አምልኮ እና ጭፈራ የተለያዩ ናቸው፡፡
በዘፈን የሚጨፍረው ወንጀል መሆኑን አውቆ ተው ሲሉት ዱዓ አድርጉልኝ አላህ እንዲያላቅቀኝ ሲል፣ በተገላቢጦሹ በሰለዋት ስም ሰርግ ላይ፣ ሃድራ ብለው የሚጠሩት ላይ፣ ሸውቅ ብለው የሚጠሩት ላይ፤ መውሊድ ብለው የሚጠሩት ላይ፤ የመልክተኛው ውዴታ ብለው የሚጠሩት ላይ የሚጨፍሩት ሰዎች ተዉ አላህን ፍሩ ሰለዋት ኢባዳ ነው፣ ኢባዳ (አምልኮ ደግሞ) በጭፈራ አይከናወንም ስትለው አደለም ዱዓ አድርግልኝ ሊልህ ቀርቶ ሸይጧን የሚሰራውን ጥፋት አሳምሮለት ላንተ ስም ያወጣልሃል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
ከሚያወጡልህ ስም መሃል
- የነብዩ ሙሃባ የሌላቸው፣
- ወሃቢ፣
- እና የመሳሰለውን
‹‹ቢድዓ ኢብሊስ ዘንድ ከወንጀል በላይ ተወዳጅ ናት›› ይሉናል የቢድዓን ተንኮል የሚያውቁት ሰለፎቻችን፡፡
ግን ወንድም እና እህቶቼ ሆይ! ስም ማውጣቱ ይቅርና እስቲ የሚከተለውን ልብ በል፡፡
1) ቁርዓን መቅራት፣ ዱዓ ማድረግ አምልኮ ናቸው ወይንስ አይደሉም?
መልስህም አዎን ወደ አላህ የምንቃረብበት ነው ይሆናል፡፡
2) ታድያ የአላህን ቃል ቁርዓን ስትቀራ አንድም ቀን ጨፍረህ ታውቃለህን? ዱዓ ስታደርግስ ጨፍረህ ታውቃለህን?
መልስህም አረ በፍፁም ይሆናል፡፡
3) ታድያ ለምን ይሆን አላህን ውዱ ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ላይ ሰላትና ሰላም እንዲያወርድ ስትለምን የምትጨፍረው????????????
ሰለዋትስ አምልኮ (ኢባዳ) አይደለምን?
መልስህ እንዲያውም ከታላላቅ ኢባዳዎች መሃል ነው ይሆናል፡፡
አንተ የአላህ ባርያ ሆይ! በአላህ ስም አላህን እንድትፈራ ልጠይቅህ እና ሸይጧን አይጫወትብህ ሰሃባዎች (ከማንም በላይ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወዳጆች) የማያውቁትን ሰለዋትን አስታኮ ማጨብጨብ፤ ማፏጨት እና መጨፈር ተወው ይቅርብህ፤ ነገ አላህ ፊት ማስረጃ ብትጠየቅ መልስ አይኖህም እና፡፡
ሱና ከበቂያችን በላይ ነው፡፡
ከሳሪዎች እነማን እንደሆኑ ልንገርህን/ሽን????
አላህ እንዲህ ይላል
قُلْ هَلْ نُنَبِّئُكُم بِٱلْأَخْسَرِينَ أَعْمَٰلًا
«በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን?» በላቸው፡፡
ٱلَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا
እነዚያ እነሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው፡፡
ስለዚህ ሃቅ ለእኛ የመሰለን ሳይሆን ሸሪዓ ያዘዘበት፤ መለኮታዊ ራዕይ የወረደበት ነው፡፡ አላህን እንፍራ፣ በተለይ አሁን በየሰርግ ቤቱ በሰለዋት የሚጨፍሩ ሰዎች አላህን ፍሩ፣ ይህን መጥፎ መንገድ በማስተዋወቃችሁ፣ ሱናን በማጠልሸታችሁ ወደ አላህ በተውበት ካልተመለሳችሁ አደጋው ከባድ ነው፡፡
ሰርግ ቤት፤ መውሊድ፤ ሀድራ የሚባለው ላይ የሚሰራው ስራ ሸር ለመሆኑ ምንም እነሱ ጥሩ አስበን ነው (የነቢ ውዴታ ይዞን ነው) ቢሉም ወንድ እና ሴት መደባለቃቸው የሸር ተግባር ለመሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡
አላህን እንፍራ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው፣ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts