🍁ሸህ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢቢ
→ክፍል-1
መጅሊስን ያቋቋሙት ሼህ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢቢ ልጃቸውን ደርግ ገድሎባቸዋል ። ግን
እሳቸው ከመንግስቱ ጎን ይቀመጣሉ ለምን ይሆን
ጋዜጠኛ Zekeriya
Mohammed
አላህ በጀነቱል ፊርደውስ ያኑራቸውና ታላቁ አሊም ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፣ በደርግ
ሥርዓት የቀይ ሽብር ዘመቻ ልጃቸው ተገድሎባቸዋል። የልጃቸውን አስከሬን ደግሞ
እግቢያቸው በር ላይ ነበር የጣሉላቸው። በዚህም ምክንያት ሐጅ ሳኒ ዕድሜ ልካቸውን
ግቢያቸው ሲገቡም ሆነ ሲወጡ በጠባቧ በር ነበር የሚጠቀሙት። የልጃቸው አስከሬን የተጣለበትን ቦታ በእግራቸውም ሆነ በመኪና አይሻገሩትም ነበር። ሐዘናቸው ቀላል አልነበረም።
ከዚህ በመነሳት የቅርብ ወዳጃቸው ሐጅ በሽር ዳውድ (አላህ የጀነት ያድርጋቸው) አንድ ቀን ለሐጅ ሙሐመድ ሳኒ፣ "ሐጂ፣ ለምንድነው ከልጅዎ ገዳይ (ከመንግስቱ ኃ/ማርያም) ጎን
የሚቀመጡት? … ሰው ምን ይልኋል?!" ሲሉ በግሳፄ መልክ ጠየቋቸው
የሐጅ ሙሐመድ ሳኒ መልስ
"በእኔ እዚያ መቀመጥ ሰበብ፣ አላህ ለኢትዮጵያ ሙስሊም መልካም ነገር ቢያመጣለት ብዬ እንጂ፣ ሌላ ምን እፈልግ ኖሯል?!" የሚል ነበር።
ይቀጥላል...