኛውንም ይታዘዛሉ። ለእነርሱ አላህ ያዝንላቸዋል። አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።” (አት-ተውባህ 9፤ 71)
✡በአደም ታሪክም ውስጥ መለኮታዊ ትእዛዝ የተላለፈላቸው ለርሱም ለባለቤቱም ነው፡-
★“አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ ገነት ውስጥ ተቀመጥ። ከርሷም (ከመልካም ፍሬዎቿም) በፈለጋችሁበት ሥፍራና ጊዜ ያሻችሁትን ተመገቡ።
ይህችን ዛፍ ግን አትቅረቡ፤ ከበዳዮች ትሆናላችሁና።” (አል-በቀራህ 2፤ 35)
✡ይሁንና በዚህ ታሪክ ውስጥ- በቁርኣን ትረካ መሠረት- ኃጢአት የማሠራቱን “ተግባር” የፈፀመው ሰይጣን እንጅ ሐዋእ አይደለችም።
★“ሰይጣንም ከርሷ (ከገነት) አስወገዳቸው። ከነበሩበት (በውስጧም ከነበረው የገነት ድሎትም) አወጣቸው።” (አል-በቀራህ 2፤ 36)
✡ሐዋእ ፍሬዋን ብቻዋን አልበላችም። ጀማሪም አልነበረችም። ስህተቱ የሁለቱም ነበር። ፀፀቱና ንስሐቸውም እንዲሁ የሁለቱም ነበር።
★“ጌታችን ሆይ! ራሳችንን በድለናል። ካልማርከንና ካላዘንክልን ከከሣሪዎች እንሆናለን በማለት (ጌታቸውን) ተማፀኑ።” (አል-አዕራፍ 7፤23)
✡እንደውም በአንዳንድ የቁርኣን አንቀጾች ኃጢአቱ በዋነኛነት የአደም መሆኑ ተገልጿል፡-
★“ከዚህ ቀደም ከአደም ቃልኪዳን ይዘናል። ግና ረሳው። ቁርጠኝነትንም አላገኘንበትም።” (ጧሃ 20፤ 115)
★“ግና ሰይጣን ጐተጐተው። አደም ሆይ! ዝንተዓለም መኖርና የማይወገድ ሥልጣን ማግኘት የምታስችልህን ዛፍ ላመላክትህን? አለው።” (ጧሃ
20፤ 120)
★“አደም (በዚህ አኳኋን) የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ። ስህተት ላይ ወደቀም።” (ጧሃ 20፤ 121)
✡ንስሐውም እንዲሁ የርሱ ብቻ እንደሆነ ተደርጐ ቀርቧል፡-
★“ከዚያም ጌታው መረጠው። ንስሐውንም ተቀበለው። መቀናትንም ለገሰው።” (ጧሃ 20፤ 122)
✡ከነዚህ አናቅጽ የምንረዳው የኃጢአቱ አነሳሽ እርሱ እንደነበር እና ሐዋእ ተከታይ ብቻ እንደነበረች ነው። ምንም ይሁን ምን የሐዋእ ኃጢአት በርሷ ብቻ ተወስኖ የሚቀር እንጅ ወደ እንስት ልጆቿ የሚተላለፍ አይደለም። የአንዷን ነፍስ ኃአጢት ሌላዋ አትሸከምምና።
★“ይህች ያለፈች ሕዝብ ናት። ለርሷም የሥራዋ አላት። ለናንተም የሥራችሁ አላችሁ። እነርሱ ይሠሩት በነበረው እናንተ አትጠየቁም።” (አል-በቀራህ 134)
✡ሁለቱም ፆታዎች በምንዳና ጀነትን በመጎናፀፍ እኩል መሆናቸውን ቁርኣን ሲያብራራ፡-
★““ጌታቸውም ልመናቸውን ተቀበለ። እኔ ከናንተ ውስጥ ሴትም ሆነ ወንድ የማንኛችሁንም (መልካም) ሥራ ከንቱ አላደርግም። ከፊላችሁ የከፊሉ አካል ነው (አለ)።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 195)
✡መልካም ሥራ እንደማይጠፋ በግልፅ አስቀምጧል! የወንድም የሴትም መልካም ሥራ። ሁለቱም ፆታዎች አንድ ናቸው። ከአንድ ዓይነት አፈር ከተመሳሳይ ቁስ ተፈጠሩ። አላህ እንዲህ ብሏል፡
★“ከሴትም ይሁን ከወንድ አማኝ ሆነው መልካም የሠሩትን ጥሩ ሕይወትን እናኖራቸዋለን። ምንዳቸውንም ከሠሯቸው መልካም ሥራዎች ይበልጥ መልካም በሆነው(መኖሪያ) እንመነዳቸዋለን።” (አን-ነሕል 16፤ 97)
★“ከሴትም ከወንድም አማኝ ሆነው መልካም ሥራዎችን የሚሠሩ በእርግጥም ገነትን ይገባሉ። ቅንጣት ያህልም በደል አይደርስባቸውም።” (አን-
ኒሳእ 4፤ 124)
✡የሴትን ልጅ የገንዘብ መብቶች በተመለከተ ደግሞ ኢስላም የበርካታ ዐረብና ዐረብ ያልሆኑ ሕዝቦች ሴትን ልጅ ከባለሃብትነትና ከውርስ የመከልከል፣
ወይም በሃብታቸው ያሻቸውን እንዳያደርጉ የማፈን፣ ወይም ሃብታቸውን በባሎቻቸው የመነጠቅ ልምድ #ተቃርኗል።👇👇