. #ገና_ወድሀለው . . .
ገና ወድሀለው . . .
እንደ ንጋት ፀሀይ ልብ እንደሚያሞቀው
እንደ ቀትር ጥላ ጉልበት እንደሚያድሰው
እንደ ምሽት ጀምበር ልክ እንደሚናፈቀው
ብዙ ይቀረኛል ገና ወድሀለው
ከሰማይ ሰማያት የሚወረወር
ያ' ደማቅ ኮከብ ብርሀኑ የሚያምር
ልክ እንደዛው ነው የኔና ያንተ ፍቅር፡፡
ገና ወድሀለው ገና አፈቅርሀለው ገና
ሰው እስኪገርመው አለም እስኪቀና
እናንተም ስሙኝ ልብ ይበል ልብ ያለው
ማንም ከሱ አይለየኝም ገና እወደዋለሁ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘