ዘወትር ምጽዋትን እንድታፈቅሯት የምለምናችሁደ ለምን ይመስላችኋል?
ለተቸገሩ ሰዎች መስጠት ማለት ስጦታችንን በሌላ በማንም ሳይኾን በራሱ በእግዚአብሔር እጅ ማስቀመጥ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ የሰጠነው እንደሚመለስልን ብቻ ሳይኾን መቶ ዕጥፍ ኾኖ እንደሚሰጠን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ላሳየነው ጥቂት ቸርነት የሚደረግልን ቸርነትም ታላቅ ነው፡፡
እግዚአብሔር የሰጠነውን አብዝቶ የሚመልስልንስ ለምንድን ነው? የምንሰጠው ስጦታ ጥንቱንም የሰጠን እርሱ እንደ ኾነ እየመሰከርን ስለ ኾነ ነው፡፡ በመኾኑም ወደንና ፈቅደን ይህን በተግባር ስንመሰክር፥ በተቀበለን እጁ የሰጠነውን ብቻ ሳይኾን ከሰጠነውም ጋር አብሮ መንግሥተ ሰማያትን ይሰጠናል፤ አክሊል ሽልማትን ያቀዳጀናል፤ ስፍር ቊጥር የሌለው በጎ በጎ በረከትም ያድለናል፡፡
እስኪ ንገሩኝ! እግዚአብሔር እየጠየቀን ያለው ከባድ ነገር ነውን? በፍጹም! እየጠየቀን ያለው በቤታችን ውስጥ ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር ለሌሎች እንድንሰጠው ነው፡፡ ይህን እንድናደርግ የሚሻውም የክብር አክሊል እንዲያቀዳጀን ምክንያት ሲፈልግብን እንጂ ለእነዚህ ችግረኞች የሚያስፈልጋቸውን ነገር መስጠት ተስኖት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ይህን እንድናደርግ የሚፈልገው ቃል የገባልንን ርስቱንና መንግሥቱን እንዲያወርሰን እጅግ ስለሚቸኩል ነው፡፡
ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ! እማልዳችኋለሁ እማፀናችሁማለሁ! እግዚአብሔር ጥቂት ምክንያት አግኝቶብን ሊሰጠን የሚወደውን እንዳናጣ በቤታችን ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር [ልብስ፣ ጫማ፣ ወዘተ] አውጥተን ለተቸገሩት ሰዎች እንስጣቸው፡፡ እግዚአብሔርም ያደረግናትን ጥቂቷን ምጽዋት በወዲያኛው ዓለም ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አምላክ አይደለም፡፡ በዚህም ዓለም በመስጠታችን ምክንያት የሚያገኘንን ነገር መፍራት አይገባንም፡፡ ቃለ እግዚአብሔር፡- “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ካለ በኋላ፥ ጨምሮም፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይላልና (መዝ.111፥9)፡፡
ኦ ምጽዋት! እንደ ምን ትደንቅ? እንደ ምንስ ትረቅ? ሰው ባልንጀራውን አፍቅሮ ለጥቂት ጊዜ ጥቂት ነገርን ይሰጣል፡፡ ይህን በማድረጉ ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኘው ፍቅር ግን ለዘለዓም ዓለም ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡
ተወዳጆች ሆይ! ዘወትር ምጽዋትን እንድታፈቅሯት የምለምናችሁ ለዚህ ነው፡፡ ኹልጊዜ ምጽዋትን እንድትወዷት የምማፀናችሁ ለተቸገሩ ሰዎች ጥቂት ቸርነትን አድርገን ከእግዚአብሔር ዘንድ መጠን ወሰን የሌለውን ቸርነት እንድንቀበል ነው፡፡ ደጋግሜ ለተቸገሩ ሰዎች ፍቅርን እናሳይ የምላችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደር የሌለውን ፍቅር እንድንቀበል ነው፡፡
ስለዚህ ያለንን ለድኾች እናካፍል፡፡ ያን ጊዜም “በተኑ፤ ለችግረኞችም ሰጡ፡፡ ጽድቃቸውም ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይባልልናል፡፡ እግዚአብሔር በክቡር ዳዊት አድሮ “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ብሎ ሲናገር መበተን ማለት ማጣት ማለት እንዳልኾነ እንድናውቅ እንድንረዳም ሽቶ ወድያውኑ፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ብሎ የሚነግረን ለዚህ ነውና፡፡ “ያላቸውን ለተቸገሩ ሰዎች የሚያካፍሉ ሰዎች ጽድቃቸው የዘለዓለም ዓለም ነው፤ አይጠፋባቸውም፡፡ እነርሱ አላፊና ጠፊ ነገር ይሰጣሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚቀበሉት ግን መቼም ቢኾን መች የማያልፍ፣ መቼም ቢኾን መች የማይጠፋ፣ መቼም ቢኾን መች የማያረጅ ኾኖ ነው” ብሎ ሲነግረን ነውና!!
ምንጭ፦
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎች ገጽ 116-118
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ