ከምቀኝነት እንውጣ!!
-------------------------
በበታችነት ስሜት ከምትሰቃይ፤
ለምን መክሊት አትፈልግም፡
ሌሎች ላይ ሴራ ከማሰብ፤
እርክሰት ጋር ከምታዘግም፡
እኔም የራሴን ከያዝኩ፤
አንተም የራስህ ካለህ፡
እስኪ ቆመህ ተጠየቅ!?
ምን ሊጠቅም ትመቀኛለህ??
ከዱንያ ስቃዩ በላይ፤
ይከፋልና የነገው ጣጣ፡
እባካችን እንተሳሰብ፤
ከምቀኝነት እንውጣ፡
➥እንደ ምቀኝነት ራስን አቃጥሎ የሚጨርስ መርዛማ በሽታ የለም።
እየተቀባህ የማያወዛ
እየሸጥክ ፈፅሞ አትገዛም
ምቀኝነት ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ አደገኛ ቫይረስ ይመስለኛል...ብቻ ሁላችንም እንከልከል ሐቂቃ!!
◎قال الشيخ صالح آل الشيخ حفظه الله
لا تحسد من هو أحفظ منك
أو أعلم منك
أو أنفع للعباد منك
ሷሊህ አሉ-ሸይኽ ይህን ይላሉ፦
ከአንተ የተሻለ ለፊዝ፣
ከአንተ የተሻለ አዋቂ፣
ከአንተ የተሻለ ለዑማው ጠቀሚ የሆነን ሰው አትመቀኝ።
بل افرح أن يقوم قائم بحق الله عز وجل وحق العباد
በል እንደውም በአላህ ሐቅ ላይና በባሮቹ ሐቅ ላይ በመቆሙ ልትደሰት ነው የሚገባው ይላሉ።
الطريق إلى النبوغ العلمي ص:115 رقم 537
.....✍️ኑረዲን አል-ዓረብ
t.me/nuredinal_arebit.me/nuredinal_arebi