🔰 #የሀይማኖት_ንፅፅር
#ክፍል 1⃣7⃣
🤔 #ክርስቶስ_ማን_ነዉ?
ማስረጃ ቁጥር ➋
ወሳኝ ትምህርታዊ ጥያቄዎች
ወሳኝ ትምህርታዊ ጥያቄዎች!
ውድ አንባቢያን! ዛሬ የምናየው ኢየሱስ (የአላህ ሰላም በሱላይ ይሁንና) እንዳልተሰቀለ ከሚያረጋግጡልንና ብዙም ርቀን ሳንሄድ በቀላሉ የምንረዳው! እውነትን ላለመቀበል ካልሆነ በቀር ልክ #እንደ_ጠራራ_ፀሃይ ግልፅ ብሎ የሚታየን! ኢየሱስ ስለመሰቀሉ የሚናገሩ መረጃ አሉ ተብለው ስለቀረቡት ጥቅሶች እና መረጃ ተብለው በማህበረሰቡ ዘንድ #የሚታመኑ የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች ራሳቸው #እርስ_በርስ ስለመፋለሳቸው ነው የምናየው! #እውነት ኢየሱስ ተሰቅሏል ከተባለ! #ስለመሰቀሉ_የሚያወሩት_ጥቅሶች_ለምን
#እርስ_በርስ_ይጋጫሉ!? የሚጋጩና የሚቃረኑ ሃሳቦችንስ አምኖ መቀበል ተገቢ ነውን!? እስኪ ሶስቶቹን ብቻ በማንሳት እነዚህን ጥቅሶች እንያቸው!
➊ኛ.የማርቆስ ወንጌል (ም.15፡ቁ.24) ላይ
‹‹ሰቀሉትም ልብሱንም ማን ማን እንደሚወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተከፋፈሉ በሰቀሉትም ጊዜ ‹‹ #ሦስት ሰዓት ነበር››
☞ ዮሐንስ ወንጌል(ም.19፡ቁ.14)ላይ ደግሞ ‹‹የፋሲካ ዝግጅት ነበር ጊዜውም ወደ ‹‹ #ስድስት ሰዓት ነበር››በዚያን ጊዜ ጰላጦስ አይሁዳውያኑን ‹‹እነሆ ንጉሳችሁ›› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን አስወግደው ስቀለው እያሉ ጮሁ››
ልብ ይበሉ! እዚህ ጥቅስ ላይ ገና አልተሰቀለም!
✡ የኛ ጥያቄ፡- ኢየሱስ ስንት ሰዓት ነው የተሰቀለው
#3 ሰዓት ወይስ #6 ሰዓት!?
➋ኛ. በማርቆስ ወንጌል (ም.16፡ቁ.5) ላይ
‹‹ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናፀፈ #ጎልማሳ በቀኝ በኩል #ተቀምጦ_አዩና_ደነገጡ››
☞ በዮሃንስ ወንጌል (ም.20፡ቁ.12) ላይ ደግሞ
‹‹ #ሁለት_መላዕክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ስጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላኛውም በእግርጌ #ተቀምጠው_አየች››
✡ የኛ ጥያቄ፡- መቃብሩ የሄደችው አንድ ሴት ነበረች ወይስ ሌሎችም ነበሩ!? መቃብሩ ውስጥስ የነበረው ማነው!?‹‹ነጭ ልብስ የተጎናፀፈ ጎልማሳ ወይስ ሁለት መላዕክት!?
➌ኛ.ማርቆስ ወንጌል (ም.15፡ቁ.23) ላይ
‹‹ #ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት እርሱ ግን አልተቀበለም ሰቀሉትም ልብሱን ማን ማን እንደሚወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተከፋፈሉ››
☞ ማቴዎስ ወንጌል (ም.27፡ቁ.34) ላይ ደግሞ
‹‹ #በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም፡፡ ከሰቀሉትም በኃላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ››
✡ የኛ ጥያቄ፡-እንዲጠጣ ያቀረቡለት የወይን ጠጅ በከርቤ ወይስ በሐሞት የተቀላቀለ!?
✡ለአብነት ያህል እነዚህን ጥቅሶች ብቻ አቀረብን
እንጂ ሌሎች ብዙ የሚያወዛግቡ ጥቅሶች አሉ፡፡
****ከነዚህ ጥቅሶች በግልጽ እንደምንረዳው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልም ሆነ ከሞት መነሳት ተፅፈዋል የተባሉት መረጃዎች እርስ በርሳቸው እንደሚቃረኑ ነው፡፡ ስለ መሰቀሉና ሞቶ ስለመነሳቱ የተፃፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እውነት ከሆኑ ለምን እርስ በርስ ይጋጫሉ!? በመሰረቱ የተጋጩ ሀሳቦችን አምኖ መቀበል ልክ ነውን?
✡ኢስላም ግን አል-መሲሕ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በጠላቶቻቸው እጅ የመሰቀላቸውን ዶክትሪንም ሆነ የዶክትሪኑን መሠረት #በፍፁም_አይቀበልም፡፡ ይህ እምቢታ አላህ ቁርዓን ውስጥ ባለው ላይ
የተመረኮዘና የሌሎችን ኃጢአት ለማሰረዝ የመሰዋቱን ሁኔታ ከነጭራሹ በመቃወም ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
#የአደም_የመጀመሪያ_ኃጢአት ራሱ አዳም በፈፀመው ስህተት ተፀፅቶ ምህረት ከለመነ በኋላ የተሰረዘለት መሆኑን #ኢስላም_ያስተምረናል፡፡
ቁርዓን የኢየሱስን መሰቀልና መሞት ውድቅ አድርጓል፡፡ በአንፃሩም ወደ ሰማይ ማረጉን እንዲህ ሲል ይገልፅልናል፡-
★☞ ‹‹እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡ ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡››(ሱረቱ ኒሳእ 4፡157-158)››
✡ ኢስላም የኢየሱስን (ዒሳን) መሰቀል አይቀበልም፡፡ ጌታው አላህ ከስቅላት አድኖት ወደ ሰማይ አሳርጎታል፡፡ ኢየሱስን ከጠላቶቹ (ከከሃዲዎቹ) በላይ እንደሚያደርገውም ቃል እንደገባለት አላህ
ሱብሃነወተዓላ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡-
★☞ ‹‹አላህም ባለጊዜ (የሆነውን አስታውስ) ዒሳ ሆይ! እወስድሃለሁ ወደኔም አነሳሃለሁ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች (ተንኮል) አፀዳሃለሁ፡፡ እነዚያን አንተን
የተከተሉትንም ወገኖች እስከ እለተ ቂያማ (ትንሳኤ)
ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አደርጋለሁ፡፡ ከዚያም
መመለሻችሁ ወደኔ ነው፡፡ ትወዛገቡበት የነበረውን ነገር በመካከላችሁ ብይን እሰጣለሁ፡፡ እነዚያን የካዱትን ወገኖች በዚህችም በቀጣዩም ዓለም ብርቱ ቅጣትን እቀጣቸዋለሁ፡፡ (ከቅጣት የሚያድን) ረዳት አይኖራቸውም፡፡ ለነዚያ ላመኑትና መልካም ተግባራትን ለፈፀሙት (አላህ) ምንዳቸውን ይሰጣቸዋል፡፡ አላህ በዳዮችን አይወድም፡፡
( #ሙሃመድ_ሆይ!) ይህ የምናነብልህ (ታሪክ የምናወሳልህ መልዕክት) የጥበበኛው (መፅሃፍ) ታአምራትና መልዕክቶች አካል ነው፡፡
#ከአላህ_ዘንድ_ዒሳ_እንደ_አደም_አምሳያ_ነው፡፡
(አላህ አደምን) ከአፈር ፈጠረው፡፡ ሁን አለው ሆነ፡፡
(ሱረቱ አል-ዒምራን3፡55-59)
✡ እስካሁን ባሳለፍነው እንደተመለከትነው በኢየሱስ ላይ ክርስቲያኖች ያላቸው አቋም ይህ ብቻ አይደለም፡፡ አምላክ ነው፤ ከስላሴዎቹ አንዱ ነው፤›› የሚለው ይገኝበታል፡፡ #እናቱን_ቅድስት_ማሪያምን ‹‹ወላዲት አምላክ/የአምላክ እናት›› በማለት ያመልካሉ፡፡ ይሰግዱላታል፡፡ ይማፀኗታል፡፡
ታማልደናለች ወዘተ በማለት ‹‹አማልክት›› አድርገው ይዘዋታል #ኢየሱስ_ይህንን_ፈፅሞ_አላስተማረም፡፡ ‹‹አምልኩኝ፤እናቴንም ተገዙ፤ የአምላክ ልጅ ነኝ፤›› #የሚለው የርሱ አስተምህሮት አይደለም፡፡
ጌታችን አላህ (ክርስቲያኖች ከሚሉት ጥራት ይገባውና) ኢየሱስ (ዒሳ) ይህን አለማለቱን እያወቀ ነገ በእለተ ትንሳኤ ቀን እንዲህ ሲል (ዱኒያ ላይ ሲገዙት የነበሩት) ሰዎች ፊት ይጠይቀዋል፡-
★☞ ‹‹አላህም፡- ‹የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ሰዎችን፣ እኔንና እናቴን ከአላህ ውጪ አማልዕክት አድርጋችሁ ያዙኝ ብልሃልን?› በሚለው ጊዜ (የሚሆነውን አስታውስ)፡፡ (ዒሳም) ክብርና ልዕልና ላንተ ይሁን! ለኔ ልለው የማይገባኝን ነገር ማለቴ ፈፅሞ አግባብ አይደለም፡፡ ይህን ተናግሬ ከሆነ ታውቀዋለህ
በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ግን አንተ ዘንድ ያለውን አላውቅም፡፡ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም አዋቂ አንተ ብቻ ነህና ይላል፡፡ አንተ ሩቅ ሚስጥራትን አዋቂ ነህና ይላል፡፡ (ይላልም) #የነገርኳቸው ያዘዝከኝን ብቻ ነው #የኔም_የናንተም_ጌታ_የሆነውን አላህን ብቻ አምልኩ (ነው ያልኳቸው)፡፡ ከመካከላቸው በነበርኩበት ወቅት ስለነርሱ መስካሪ ነበርኩ፡፡ እንዳርግ ካረከኝ በኋላ ግን የነሱ ጠባቂና
ተቆጣጣሪ አንተው ነበርክ፡፡ አንተ በሁሉም ነገር ላይ መስካሪ ነህ፡፡ ይላልም ብትቀጣቸው ባሮችህ ናቸው፡፡ ብትምራቸውም አንተ ኃያልና ጥበበኛ ነህ፡፡
(ቁርዓን ሱረቱል ማኢዳህ5፡116-118)👇