አላህ በሰጠን ንፁህ አእምሮ ስናየው አንቀፁ በግልፅ እንዳስቀመጠው፤ ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ለማግኘት፤ አላህ እንደመስፈርት ያስቀመጠው ‹‹በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያምልኩኝ ይገዙኝ›› ይላል አላህ፡፡
ይሄ ከፀሃይ በላይ ግልፅ የሆነ አንቀፅ እስቲ የአገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ እንድንፈትሽ ያድርገን፡፡ ኢትዬጵያ ውስጥ ስንት ቀብሮች ይመለካሉ፤ መንዙማ በሚል ስም ከአላህ ውጭ ስንቶች የአላህ መብት ይሰጣቸዋል፤ ከአላህ ውጭ ያለ ይመለካል፤ ይህ ሁሉ እያለ አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ ወደ አላህ መንገድ እንጣራለን የሚሉም የነብያትን ፈለግ ተከትለው ተውሂድን ማስተማር ሲገባቸው፤ አይደለም በተውሂድ ሊጀምሩ፤ የዳእዋቸው መጨረሻም አላደረጉትም፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ይህ ሁሉ ሽርክ እያለ ‹‹አንድ ነን›› የሚባለው ከባድ የሆነ ሰዎችን ባሉበት ጥመት ላይ የመተው ጭካኔ ከባዱ በደል ነው፡፡
አንዳንዶች እንዚህን ሁሉ ሽርኮች ጠንቅቀው እያዩ እና እያወቁ ተውሂድ እና ሱና ካልተስተካከሉ ምንም ፍሬ የማያፈሩ አርስቶችን ሰዉን ይሰብኩታል፡፡ ተውሂድ እና ሱና ካልተስተካከለ ምንም አይነት ስራ በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ይሁን፤ ፆምም ይሁን፤ ስግደትም ይሁን፤ ምፅዋትም ይሁን፤ ሃጅም ይሁን ሌላም ሌላም ዋጋ የላቸውም፡፡
ሁለቱ የስራ መስፈርቶች ለአላህ ብሎ መስራት እና የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ገጥሞ መገኘት ነው፡፡
አላህን በብቸኝነት ሳያመልኩ፤ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፈለግ ሳይከተሉ የሰሩት ስራ ውድቅ ነው፡፡ ስራም አይባልም፡፡ ሽርክም እያለ ፤የሃይማኖት መመቻቸት፤ በሰላም ከፍርሃት ተጠብቆ መኖር፤ የምድር ምትክ መሆን፤ በጠላት ተከብሮ እና ተፈርቶ መኖር ፈፅሞ አይታሰብም፡፡
ሰዎች እንዴት ያስባሉ የአላህን መብት ሳያሟሉ ፍጡራን ለነሱ ፍትሃዊ እንዲሆኑላቸው፡፡ አላህን የፈራ ሁሉም ይፈራዋል፡፡ አላህን ያመፀ፤ ሁሉንም ይፈራል፡፡
ገርሞ የሚገርመው ደግሞ አንድነት በታታኝ ስለሆነው ስለ ሽርክ እና ቢድአ አስከፊነት ትምህርት ሲሰጥ ፌስቡክ እና ሌሎች ሚድያዎች ላይ ‹‹አትከፋፍሉን፤ አንድ ነን›› የሚባለው ከኢስላም አስተምህሮት ጋር በፍፁም የማይሄደው የተሳሳተ አካሄድ ነው፡፡ አላህ አንድ ሁኑ ሲል በእምነት ገመድ እንጂ ሽርክ እና ቢድዐን ይዛችሁ አላለም፡፡ ወይ ከምንም ነገር በፊት ነብያት እንዳስቀደሙት ተውሂድን አስቀድሞ ለህዝባችን ማድረስ፤ አለበለዚያ ይህንን ማድረግ ያልቻለ፤ ሰዎች ሲያስተምሩ እንቅፋት አለመሆን፤ እና ለነሱም መጥፎ ስም አለመለጠፍ፡፡
ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ ‹‹የዚህ ህዝብ መጨረሻው የሚስተካከለው፤ የመጀመሪያውን (ህዝብ) በተስተካከለበት መንገድ ብቻ ነው››፡፡ እሱም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቅድሚያ ለተውሂድ በመስጠታቸው ነው፡፡
አላህ እውነተኛ አንድነት ይስጠን፡፡ እሱ እንዳለው በተውሂድ ላይ ተሳስረን አንድ የምንሆን ያድርገን፡፡ የአላህ የእምነት ገመድ ለሽርክ ቦታ የላትም፡፡
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ በአበል ቃሲም ላይ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts