መውሊድን ማን አዘዘበት?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይወሂ ወሰለም) “የእኛ (የአላህ እና የመልክተኛው) ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ውድቅ ነው፡፡ (ተቀባይነት የለውም)” ብለዋል፡፡
ይህ ሀዲስ የሚከተሉትን ነጥቦች ይጠቁማል
1) በዚህ ሸሪዓ ላይ ደንጋጊዎቹ አላህ እና ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ናቸው፡፡ ለምሳሌ አላህ ሰላት፣ ዘካን፣ ፆምን… ደነገገ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ዘካተል ፊጥርን እና ሌሎችን ህግጋት ደነገጉ፡፡ መልክተኛውን መታዘዝ አላህን እንደመታዘዝ ነው፡፡ አላህም አዘዘ፣ ነብዩም አዘዙ ከእኛ የሚጠበቀው ትእዛዙን መፈፀም ነው፡፡
2) ሀዲሱ በግልፅ እንደሚጠቁመው እኛ ከመሬት ተነስተን ሰላትንም ይሁን ማንኛውን አምልኮ ልንደነገግ አንችልም፡፡ አላህ እና መልክተኛው ካዘዙን በኋላ ነው፣ እነሱ ባዘዙን መንገድ እና ስርዓት መፈፀም ያለብን፡፡ ለምሳሌ ፈጅርን እውነተኛው ጎህ ከመቅደዱ በፊት 2 ረከዓ የሰገድነው ነብዩ (ሰለላሁ አለይወሂ ወሰለም) በዛ ሰዓት እንደሚሰገድ እና በዛ ወቅት መስገድ እንዳለብን ስላዘዙን ነው፡፡ ከዛ ውጭ እኛ ከመሬት ተነስተን የውሸተኛው ጎህ ላይ ብንሰግደው ስራችን ውድቅ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ያልታዘዝነውን ስለሰራን፡፡ ስራው ስራ ተብሎም አይወሰድም፡፡
ልክ እንደዚሁ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አሹራን ቀን ሲፆሙ አይተን እኛም ፆምን፡፡ በሳምንት አንድ ጊዜ የምትመጣውን ሰኞ ሲፆሙ አይተን እኛም ሰኞ እና ሀሙስን ፆምን፡፡
ታድያ መውሊድ አክባሪዎቹ የአላህ ወይንም የነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትእዛዝ የሌለበትን መውሊድ አክበረው ወደ አላህ ለመቃረብ ነው ወይንስ የአላህን ቁጣ ለማትረፍ ደፋ ቀና የሚሉት?
ሰሃባዎች፣ ታቢኢኖች፣ አትባኡ ታቢኢን፣ 4ቱ አኢማዎች፣ የሃዲስ ዘጋቢዎች አላህን ይፈሩ፣ ነብዩን በጣም ይወዱ ነበር፡፡ ነገር ግን አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙበትን “መውሊድ (ልደት ማክበር)” የሚባል ፈጠራ አልሰሩትም፡፡
መውሊድ ማክበር መልካም ቢሆን ኖሮ እነዚህ ምርጥ ትውልዶች ከእኛ ቀድመው ይሰሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነውና እነሱ ከዚህ እርጉም ተግባር ተቆጠቡ፡፡
አላህ ሰሃባዎች በቆሙበት መንገድ ላይ ከሚቆሙት ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts