አብሽር!
ከትላንት የባሰ ነገር ቢወሳሰብ
ዛሬ ላይ ቢከብድህ ነገህን ለማሰብ
ጫናው እጥፍ ሆኖ የኑሮ ግብግብ
ሌላኛው ቢለኮስ አንደኛው ሲረግብ
ወጣው ሲሉ መውደቅ ቀን እያዳለጠ
ያዝኩ ሲሉ ማጣት ከእጅ እያመለጠ
ነፍስን የሚፈትን የሌለው መባቻ
እሽቅድድም ቢሆን ሰርክ ድካም ብቻ
ቢበዛውም ህይወት ፈተና ቢከበው
እጅ መስጠት የለም ሁሉም ለበጎ ነው
ከትላንት የባሰ ነገር ቢወሳሰብ
ዛሬ ላይ ቢከብድህ ነገህን ለማሰብ
ጫናው እጥፍ ሆኖ የኑሮ ግብግብ
ሌላኛው ቢለኮስ አንደኛው ሲረግብ
ወጣው ሲሉ መውደቅ ቀን እያዳለጠ
ያዝኩ ሲሉ ማጣት ከእጅ እያመለጠ
ነፍስን የሚፈትን የሌለው መባቻ
እሽቅድድም ቢሆን ሰርክ ድካም ብቻ
ቢበዛውም ህይወት ፈተና ቢከበው
እጅ መስጠት የለም ሁሉም ለበጎ ነው