Репост из: Minber Tube
" በአስቸኳይ መስጂዶችን ማፍረስ አቁሙ ፤ የፈረሱትንም በፍጥነት መልሳችሁ አሰሩ ፤ ሕዝበ ሙስሊሙንም በይፋ ይቅርታ ጠይቁ " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲሱ "በሸገር ከተማ " መስጂዶች እየፈረሱ መሆኑን በመግለጽ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ።
ምክር ቤቱ ለኦሮምያው ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፃፈው ደብዳቤ ነው ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፈው።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤው ፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እየፈረሱ ያሉ መስጂዶች በአስቸኳይ እንዲያስቆም ብሏል።
ከዚህ ባለፈም ፤ የፈረሱ መስጂዶች በሸገር ከተማ አስተዳደር በፍጥነት እንዲሰሩና ሕዝበ ሙስሊሙን አስተዳደሩ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል።
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ፥ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በተፃፈው ደብዳቤ :-
1. በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉንዴሳ ወረዳ ልዩ ስፍራ ቀርሳ በቀን 14/07/15
2. በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ መጉላ ቶውፊቅ መስጂድ 19/08/15
3. በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አን ኢ ሳይት ሰላም መስጂድ በቀን 24/08/25
4. በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ በቀን 25/08/15 መፍረሳቸውና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ መሆኑን አሳውቋል።