✨ ሰው ለሰው መድኃኒት ነው ✨
አበቃው 🤗
✍️ ተፃፈ በ 🇲 🇮 🇰 🇺
@Miku_Thoughts
ጊዜው ጥቅምት 17, 2017 ዓ.ም ዕለተ እሁድ ነው በግምት ከምሽቱ 6:30 አካባቢ ይሆናል ፤ ሁሉም የዶርም ጓደኞቼ ተኝተዋል እኔ ግን የማምሸት ልምድ ስላለኝ የምሰራቸውን ስራዎች ከጨረስኩ በኃላ ማረፊያዬ ወደሆነው አልጋዬ ላይ ተቀምጬ ብዙም የማልጠቀመውን ከ social media ውስጥ አንዱ የሆነውን 𝐈𝐧𝐬𝐭𝐚𝐠𝐫𝐚𝐦 ከፍቼ ማየት ጀመርኩ ፤ ገና ከመክፈቴ ብዙም ሳይቆይ " ስም ሳትጠቅሱ ለፈለጋችሁት ሰው መልዕክት ፃፉ " የሚል አንድ 𝐏𝐨𝐬𝐭 ተመለከትኩ እኔም እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የፈረደበትን comment ለማንበብ ገባው { አደራ የሰው ሚስጥር ለምን ታነባለህ እንዳትሉኝ😅 }.... የተፃፉትን commentኦች ማንበብ ጀመርኩ የተፃፉት commentኦችእንዲህ አይነት ነበሩ
አንዳንዱ ፍቅሩን መውደዱን ሲገልፅ ፣ ሌላው ደግሞ ናፍቆቱን ይገልፃል ፣ አንዱ ደግሞ ፀፀቱን ሲፅፍ ሌላው ደግሞ በፍቅር መሰበሩን እና መጎዳቱን ይፅፋል ፣ ሌላኛው ሲቀልድ አንደኛው ደግሞ ብሬን መልስልኝ ይላል(የዚህስ አያምጣው ነው😁)፣ አንዳንዱ ይቅርታን ሲጠይቅ ሌላኛው ደግሞ ትልቅ ጥፋት ቢሆንም ይቅር ማለቱን ይፅፋል፣ አንዳንዱ ደስታው ሲገልፅ ሌላኛው ደግሞ ሀዘኑን እና መከፋቱን ይገልፃል። ይህንን ሁሉ እያነበብኩ ሳለው የገረመኝ እና ያሳዘነኝ ነገር ከተፃፉት commentኦች ውስጥ ከ90% በላይ የሚሆነው ብሶቱን ፣ ጉዳቱን እና ሀዘኑን ነው የፃፈው።
ይሁን ብዬ የሁሉንም Comment ማነበቤን ቀጠልኩ ፤ ነገር ግን በመሃል አንድ ማለፍ ያለቻልኩት አንዲት እህት የፃፈችውን ፅሁፍ ሳነብ ነበር ፤ ፅሁፉንም ካነበብኩበት ጊዜ በኃላም ለረጅም ደቂቃዎች ያህል በሃሳብ አለም ተውጬ ከራሴ ጋር ስነጋገር ነበር የከረምኩት🤔 .... ፅሁፉም " ደናነሽ ብላችሁ በደንብ አልጠየቃችሁኝም😢💔 " የሚል ነበር ። በሃሳብ አለም ውስጥ ጉዞን በጀመርኩበት ጊዜ ፅሁፉን ለመረዳት እና የፀሀፊዋን ሃሳብ ለማወቅ የፈጁብኝ ጊዜያት ጥቂት secondኦች ብቻ ነበሩ ያው ታሞ የሚያውቅ ህመምን ይረዳል አንደሚባለው ሁሉን ነገር ለመረዳት አልተቸገርኩም ነበር።
"ደናነሽ ብላችሁ በደንብ አልጠየቃችሁኝም😢💔 "
ይህንን ሃሳብ ለማንሳት የወደድኩበትን ምክንያት በመግለፅ ፅሁፌን ላጠናቅ።
ሃሳቤን በጥያቄ ልጀምር
እስኪ ስንቶቻችን ነን በዙሪያችን ካሉ ወዳጆቻችን ጋር አብሮ ጊዜን ከማሳለፍ በላይ ያሉበት ሁኔታ የምናውቀው?
ስንቶቻችን ነን ለወንድም እህታችን ፣ ለጓደኛ ዘመዳችን ጊዜን ሰተን የልባቸውን እንዲያወሩን ዕድል የምንሰጠው?
እስኪ ቆም ብለን እናስበው ስንቶቻችን ነን እንዲህ እያደረግን ያለነው?
ይቺ እህታችን "ደናነሽ ብላችሁ በደንብ አልጠየቃችሁኝም😢💔 "ያለችው የእውነቷን ነው።
ብዙ በዙሪያዋ ያሉ ሰዎች ከእሷ ጋር ጊዜን ያሳልፋሉ እንጂ ቀርቦ የሚያዋያት የልቧን የምትነግረው ሰው አላገኘችም። እርዳታን ፍለጋ ፣ የሚሰማትን ፍለጋ አይኗን ስታንከራት ብትውልም አንድም ሰው ስላጣች ነው " ደናነሽ ብላችሁ በደንብ አልጠየቃችሁኝም😢💔 " ብላ ለሁሉም መልዕክትን ያስቀመጠችው።
ስለዚህ ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው በዙሪያችን ያሉ ወዳጆቻችን ምን አይነት የህይወት መንገድ ላይ እንዳሉ ስለማናውቅ ደናነህ ደናነሽ ብለን በደንብ እንጠይቅ!!
ምክንያቱም ሁላችንም ሰው ያስፈልገናል ሰው ለሰው መድኃኒት ነው ፤ ከዛም አልፎ ለወዳጆቻችን ደግሞ አለሁልህ አለሁልሽ ብለን ከጎናቸው ልንሆን ይገባል😊
ከዛም በስተመጨረሻ ከነበርኩበት የሀሳብ አለም ነቅቼ ሰዓቱን ሳየው 7:00 አካባቢ ነበር ድካም ተጫጭኖኝ ስለነበር ስልኬን አስቀምጬ ልክ እንደ የዶርም ጓደኞቼ የእንቅልፍን አለም ተቀላቀልኩ።
አበቃው 🤗
✍️ ተፃፈ በ 🇲 🇮 🇰 🇺
@Miku_Thoughts