የትዝታ ወልዴ ግጥሞች


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


የምወዳችሁ ይሄ ''የትዝታ ወልዴ ግጥሞች channel ነዉ''
ሀሳብ፣ አስተያት እና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ
@TIZITA21
Tiktok 👇
https://www.tiktok.com/@tizu422?_t=8sNmoeHUwqA&_r=1
youTube👇
https://www.youtube.com/channel/UC_EVyfbdSLjfKkMWZ4XGxeQ
Instagram
https://www.instagram.com/p/CZRrvITIgLR/?

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций






ዛሬ 11 ሰአት ላይ በአፍሪ ቴስት


እንኳን አደረሰን

2k 0 0 10 23





እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ በዓል የሰላም እና የፍቅር ይሁንላችሁ መልካም በዓል

@Tizitawolde_poems


Репост из: የትዝታ ወልዴ ግጥሞች
መልካም ልደት

አንዳንዴ ህይወቴን ባንተ ጫማ መሀል ከትቼ ሳረገዉ
ወይ አይጠብ አይሰፋኝ
ወይ በቅቶ አያረካኝ

እሱም እዚያ ማዶ
የኔም ልብ ሰርዶ
ያንተም ቅዝም ወዲያ
እንደተላለፍን ላንገናኝ🙈 ኤ.......ዲ........ያ

እንዲሁ ግርም አለኝ
አጃ....ኢብ ነዉ አቦ
አምላክን የሚያህል ከግዝፈቱ ጠቦ

ባጭር ቁመትና በሚጢጢ ደረት
ከማህፀን ወጥቶ ሲወለድ በበረት

አጃ.....ኢብ

ባለስልጣን ሳለ እንደ ሎሌ ወርዶ
በዳይን ለማዳን ዳኛዉ አገርድዶ

አጃ.....ኢብ ነዉ አቦ..........

የምድርስ ድፍረቷ እንደምን ቻለችህ
ምን ቃል ብትነግራት ነዉ?.........
ጌታዋን አምላኳን በበረት ወስና ፀንታ ያቆየችህ

እንደምን ብትወደን
እንዴት ብታፈቅረን
እንዴት ብታከብረን
አረ እንደምን ብለህ ታናሽነት መረጥክ
አንድ የምትለዉን ልጅህንም ሰደድክ።

አጃ.....ኢብ ነዉ አቦ

የትህትናህ ድንቁ
ምስጢርህ መርቀቁ
አለምን ከመፍጠር ሰ'ዉን የማዳንህ እጅጉን መድነቁ

መልካም ልደት ላንተ
ከክብሩ ወርዶ ለተንከራተተ

መልካም ልደት ለኔ
ከበረት ወጥቼ ለከበርኩኝ እኔ

።።።።።።።።።
።።።።።።።።።
አጃኢብ🙈
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤❤
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems




ዛሬ 3:00 live አለን ዉዶች እንዳትቀሩ




በዛሬዉ live...ስለምን እናወራለን መሰላችሁ......

#ግጥም እናንባለን ( የናንተንም ግጥሞች)

#ከግጥም ጋር ስለተያያዙ ገጠመኞቼ እናወራለን።

#ግጥም መፃፍ እንዴት እንደጀመርኩና ደግሜ ግጥም የደረሰበት አልደርስም ስላልኩባቸዉ ቀናት🤭

#ገጣሚ ነኝ ለማለት ለምን እንደማልደፍር ( በዚ ሀሳብ ለራሴ በደምብ የሚገዛኝ ግጥም ከፃፍኩ ገጣሚ ነኝ) የምል ሰዉ ነኝ ስለ ሀሳቤም በደምብ እናወራለን

ጥሩ ገጣሚ ለመሆን ለኔ የጠቀመኝን Tip እነግራችኃለሁ

@Tizitawolde_poems


ስለቀናነታችሁ ከልቤ ነዉ የማመሰግነዉ ሁላችሁንም ነገ ማታ 3:00 ሰአት የትም እንዳትሄዱ ግብዣ አለኝ ለማክበር ( Telegram live ) ላይ ነዉ 😁 እና ስለምን እንደሚሆን ነገ አሳዉቃችኃለሁ።


🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🍾🍾🍾🍾🍾🍾🍾🍾
ተመስገን🤲🏻 ክበሩልኝ የኔ ዉድ ቤተሰቦች 6000 ሞልተናል አመሰግናለሁ ሁላችሁንም።


9 ሰአት ስትቀጥረኝ

እንዴት ሆኜ ልጠብቅህ?

መልከ ዑራኤልን እየደረስኩ
ወይስ
መልከ ገፅህን እያሰብኩ?


ትዝታ ወልዴ)💕

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems


9 ሰአት ስትቀጥረኝ..........




ወደድኩሽ ካለኝ በኃላ......

ስደዉል ስልኩን ቢዘጋም
ስቀጥረዉ ቢቀርብኝ
መልዕክቴን አይቶ ዝምቢል
በድንገት ባገኘዉ እንኳ በፍጥነት ከኔ ገሸሽ ቢል....

እኔ ልሙት ይወደኛል.......

ቢፈራኝ ነዉ እንጂ ፍቅሬ ቢያስጨንቀዉ
ምን እላት እያለ ስለሚ'ያሳስበዉ
ስልኩን የማይመልስ ትቶኝ የሚሮጠዉ

ሌላ ጊዜ እድል ቀንቶኝ
በአንዲቷ ቀን ካፌ ቀጥሮኝ
አይኖቹ ከስልኩ
አያየኝም ብዬ ያልኩ
ሌላ ሴት እያየ በድንገት ሲጠቅሳት
አይኔ ካይኑ ተገጫጨ
የያዘዉ ብርጭቆ ከእጆቹ አሟለጨ

ፈገግ አልኩ ደነገጠ
ምንን ያህል ቢወደኝ ልቡ የቀለጠ?
አወይ አጋጣሚ ብዬ ተገረምኩ
ይሄኔ ሲያየኝ ደንግጦ ነዉ አልኩ

እኔን ይንሳኝ ይወደኛል ስላችሁ
ደግሞ የዛሬዉን ጉዱን ልንገራችሁ

መጥሪያ አምጥቶ እጆቼ ላይ አስቀመጠ
ላገባ ነዉ ብሎ ልክ እንደ ልማዱ ደሞ ፈረጠጠ

ገለጥኩት.......
የልቤ ከምላት ከኔዉ ጓደኛ ጋር
የሚሆናት አጋር

ምን ያክል ቢወደኝ
እንዴት ቢሳሳልኝ
አወይ የሱ ፍቅር

የልቤ ምላትን እንደ ልቡ አድርጐ
እኔን ለማስደሰት ሚያገባት ሰርጐ

ይወደኝ አይደለ?

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ✍🏽
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems

4.8k 0 34 22 75

ልልክላችሁ ነዉ ግን የኔ ታሪክ አደለም ስለጠፋችሁ ነቃ ነቃ እንድትሉልኝ ነዉ😂🫠


እንዴት ናችሁልኝ የምወዳችሁ🥰
ለማንም ያላወራሁትን 1 ታሪኬን በግጥም ፅፊዋለሁ ነገ ጠብቁኝ አሁን ተኝታችኃል ብዬ ነዉ😁

4k 0 3 15 26
Показано 20 последних публикаций.