🔰🔰 #የሀይማኖት_ንፅፅር
#ክፍል 6⃣
🐶 #ውሻ_ለምን_በእስልምና_ነጃሳ_ተባለ!?
......ውሻ በኢስላም የተጠላ ነው የሚል አንድም ሃይማኖታዊ ማስረጃ ከቅዱስ ቁርኣንም ሆነ ከሐዲሥ ማቅረብ አይችሉም፡፡ ይህም ተራ አሉባልታ ነው፡፡ ኢስላም ውሻን መጥላትን ሳይሆን እያስተማረን ያለው ውሻን ማሳደግን በምን አይነት መልኩ መሆን እንዳለበት በመግለፅና ገደብ በማበጀት ብቻ ነው፡፡
ነገር ግን #ከውሻ_አፍ_የሚወጣው_ልጋግ የሰው ልጅን የሚጎዱ ጀርሞችን ስለያዘ ከዚህ ነገር እንድንታቀብ እስልምናችን ያዘናል። የውሻ ልጋግ ነጃሳ መሆኑን ይህ ሐዲስ ያመላክታል።
ﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ -: “ ﺇﺫﺍ ﺷﺮﺏ ﺍﻟﻜﻠﺐ ﻓﻲ ﺇﻧﺈ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﻓﻠﻴﻐﺴﻠﻪ ﺳﺒﻌﺎ ” ـ ﻭﻟﻤﺴﻠﻢ ” ﺃﻭﻻﻫﻦ ﺑﺎﻟﺘﺮﺍﺏ ”
ﻭﻟﻪ ﻓﻲ ﺣﺪﻳﺚ ﻋﺒﺪﺍﻟﻠﻪ ﺑﻦ ﻣﻐﻔﻞ : ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ -: “ ﺇﺫﺍ ﻭﻟﻎ ﺍﻟﻜﻠﺐ ﻓﻲ ﺍﻹﻧﺈ ﻓﺎﻏﺴﻠﻮﻩ ﺳﺒﻌﺎ ﻭﻋﻔﺮﻭﻩ ﺍﻟﺜﺎﻣﻨﺔ ﺑﺎﻟﺘﺮﺍﺏ ”.
➊. አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል:- ”
☞ከእናንተ አንዳችሁ ከእቃው ውስጥ ውሻ ከጠጣ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።” ሙስሊም ባሰፈሩት ዘገባ: – ” የመጀመሪያውን በአፈር” የሚል ታክሏል።
➋. አብደላህ ኢብን ሙገፈል እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንድህ ብለዋል:- ” ውሻ ከእቃ ውስጥ ልጋጉን ከጣለ (እቃውን) ሰባት ጊዜ እጠቡት። ስምንተኛውን በአፈር ፈግፍጉት ከሐዲሱ የምንማራቸው ቁምነገሮች!
1ኛ. የውሻ ልጋግ ነጃሳ መሆኑን ይህ ሐዲስ ያመላክታል።
2ኛ. ውሻ ከእቃ ውስጥ ከጠጣ ወይም ከተመገበ ልጋጉ እቃውን ስለሚነካው እቃው ይነጀሳል።
3ኛ. የውሻ ልጋግ ያረፈበትን ነገር ሰባት ጊዜ ማጠብ ግዴታ ነው።
4ኛ. በአፈር መፈግፈግ ግዴታ ነው። ይኸውም በመጀመሪያ በአፈር ከፈገፈጉ በኋላ ሰባት ጊዜ በውሃ ማጠብ በላጭ ሲሆን፣ በውሃ ሰባት ጊዜ ካጠቡ በኋላ በአፈር መፈግፈግም ይቻላል። በአፈር መፈግፈግ የሚያስገኘውን ሳይንሳዊ ጥቅም በተመለከተ የተለያዩ ጥናቶች የሚጠቁሙት ነገር
እንዳለ ሆኖ፣ ዋናው ነገር ግን በአፈር ማጠብ የነቢዩ(ﷺ) ትእዛዝ በመሆኑ ብቻ የሚፈፀም
(ተዓቡዓይ) እርምጃ መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው።
5ኛ. ይህ ሐዲስ እንዲሁ ኢስላም ለንጽህና የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ያመለክታል።
6ኛ. የውሻ ልጋግ ነጃሳ ከመሆኑ አኳያ ውሻን ያለ ምክንያት በቤት ውስጥ ማስቀመጥ ክልክል ነው።
በመሆኑም በአሁኑ ሰአት በተለይም በውጭው ዓለምና ሙስሊም ባልሆኑ ማሕበረሰቦች ዘንድ ውሻ ልክ እንደ አንድ የቤተሰቡ አባል ከነዋሪዎች ጋር በሳሎን ቤት፣ ማእድ ቤት፣ መኝታ ቤት፣ አብሮ የሚኖርበት፣ አብሮ የሚመገብበት እና ከአልጋ ላይ የሚተኛበት ሁኔታ በእስልምና ፍፁም የማይፈቀድ ነገር ነው።
7ኛ. ሐዲሱ ውሻን ባጠቃላይ የሚመለከት ቢሆንም ለአደንና ለጥበቃ ተግባር የሚያገለግሉ ውሾች ግን ከሌሎቹ በተለየ መልኩ የሚታዩበት ሁኔታ መኖሩን ሊቃውንት ጽፈዋል። ሸሪዓዊ መረጃዎችም ይህንኑ ያመለክታሉ። ውሻን ማሳደግ የተፈቀደበት አግባብ በዝርዝር እስኪ እንመልከት ውሻን ማሳደግ የተፈቀደውም፡-
1ኛ. #ለአደን_ስራ!
ውሻን በማሰልጠን በኢስላም ለመብልነት የተፈቀዱ የእንሰሳት አይነቶችን አድኖ ቢይዝልን እንሰሳው የተፈቀደ(ሐላል) ይሆናል፡፡ ስለዚህ ውሻን ለአደን ተግባር መያዝ ይቻላል፡፡ ማስረጃውም ቀጥሎ የሚቀርበው የአላህ ቃልና የመልክተኛው ሐዲሥ ነው፡-
➊“ለነርሱ ምን እንደተፈቀደላቸው ይጠይቁሃል፤ በላቸው፦ ለናንተ መልካሞች ሁሉና እነዛ ከአዳኞች አሰልጣኞች ሆናችሁ ያስተማራችኋቸው (ያድኑት) ተፈቀደላችሁ፤ አላህ ካስተማራችሁ ዕውቀት ታስተምሩዋቸዋላችሁ፤ ለናንተም ከያዙላችሁ ነገር ብሉ በርሱም ላይ የአላህን ስም አውሱ አላህንም ፍሩ፤ አላህ ምርመራው ፈጣን ነውና።”
(ሱረቱል ማኢዳህ 5፡4)፡፡
✡በዚህ ትርጉም ውስጥ ‹‹ከአዳኞች›› ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱና ዋነኛው ውሻ ነው፡፡
በዚህ መሰረት ውሻን ለአደን ተግባር መጠቀም ይቻላል፡፡
✡ስለዚህ ጉዳይስ በሃዲስ ምን ተባለ?
➋ ☞ዐዲይ ኢብኑ አቢ ሓቲም (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ቢስሚላህ በማለት ለአደን (ያሰለጠንከውን) ውሻህን ብትልክና አድኖ ቢገድለው አንተም ከአደኑ ብላ፡፡ ውሻው ያደነውን መብላት ከጀመረ ግን አትብላ፡፡ እሱ ለራሱ ነው ያደነውና፡፡ ሌሎች የአላህ ስም ሳይወሳባቸው የተላኩ ውሾችን ከተቀላቀለና እነሱ አድነው የገደሉትን ካገኘህ አትብላ፡፡ የትኛው ውሻ እንደገደለው አታውቅምና…”
#ቡኻሪይ_5484፣_5081፡፡
✡በቁርኣኑም ሆነ በሐዲሡ መሰረት ለአደን የምንጠቀመው ውሻ ላይ ሁለት ነገር ማሟላት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ #ማሰልጠንና_ቢስሚላህ ብሎ መላክ፡፡
2ኛ. #ለጥበቃ.
✡ሌላው ውሻን ማሳደግ የሚቻልበት መንገድ ከጥበቃ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ ጥበቃ ሲባል ደግሞ፡-
1/ የጓሮ አዝመራን
2/ ለቤት እንሰሳዎች
3/ መኖሪያ ቤትን፡-
➊ ☞አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገሩት የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- “ለበግ/ፍየል እረኝነት ወይንም ለአደን ወይንም ለአዝመራ ጥበቃ እንጂ፡ (ከዛ ውጪ ላለ ነገር) ውሻን የያዘ ሰው በየቀኑ ከአጅሩ ላይ ይቀነስበታል” #ሙስሊም 4111፡፡
✡ለአደንና ለእረኝነት ውሻን ማሳደጉ የተፈቀደ ከሆነ ለቤት ጥበቃ ደግሞ ከዛም በበለጠ መልኩ የሚፈቀድ መሆኑን ቂያስ በማድረግ ኢማሙ
ነወዊይ ረሒመሁላህ (ሸርሑ ሶሒሕ ሙስሊም 10/340) ላይ ገልጸዋል፡፡
✡እንዲሁም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ይህን ሀሳብ ደግፈዋል።
(አል-ኢስላሙ ሱአሉን ወጀዋብ ቁ. 69777)፡፡
ከዚህ ውጪ ዝምብሎ ውሻን ማሳደግ አልተፈቀደም፡፡ ምእራባዊያን የኛ ምሣሌ አይደሉም!!!
#ክፍል7⃣
በክርስትናስ ውሻ የተጠላ/አፀያፊ አይደለምን!?ይቀጥላል..
.... ሼር በማድረግ ማህበረሰቡ ጋር በማድረስ ኢስላማዊ ግዴታዎን ይወጡ!
..........👇👇👇.....
@Loveyuolema