፨ድንግል በስደትሽ፨
በወርሀ መስከረም በዓመቱ መግቢያ፣
እስኪ ትንሽ ልበል ስለ እመቤታችን ስደት በኢትዮጵያ።
የወራት መነሻ የአበቦች ማፍሪያ፣
መአዛሽ ያውዳል የለሽም አምሳያ፣
ለ 7ቱ አጽዋማት መንገድ ጠራጊ ነሽ፣
ሰው ሁሉ በፍቃድ ሁሌ የሚጾምሽ፣
በአበባዎች ዘመን ሰው ሁሉ ሲደሰት፣
ወላዲተ አምላክ ወጣች ወደ ስደት።
ህጻኑን ታቅፋ ከነዮሴፍ ጋራ፣
ስደትን ጀመረች አቋርጣ ተራራ፣
ይህ ሁሉ መከራ መች ለእሷ ይገባል፣
ለእኛ ለልጆችሽ ምሳሌ ሆኖናል።
ስደት ጀማሪዋ ወላዲተ አምላክ፣
ሁሌ የምትሰጠን አዲስ ህይወት ታሪክ፣
በዛ በግብፅ ሀገር ሀሩር በበዛበት፣
እርሃብና ጽሙ የአሸዋውም ግለት፣
ሁሉንም ታግሰሽ ካሳ ከፈልሽልን፣
አንች ተቀብለሽ ስደት መከመነሻ።
ያዳም ልጁ ተስፋ ከሞትም መነሻ፣
ድንግል እናታችን የገነት መውረሻ፣
የነገስታት ንጉሥ በእጅሽ ታቅፈሽ፣
ውሃ ጥሙን ሁሉ ኧረ እንደምን ቻልሽ፣
አንች መልካም እርግብ የትህትና እናት፣
በዛ በመከራ በስደትሽ ወራት፣
ዬሴፍ ሰሎሜ ከልጅሽ በስተቀር፣
ኧረ ማን ነበር የሚያጽናናሽ በፍቅር?
ኮቲባ በንቀት ልጅሽን ስጥለው፣
የትዕማር ክፉ ሃሳብ ልብሽን ሲያደማት፣
አምላክነቱን ገልጦ ምድር ሲወጣቸው፣
አይተናል ሰምተናል ሁሉ ይቻለዋል፣
ለበዛው ምህረቱ ክብር ይገባዋል፣
የሽፍቶቹን ኮቴ ከእሩቅ ስትሰሚ፣
ልጄን ሊገድሉት ነው ብለሽ ስትሰጊ፣
ይህን ሁሉ ሰቆቃ መራሩ ሀዘንሽ፣
መዳኛ ሆኖናል ለአስራት ልጆችሽ።
በስደትሽ ወራት ሀዘን በበዛበት፣
ሰሎሜና ዪሴፍ አገኙ በረከት፣
በጽጌ ማህሌት ካህናት ድያቆናቱ፣
ምዕመናን ምእመናት አዛውንት ወጣቱ፣
ንኢ ንኢ ብለው በፍቅር ሲጣሩ፣
የሁሉ እመቤት መጣች ከቤታቸው ለሁሉም ማህበሩ፣
ድንግል ባንቺ ስደት እንድንማር ጽናት፣
እኛንም አድኝን ከመከራ ጭንቀት።
የልጆችሽን ልመና ድንግል ትሰሚያለሽ፣
እሩህሩህ ነሽና ታማልጂናሽ።
ይህን ካልኩ ይብቃኝ ድንግል ለስደትሽ፣
መቼም አልጨረሰው ስዘረዝር ብውል።
የአማኑኤል እናት ክብር ይገባሻል፣ የአስራት ልጆች ሁሌም ይጠሩሻል፣
ከጭንቅ ከመከራ ሁሌ እንድታወጭን፣
ሰላምና ጤና ፍቅርንም አድይን፣
በሄድንበት ሁሉ ጠበቃ ሁኚልን።
ከዲ/ን ሃብተ ማርያም 2011ዓ.ም
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
በወርሀ መስከረም በዓመቱ መግቢያ፣
እስኪ ትንሽ ልበል ስለ እመቤታችን ስደት በኢትዮጵያ።
የወራት መነሻ የአበቦች ማፍሪያ፣
መአዛሽ ያውዳል የለሽም አምሳያ፣
ለ 7ቱ አጽዋማት መንገድ ጠራጊ ነሽ፣
ሰው ሁሉ በፍቃድ ሁሌ የሚጾምሽ፣
በአበባዎች ዘመን ሰው ሁሉ ሲደሰት፣
ወላዲተ አምላክ ወጣች ወደ ስደት።
ህጻኑን ታቅፋ ከነዮሴፍ ጋራ፣
ስደትን ጀመረች አቋርጣ ተራራ፣
ይህ ሁሉ መከራ መች ለእሷ ይገባል፣
ለእኛ ለልጆችሽ ምሳሌ ሆኖናል።
ስደት ጀማሪዋ ወላዲተ አምላክ፣
ሁሌ የምትሰጠን አዲስ ህይወት ታሪክ፣
በዛ በግብፅ ሀገር ሀሩር በበዛበት፣
እርሃብና ጽሙ የአሸዋውም ግለት፣
ሁሉንም ታግሰሽ ካሳ ከፈልሽልን፣
አንች ተቀብለሽ ስደት መከመነሻ።
ያዳም ልጁ ተስፋ ከሞትም መነሻ፣
ድንግል እናታችን የገነት መውረሻ፣
የነገስታት ንጉሥ በእጅሽ ታቅፈሽ፣
ውሃ ጥሙን ሁሉ ኧረ እንደምን ቻልሽ፣
አንች መልካም እርግብ የትህትና እናት፣
በዛ በመከራ በስደትሽ ወራት፣
ዬሴፍ ሰሎሜ ከልጅሽ በስተቀር፣
ኧረ ማን ነበር የሚያጽናናሽ በፍቅር?
ኮቲባ በንቀት ልጅሽን ስጥለው፣
የትዕማር ክፉ ሃሳብ ልብሽን ሲያደማት፣
አምላክነቱን ገልጦ ምድር ሲወጣቸው፣
አይተናል ሰምተናል ሁሉ ይቻለዋል፣
ለበዛው ምህረቱ ክብር ይገባዋል፣
የሽፍቶቹን ኮቴ ከእሩቅ ስትሰሚ፣
ልጄን ሊገድሉት ነው ብለሽ ስትሰጊ፣
ይህን ሁሉ ሰቆቃ መራሩ ሀዘንሽ፣
መዳኛ ሆኖናል ለአስራት ልጆችሽ።
በስደትሽ ወራት ሀዘን በበዛበት፣
ሰሎሜና ዪሴፍ አገኙ በረከት፣
በጽጌ ማህሌት ካህናት ድያቆናቱ፣
ምዕመናን ምእመናት አዛውንት ወጣቱ፣
ንኢ ንኢ ብለው በፍቅር ሲጣሩ፣
የሁሉ እመቤት መጣች ከቤታቸው ለሁሉም ማህበሩ፣
ድንግል ባንቺ ስደት እንድንማር ጽናት፣
እኛንም አድኝን ከመከራ ጭንቀት።
የልጆችሽን ልመና ድንግል ትሰሚያለሽ፣
እሩህሩህ ነሽና ታማልጂናሽ።
ይህን ካልኩ ይብቃኝ ድንግል ለስደትሽ፣
መቼም አልጨረሰው ስዘረዝር ብውል።
የአማኑኤል እናት ክብር ይገባሻል፣ የአስራት ልጆች ሁሌም ይጠሩሻል፣
ከጭንቅ ከመከራ ሁሌ እንድታወጭን፣
ሰላምና ጤና ፍቅርንም አድይን፣
በሄድንበት ሁሉ ጠበቃ ሁኚልን።
ከዲ/ን ሃብተ ማርያም 2011ዓ.ም
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✞@MENFESAWItsufoche✞
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤