ሴቶች ባላደረግነው አስተዋጽኦ የግጭት ተጎጂ በመሆናችን ድምፃችን የበለጠ እንዲሰማ ማድረግ አለብን-ክብርት መዓዛ አሸናፊ
ሴቶች ባላደረግነው አስተዋጽኦ የግጭት ተጎጂ በመሆናችን ድምፃችን የበለጠ እንዲሰማ ማድረግ አለብን ሲሉ የቀድሞዋ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክብርት መዓዛ አሸናፊ ተናገሩ።
ክብርት መዓዛ ይህንን ያሉት ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ውስጥ የሴቶችን ተገቢ ውክልና ለማረጋገጥ እንዲቻል ለበጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ቁልፍ ንግግር ላይ ነው።
ለዘላቂ ሰላም ትኩረት ሰጥተን መሥራት ይገባናል፤ በሀገር ጉዳይ አስተያየት መስጠት የጋራ ጉዳይ ስለሆነ እኛ ሴቶች ያገባናል በማለት መንቀሳቀስ አለብን ያሉት ክብርት መዓዛ፣ እንደ ሀገር ከልዩነታችን ይልቅ አብሮነታችንና የጋራ ጉዳያችን ስለሚበዛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በማለት ገልጸዋል።
አያይዘውም የሴቶች ተሳትፎ ከሀገራዊ ምክክሩ ባሻገር በሽግግር ፍትሕ ተጠቃሚነትም ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሠራ አሳስበዋል።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ የጥምረቱ ጽ/ቤት የሆነችው ትምራን ሥራ አስኪያጅ ኢየሩሳሌም ሶሎሞን በእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክታቸው፣ ጥምረቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መቋቋሙን ተከትሎ ትርጉም ያለው የሴቶች ተሳትፎ እንዲኖር ለማስቻል ከሁለት ዓመታት በፊት መቋቋሙን ጠቁመዋል።
ምሥረታውን ተከትሎ ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት በኮሚሽኑ ውስጥ ሴት ኮሚሽነሮች እንዲወከሉ ማድረጉን፣ በምክክር ትግበራ ሂደት 30 በመቶ የሴቶች ተሳትፎ እንዲኖር ማስቻሉንና ተደራሽ ለመሆን ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ ሴቶች የአሠልጣኞች ሥልጠና በመስጠት እና ማሠልጠኛ ሰነዶችን በተለያዩ ቋንቋዎች በማዘጋጀት ለሴቶች ብቻ የተለዩ በርካታ የውይይት መድረኮች ማካሄዱን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዋና ዳይሬክተር እና የጥምረቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሳባ ገ/መድኅን በበኩላቸው፣ በሴቶች የምክክር ሂደት ሴቶች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች ለረጅም ጊዜ አብረው በመቆየት የተሳካ ሥራ መሥራታቸውን ጠቅሰው፣ ጥምረቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ ያከናወናቸውንና በቀጣይ ሊሠሩ የታቀዱ ተግባራትን ዘርዝረዋል።
በመድረኩ ላይ በተለያዩ የሞያ መስኮች ተሰማርተው ለሴቶች እኩልነት እና ተጠቃሚነት በጎ ተፅዕኖ መፍጠር የቻሉ ሴቶች ተገኝተው ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚቀርቡ አጀንዳዎችን አርቅቀዋል። #TIMRAN@5