ሃብት የመያዝ፣ ሃብታቸውን በሕጋዊ መንገድ ለሚፈልጉት ነገር የማዋል መብትን አፅድቆላቸዋል። ኑዛዜን እና ውርስንም ደንግጎላቸዋል።
የመሸጥና የመግዛት፣ የማከራየት፣ የመስጠት እና የማዋስ፣ ወቅፍና ምፅዋት የመለገስ እና ሌሎችም ውሎች የመፈፀም መብትን አጎናፀፋቸው። ለገንዘባቸውና ለጥቅማቸው በሕጋዊ መንገድ የመከራከር መብትም ከዚሁ ይመነጫል።
✡ሴት ልጅ እንደ ወንድ ሁሉ ዕውቀት የመፈለግም መብት አላት። ከመብትም አልፎ ግዴታ
ተደርጎባታል። ሐዲስ የሚከተለው ተላልፏል።
➊ﻃﻠﺐ ﺍﻟﻌﻠﻢ ﻓﺮﻳﻀﺔ ﻋﻠﻰ ﻛﻞ ﻣﺴﻠﻢ
“ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው።”
✡በሁሉም ላይ። ፆታ አልተለየም። ይህ በዑለሞች አጠቃላይ ስምምነት የፀደቀ ነው። ሴት ልጅ ወደ መስጊድ ሄዳ የጀመዓ ሶላት መስገድም መብትም አላት። እንደ ወንዱ ሁሉ እርሷም የግዴታ ዒባዳዎችን የመፈፀም ግዴታ አለባት።
ሶላት፣ ዘካ፣ ሐጅ፣ ፆም እና ሌሎችም የኢስላም መሠረታዊ ተግባራት የማከናወን ግዴታ አለባት። እንደ ወንዱ ሁሉ ምንዳ ታገኝባቸዋለች። ልክ
እንደ ወንዱ ማኅበራዊ ኃላፊነትም አለባት።
★“የወንድና የሴት አማኞች ከፊሉ የከፊሉ ረዳት ናቸው። በመልካም ያዛሉ። ከክፉ ይከለክላሉ።” (አት-ተውባህ 9፤ 71)
✡ጥበቃና ከለላ ለጠየቃት የመስጠት መብትም አላት። ከለላዋም ይከበርላታል።
➊የአቡ ጧሊብ ልጅ ኡም ሃኒእ መካ በድል በተከፈተችበት ዕለት ከአጋሪዎች ለአንዱ ከለላ ሰጥታለች። በእርግጥ ወንድሟ ሊገድለው ፈለገ። ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰሰችው። “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እኔ ጥበቃና ከለላ የሰጠሁትን ሰው የእናቴ ልጅ ሊገድለው ያንገራግራል” አለቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም፡- “አንች ከለላ የሆንሽለትን ከለላ
ሰጥተነዋል” አሏት። (ቡኻሪና ሙስሊም)
✡ይህ ሁሉ የሚያመላክተው ኢስላም ሴትን ልጅ በተለየ እይታ ከወንድ አሳንሶ እንደማያይና ሴት ልጅ ልክ እንደ ወንድ ሙሉ መብቶች እንዳሏት ነው!!!
📌ክርስትናስ ስለሴት ልጅ መብት ምን አለ!!!?
ሴት ልጅ በክርስትና እይታ...Part 2⃣ ይቀጥላል....
🔄ይህንን ተከታታይ የሀይማኖት ንፅፅር ለሌላ ሀይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን በማድረስ ኢስላማዊ ግዴታዎን ይወጡ!
Join👇
@Loveyuolema @Loveyuolema