ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 22 በሱረቱ አል-ነጅም ላይ ሙሽሪኮች ከሙስሊሞች ጋር መስማማታቸውና ሱጁድ ማድረጋቸው
ነቢይ ከሆኑ በአምስተኛ አመታቸው ከሙስሊሞቹ ስደት ከሁለት ወር በኋላ በረመዳን ወር በጣም ብዛት ያላቸው ቁረይሾች በከዕባ ዙሪያ በተሰበሰቡበት ሰአት ነቢዩ (ﷺ)ወደ መስዲድ አል ሐረም (ከዕባ)ሄዱ።ከተሰበሰቡት ቁረይሾች ውስጥ ሹማምንቶችና ታላላቆቹም ነበሩበት። የነጅም ምዕራፍ (ሱረቱ አል ነጅም) ወርዶ ነበር።በመሃላቸው ቆሙና በድንገት ቁርአኑን ማንበብ ጀመሩ። እንደዚያ አይነት እጅግ በጣም ድንቅና ውብ ንግግር በፍፁም ሰምተውት አያውቁም ነበርና ተደናገጡ።ስሜታቸው በጣም ተነካ።ግራ ተጋብተውና ፀጥ ብለው መስማቱን ቀጠሉ። ማስጠንቀቂያዎችና ማስፈራሪያዎች ያሉበትን የሱራው መጨረሻ አካባቢ ደርሰው ሲያነቡ የአድማጮቹ ልቦች በጣም ደነገጡ።በመጨረሻም
ለአላህም ሰገዱ ተገዙትም።የሚለውን የሱራውን መደምደሚያ ካነበቡ በኋላ ነቢዩ (ﷺ) ሱጁድ ሲወርዱ ሁሉም አብረዋቸው ሱጁድ ወረዱ።ራሳቸውን መቆጣጠር አልቻሉም ነበር።
ቡኻሪ ከኢብን መስዑድ በዘገበልን ሐዲስ እንዲህ ይላል፦ነቢዩ (ﷺ) ሱረቱ አልነጅምን አነበቡ።ሱጁድም አደረጉ።እዚያ ካለው ሕዝብ ሱጁድ ሳያደርግ የቀረ ሰው አልነበረመረ።ከሰዎቹ ውስጥ አንድ ሰው ጠጠር ወይም አፈር በእፍኝ ወስዶ ወደፊቱ አነሳውና ፊቱን በማስነካት ይህ ይበቃኛል አለ።ከዚያ በኋላ በኩፍር ላይ መሞቱን አየሁ።ኝሱም ኡሙያ ቢን ኸሊፍ ነበር።በበድር ቀን ሞተ።
የስደተኞች (ሙሃጂሮች) ወደ መካ መመለስ
ይህ ወሬ ሐበሻ ደረሰ።ይሁን እንጂ የደረሰው ወሬ ከተጨባጩ ሁኔታ የተለየ ነበር።የደረሳቸው ወሬ ቁረይሾች ሰለሙ የሚል ነበር።ይህን ሲሰሙ በደስታ ወደ መካ ተመለሱ።መካ ለመግባት የተወሰነ ሰዓት ሲቀራቸው የነገሩን እውነታ ተረዱ።ከነሱ ውስጥ ከፊሉ ወደ ሐበሻ ተመለሱ።ከፊሉ ደግሞ በምስጢር ወይም ከቁረይሽ በሰው ከለላ ወደ መካ ገቡ።
ወደ ሐበሻ ሁለተኛው ስደት
ቁረይሾች በአንድ በኩል ሳያስቡበት ከሙስሊሞች ጋር ሱጁድ በማድረጋቸው በጣም ስለተፀፀቱ በሌላ በኩል ደግሞ ለስደተኞቹ ነጃሺ ጥሩ ጉርብትናና ሰላም በመስጠት በጣም ስለተቆጡ ሙስሊሞቹን ለመበቀል ሲሉ በመካ ውስጥ ባሉት ሙስሊሞች ላይ ቅጣቱንና ስቃዩን አበረቱባቸው።ይህንን አስከፊ ሁኔታ በማየት ነቢዩ(ﷺ) ለሁለተኛ ጊዜ አስሀቦቻቸው ወደ ሐበሻ እንድሰደዱ አመላከቱዋቸው።ሰማንያ ሁለት ወይም ሰማንያ ሶስት ወንዶችና አስራ ስምንት ሴቶች ተሰደዱ።ቁረይሾች የሙስሊሞችን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በንቃት ይከታተሉ ስለነበር ይህ የሁለተኛው ስደት ከአንደኛው በጣም አስቸጋሪ ነበር።ይሁን እንጂ ሙስሊሞቹም ከቁረይሾቹ የበለጠ ንቁና ጥበበኞች በሚወስዱት እርምጃዎችም በጣም የረቀቁ ስለነበሩ ቁረየረሾች በጥብቅ ቢከታተሉዋቸውም ወደ ሐበሻ አመለጡዋቸው።
ይቀጥላል..... ......
https://t.me/Menhaj_Asselefiya