ኦርቶዶክስን ከማደስ ወደ ማዘመን
(ሀሳቡ ላይ ብቻ አስተያየት ስጡ፣ ስድብ አይፈቀድም)
የተሐድሶ እንቅስቃሴ እንዳቆጠቆጠ ገደማ ማኅበረ ቅዱሳን አንድ አነስተኛ ጥናት አዘጋጅቶ ነበር። በወቅቱ ተሐድሶ የሚባሉ አካላት ዋነኛ መከራከሪያ የነበረው ራሳቸውን የቤተ ክርስቲያኗ አለኝታና ተቆርቋሪ አድርጎ ማቅረብ ነበር። ቤተ ክርስቲያኗን እንደሚቀበሉና ጠንካራ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖር እየታገሉ እንዳሉ አብዝተው ይገልጹ ነበር። ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን እንዲህ ሲል ይጠቅሰዋል፦
"ተሐድሶዎች በርግጥ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውን ይቀበላሉ? ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸውስ ተሐድሶ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ችግሮች ተፈትተው ጠንካራ የሆነች ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማየት የሚደረግ ትግል ነው?"
(የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ፥ አዘጋጅ ማኅበረ ቅዱሳን ገጽ 36)
መጽሀፉ ይህንን ጥያቄ ያነሳበት ምክንያት የተሐድሶ ሰዎች ከነሱ በላይ የቤተ ክርስቲያኗ ተቆርቋሪ የሌለ እስኪመስል ድረስ ሰፊ ሽፍን እንቅስቃሴ ያደርጉ ስለነበር ነው። መጋቢ በጋሻው እና ዘማሪ ትዝታው (በድሮ የማዕረግ ስማቸው) EBS ቴሌቭዥን ላይ በገዙት የእሁድ ጠዋት የአየር ሰአት ትልቅ ሽፋን ይሰጡ የነበሩት የእቅበተ እምነት ስራዎች ላይ ነበር። በተለይም በፕሮቴስታንት በኩል የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በመሞከር የኦርቶዶክሱን ቀልብ ለመያዝ ይጥሩ ነበር።
ኢየሱስ በዮሐንስ ወንጌል ማርያምን "አንቺ ሴት" ማለቱን ተከትሎ በፕሮቴስታንቶች ለሚነሱ ጥያቄዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ ለመመለስ ሲሞክሩ በግሌ በወቅቱ ተመልክቻለሁ። ከዚያ እይታየ በኃላ እስኪያቆሙ ድረስ ተከታትያቸዋለሁ። ትኩረታቸው እቅበተ እምነት ተኮር ከመሆኑ ጋር "የኦርቶዶክሱ አለኝታ" ተደርገው በመሳላቸው ሳቢያ የጠዋት ፕሮግራሙን መከታተሌን አስታውሳለሁ።
እነዚህ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ መስለው መቅረባቸው ምዕመኑን በቀላሉ እንዲያሳስቱት ጠቅሟቸዋል። ማኅበረ ቅዱሳን ለዚህም ነበር በመጽሀፉ ይህንን ጉዳይ ለምዕመኑ ለማብራራት የተለያዩ አቋሞችን በመዘርዘር የተሐድሶ ሰዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አቋም እንደሚለይ ለማሳየት የደከመው። በመጽፋቸው ከዘረዘሯቸው ነጥቦች ውስጥ የተሐድሶ መለያ አድርገው ያቀረቡት የቤተክርስቲያኗን ታሪክና ትውፊት ማጣጣል ወይንም ዝቅ አድርጎ የማየት መንገድ አንዱ ነው።
የተሐድሶ ሰዎች ቤተ ክርስቲያኗን ወደ ሚፈልጉት አላማ ለማምጣት መርህ አልባ ከመሆናቸው ጋር ማንኛውም መንገድ ከመጠቀም ወደ ኃላ እንደማይሉ መጽሀፉ ይጠቅሳል። በነሱ እሳቤ በተለይም ገድላትና ድርሳናትን ማሳነስ/Undermine/ በቀላሉ ኦርቶዶክስን የማፍረስ ዘዴ ነው የሚል እሳቤ በመያዛቸው ይህኛው አካሔድ ትልቁ የስኬት መንገድ ነው። መጽሀፉ እንዲህ ይላል፦
"ስለዚህ አዲሱ ስልት “የጥንቷ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትክክል ነበረች - The ancient Orthodox was the right Church" የሚል ነው፡፡ ይህም ማለት ቤተ ክርስቲያንን ከውጭ ከመቃወም ይልቅ ውስጥ ገብቶ ምእመን፣ ካህን፣ ሰባኪ መስሎ ከፕሮቴስታንት እምነትና ባህል ውጭ ያለውን ነገር ሁሉ “ይህ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት አይደለም፣ ይህን እገሌ የጨመረው ወይም የቀነሰው ነው ´ እያሉ ቤተ ክርስቲያኗ ኦርቶዶክሳዊ ዶግማዋ፣ ቀኖናዋና ትውፊቷ በሙሉ ጠፍቶ ፍጹም የጠራች የነጣች ድሀ ፕሮቴስታንት እስክትሆን ድረስ መሥራት ነው"
(የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ፥ አዘጋጅ ማኅበረ ቅዱሳን ገጽ 45 እና 46)
ይህ የተሐድሶ መንገድ የቻለውን ያክል ምዕመን ወስዶ አገልግሎቱ ያበቃለት በመሆኑ አዲስ መንገድ ሳያስፈልግ አልቀረም። ፕሮቴስታንቶቹ ምን አይነት መንገድ እንደነደፉ በትክክል ባላውቅም በግል ካየሁት አንጻር ግን ቸርቿን ከታሪክና ትውፊቷ በማላቀቅ የማዘመን ስራ ሌላኛው አዲሱ ስትራቴጁ እንደሆነ መገመት ይቻላል።
የድሮ ምልምሎች የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት፣ መምህራንና ካህናት ሲሆኑ የአሁኖቹ ደግሞ ትምህርት ቀመስ የሚመስሉ ለቸርቿ የአለኝታነት ስሜት መፍጠርን አላማ ያደረጉ ግለሰቦች ናቸው። እነዚህ ከቀድሞዎቹ የሚለዩት ቆብና ጥምጣም ባለማድረግ እንጅ የቤተ ክርስቲያኗን ትውፊቶች ዝቅ በማድረግና ለመድረክ የማይመጥኑ አድርጎ በማቅረቡ ረገድ ልዩነት የላቸውም።
ከቀድሞዎቹ ስህተት የተማሩት ነገር ቢኖር ገድላትና ድርሳናትን በግልፍተኝነት መስደብ ልክ አለመሆኑን ነው። በቀላሉ እነዚያን መጽሀፍ ለውይይት የማይበቁ መሆናቸውን በመናገር ገሸሽ ማድረግ ከተቻለ መስደቡና ማንቋሸሹ ረጅም ጉዞን ከማሳጠር የዘለለ አስፈላጊ አለመሆኑን ነው። ይህኛው ብልጥ አካሔድ/Smart move/ ይመስላል።
በግል ለእኔ እንደ አንድ ሙስሊም ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው። አንድ ሰው ፕሮቴስታንትም ቢሆን ኦርቶዶክስም ቢሆን ከእምነት አንጻር የሚፈጥረው ለውጥ አለ ብየ አላምንም። እንደ ሀገር ባለን የጋራ መስተጋብር ግን የቤተ ክርስቲያኗ ትውፊት በምዕራቡ አለም በተቃኘው ዘመን አመጣሽ ጸያፍ ባህል እንዲቀየር አልመኝም። ቤተ ክርስቲያኗ ግብረ ሰዶማዊነትና መሠል ጸያፍ ተግባሮችን መቃወሟን ለመደገፍ ትውፊቷን መቀበል አይጠበቅብኝም።
በዚህ ረገድ የሀገራችን የፕሮቴስታንት ቸርቾች ተግባሩን ሊቃወሙ ይቅርና ዋናዎቹ የኛ ሀገር ቤተ ክርስቲያናት ሳይቀር በትብብር/Partner/ የሚሰሩ ከነዚሁ ደጋፊ የሆኑ የውጭ ቸርቾች ጋር ነው። እነዚህ አካላት ለችግራችን በቂ ናቸው ብየ አምናለሁ። ኦርቶዶክሱን በራሳቸው መንገድ በመለወጥ ለዚህና መሠል ምዕራባዊ ፍላጎታቸው ማዋላቸው እንደ ሀገር አደገኛውን መንገድ ከማስጀመር የዘለለ ጥቅም የለውም።
▣ ይህ መልካሙን ከመመኘት የተጻፈ የግል አመለካከት ነው
(የሕያ ኢብኑ ኑህ)