የኮሮና ቫይረስ መልካም ገፅታ?
አላህ መቼም ሊረሳ የማይገባ፣ ሁሌም በደስታም በችግርም በብቸኝነት ሊመለክ የሚገባው አምላክ ነው፡፡ አላህ ካዘነላቸው ውጭ አብዛኛው ሰው ሞትን ረስቶ፣ አላህንም ረስቶ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት መከራዎች ሲመጡ የሰው ልጅ ቢያንስ ይህን መከራ ከአላህ ውጭ የሚያነሳ አለመኖሩን አውቆ ወደ ፈጣሪው መለስ ማለቱ ታላቅ ፀጋ ነው፡፡ አላህን በሰላሙም ጊዜ እናምልከው በችግር ጊዜ ይደርስልናልና፡፡
አላህ ከሚታመፅበት ምቾት፣ ጤና፣ ሃብት ይልቅ አላህ የሚታወስበት መከራ ይበልጥ መልካም ነው፡፡ ከኮሮና በፊት ዝንጉነት ላይ ለነበሩት ሁሉ ኮሮና መጥቶ አላህን ካስታወሳቸው እና ወደ እሱ እንዲመለሱ ካደረጋቸው ከዚህ በላይ ምን መልካም ነገር አለ፡፡
ስለዚህ ኮሮናን አደገኝነቱን ብቻ ሳይሆነ ታላቅ የሰው ልጆች ማንቂያ መሆኑን እና ታላቅ ማስታወሻ እንደሆነ አንዘንጋ፡፡
የአእምሮ ባለቤቶች ከእያንዳንዱ ክስተት ትልቅ ትምህርት ይማራሉ፡፡ አላህን በመከራም፣ በሰላሙም ጊዜ፣ እስከለተ ሞታቸው በብቸኝነት ከሚያመልኩት ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts