ማስታወቂያ 📜 ስለ ኮርሱ ማብራሪያ 📜
👉 የትምህርቱ ዋና ዓላማ
➺ የግእዝ ቋንቋን ተምረው ለማያውቁ ከጅማሬው ማሳወቅ እና ቋንቋውን መደበኛ በሆነ መልኩ ለመማር የሚፈልጉትን አነሣሥቶ ጥንታዊ የሆነ ቋንቋዎችን ለዘመኑ ሰዎች በዘመናዊና በቀላል አቀራረብ ማስተማር ነው።
👉የትምህርቱ አሰጣጥ
➺ ኮርሱ መሠረታዊ የሆኑ ትምህርቶች የያዘ ሲሆን በ 4 ምዕራፎች ተከፋፍሎ ይሰጣል። የትምህርት ጊዜያት ከሰኞ እስከ ዓርብ ሲሆን ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ ትምህርቶች ይለጠፋሉ። ስለዚህም በሚመችዎት ሰዓት ላይ ገብተው መከታተል ይችላሉ።
➺ ትምህርቶች የሚሰጡባቸው መንገዶች በጽሑፍ ፣ በድምፅ እና በቀጥታ ቮይስ ቻት (Voice Chat) ሲሆን አጠቃላይ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ይሰጣል። በዚህም መሠረት በየዕለቱ ለጥቂት ደቂቃ ያክል (10'-15') ሰጥተው ትምህርቱን ያካሂዳሉ ማለት ነው።
➺ ውይይቶች፣ መልመጃዎች፣ የቤት ሥራዎች እንዲሁም የምዘና ፈተናዎች ይካሄዳሉ ። ትምህርቱን በአስፈላጊው ሁኔታ ላጠናቀቁ ተማሪዎችም የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት (የምስክር ወረቀት) ይሰጣል። በኮርሱም መጨረሻ ጥሩ ውጤት ላመጡት ሽልማት ይበረከታል።
መመዝገብ የምትፈልጉና ማንኛውንም አይነት ከታች ባለው አድራሻ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
+251914946589
@Asrategabriel