ብቃትና ጥበብን የተካነው ሌላ ዘመናዊ ትግል ላይ ነው
አባ መላ የፈተና መአት ያልረታው ፤ ለካሃዲዎች ጫጫታ የማይደነብር ፤ አስቦና አስልቶ የሚጓዝ ፤ ብስለትና ትዕግስት የማይለየው ፤ ብቃትና ጥበብን የተካነ፤ አለቀለት ሲባል የሚታደስና የሚጎመራ የታላላቅ ሃገራትን ታሪክ ፈትሹ ከውድቀት ተነስተው ፈተናና ችግርን ተቋቁመው ለላቀ ውጤትና ቁመና የበቁት ሰውዬውን በመሰሉ መሪዎች ነው። አንተ ግን ይሄንን ሉጋም አልባ ቦሃቃህን ቁጭ ብለህ ክፈት። ትልቁ እውነታ መንግስትን መቃወም መብት ነው። ትልቁ መንግስት ሊኮራበት የሚገባውም የተለዩ ድምፆችን እንዲስተናገዱ መፍቀዱ ነው። ታዲያ በመቃወም ስም ለሽብርና ለሽፍታ መዘመር ግን ወንጀልም ነው። መሪውን መጥላት መብት ነው። እሱን በመጥላት ስም ግን ሀገር መጥላትም ሆነ ለመጣል መሞከር ነውርም ወንጀልም ነው። ወዳጄ ሰውየው ውጊያው ከድህነትና ኋላቀርነት ጋር ነው። አንተ ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ እንደልማድህ ድንቁርናህን በአደባባይ ፎክረው። እሱ ሌላ ዘመናዊ ትግል ላይ ነው፡፡ እግሩን ሲራመድበት ነው ያየነው። አንተ ግን እግሩ ወጣ አለ ብለህ መሮጫ እግርህን ቆመህበት ትጠብቀዋለህ? ያውም በግዙፉ የመሮጫ አደባባይ። የሮጥክ መስሎህ የቆመው ደራርቦህ እያለፈ ነው።
ብልህ እንዲህ ነው። ውጊያው በአደባባይ ከሚታየው ድንቁርናችንና የድንቁርና ፊታውራሪዎች ጋር ነው። እነሱን ሳይሆን ድንቁርናውን እናሸንፍ። እሱን ካላሸነፍነው እንዲህ ቀር እንደሆንን መቅረታችን ነው። ጅላጅሌ ባንተ አሮጌውና የቆሸሸው ሽቀላህ ልታማልለን ትከጅላለህ። ከሰውዬው ጋር ጠብ የገጠመ ሁሉ ስሙን ባዩ ቁጥር ያቃዣቸዋል። ኳስ በመሬት ባትችሉም መሬት ላይ የቆሙትን ሰዎች ግን በፀኑበት ተዋቸው። ከሰውዬው ላይ ውረዱ። እናንት ጭፍኖች ከሰውዬው አናት ላይ ምን ትሰራላችሁ? እኛ ከእልህና ቂመኝነት ጋር በፍቅር ያልወደቅን፣ ከስሜታችንም ስሜታዊነትም በላይ ለመሆን የምንጥር የዚህ ትውልድ አባሎች ነን። የመደመር ትውልድ አካል። ችግሩ ... የራበው ሁሉ፣ መብላት የሚፈልገው አንድ ዐብይ አህመድን መሆኑ ነው።
ጎንደር ፋሲለደስ