ያው ክረምትም አይደል
++++++++++++++++
ያ ፀሀይ አለፈ ጋረደው ደመና ፣
ብርድ ይመጣ ጀመር ፀሀይ አለፈና ፣
በየጎዳናው ሰርጥ ሲያወርደው ዝናቡን ፣
ተጠሎ ያሳልፋል ሁሉም ይዞ ጥጉን ፣
አንዳንድም አይጠፋም ዝናብ የናፈቀው ፣
መጠለል ሳይፈልግ የሚበሰብስ ሰው ።
ያው ክረምትም አይደል
ጥንዶች ጎዳናው ላይ
ዣንጥላውን ጥለው በዝናብ ሲመቱ ፣
እዚ ደሞ ሴቷ
በመከዳቷ ላይ ሲደረብ ክረምቱ ፣
ከአልጋዋ ሳትወጣ
ቀኑን እንዳመሸች ሲነጋባት ሌቱ ፣
በነጎድጓዱ ድምፅ ብልጭ ሲል ብርሀኑ ፣
መብረቅ አስደንግጦት ሲደበቅ ህፃኑ ።
ያገላጣ ሜዳ በሳር ተሸፍኖ ፣
አፈሩ ለምልሞ አረንጓዴ ሆኖ ፣
ተፈጥሮ ተውባ በአበቦች ደምቃ ፣
ለአይን ስታሰማው መሳጩን ሙዚቃ ፣
የጋጣው እንስሳት አልፎላቸው ምጡ ፣
የደረቀን ትተው ለምለም ሳር ሲግጡ ፣
ዋሽንቱን ሲጫወት እረኛው በመስኩ ፣
የተፈጥሮ ዳራ ያምርበታል ልኩ ።
ያው ክረምትም አይደል
ገበሬው ሲዘራ አፈር ለም ሆኖለት ፣
እሱም እንዳመነው አምላክ ጠብቆለት ፣
በእርሻ እንዲያባርረው የህዝቦቹን ርሀብ ፣
ዘመኑ የሰላም እንዲሆን የጥጋብ ፣
መጣለት ክረምቱ ይዘራል ሊያርሰው ፣
ሰው ጦም እንዳያድር አጥቶ የሚቀምሰው ።
ደሞ መሸት ሲል በየጎዳናው ዳር ፣
ሆድን ሞቅ የሚያደርግ በቆሎ ይሸጣል ፣
ያሻው አስጠብሶ ያሻው አስቀቅሎ ፣
ሲጣፍጥ ብትቀምሺው ከወክ ጋ በቆሎ ፣
ስንቱ በዛው ቀረ አስጠልይኝ ብሎ ።
ያው ክረምትም አይደል
ትምህርት ይዘጋል
ሀገሩ በሙሉ በህፃናት ይሞላል ፣
መቦረቅ ያማረው እልሁን ይወጣል ፣
በልጆች ጫጫታ መንደር ይቀወጣል ፣
ቤት የሚያፈስበት ባልዲ ይደቅናል ፣
ጭጋግ በከደነው በቀዝቃዛው አየር ፣
አሎሎ የሚያህል በረዶ ይዘንባል ።
ከተሜው ከገጠር ገጠር ያለው ሸገር ፣
በዘመድ ጥየቃ ይጎበኛል ሀገር ፣
ሰካራም መጠጡን ትዳር ያለው ሚስቱን ፣
ጎኑ ሸጎጥ አርጎ እየሞቀ እሳቱን ፣
እንዲ እያዘናጋ ያልፈዋል ክረምቱን ፣
እጀ ጉርዱ ቀረ መልበስ የለም ቁምጣ ፣
ብርድ ነው ምግቡ ሳይደርብ ለወጣ ፣
ደረብ ደረብረብ ቁምሳጥን አስንቆ ፣
ክረምት እንዲህ ያልፋል በሀበሻ ደምቆ ።
#በረከትዘውዱ
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
++++++++++++++++
ያ ፀሀይ አለፈ ጋረደው ደመና ፣
ብርድ ይመጣ ጀመር ፀሀይ አለፈና ፣
በየጎዳናው ሰርጥ ሲያወርደው ዝናቡን ፣
ተጠሎ ያሳልፋል ሁሉም ይዞ ጥጉን ፣
አንዳንድም አይጠፋም ዝናብ የናፈቀው ፣
መጠለል ሳይፈልግ የሚበሰብስ ሰው ።
ያው ክረምትም አይደል
ጥንዶች ጎዳናው ላይ
ዣንጥላውን ጥለው በዝናብ ሲመቱ ፣
እዚ ደሞ ሴቷ
በመከዳቷ ላይ ሲደረብ ክረምቱ ፣
ከአልጋዋ ሳትወጣ
ቀኑን እንዳመሸች ሲነጋባት ሌቱ ፣
በነጎድጓዱ ድምፅ ብልጭ ሲል ብርሀኑ ፣
መብረቅ አስደንግጦት ሲደበቅ ህፃኑ ።
ያገላጣ ሜዳ በሳር ተሸፍኖ ፣
አፈሩ ለምልሞ አረንጓዴ ሆኖ ፣
ተፈጥሮ ተውባ በአበቦች ደምቃ ፣
ለአይን ስታሰማው መሳጩን ሙዚቃ ፣
የጋጣው እንስሳት አልፎላቸው ምጡ ፣
የደረቀን ትተው ለምለም ሳር ሲግጡ ፣
ዋሽንቱን ሲጫወት እረኛው በመስኩ ፣
የተፈጥሮ ዳራ ያምርበታል ልኩ ።
ያው ክረምትም አይደል
ገበሬው ሲዘራ አፈር ለም ሆኖለት ፣
እሱም እንዳመነው አምላክ ጠብቆለት ፣
በእርሻ እንዲያባርረው የህዝቦቹን ርሀብ ፣
ዘመኑ የሰላም እንዲሆን የጥጋብ ፣
መጣለት ክረምቱ ይዘራል ሊያርሰው ፣
ሰው ጦም እንዳያድር አጥቶ የሚቀምሰው ።
ደሞ መሸት ሲል በየጎዳናው ዳር ፣
ሆድን ሞቅ የሚያደርግ በቆሎ ይሸጣል ፣
ያሻው አስጠብሶ ያሻው አስቀቅሎ ፣
ሲጣፍጥ ብትቀምሺው ከወክ ጋ በቆሎ ፣
ስንቱ በዛው ቀረ አስጠልይኝ ብሎ ።
ያው ክረምትም አይደል
ትምህርት ይዘጋል
ሀገሩ በሙሉ በህፃናት ይሞላል ፣
መቦረቅ ያማረው እልሁን ይወጣል ፣
በልጆች ጫጫታ መንደር ይቀወጣል ፣
ቤት የሚያፈስበት ባልዲ ይደቅናል ፣
ጭጋግ በከደነው በቀዝቃዛው አየር ፣
አሎሎ የሚያህል በረዶ ይዘንባል ።
ከተሜው ከገጠር ገጠር ያለው ሸገር ፣
በዘመድ ጥየቃ ይጎበኛል ሀገር ፣
ሰካራም መጠጡን ትዳር ያለው ሚስቱን ፣
ጎኑ ሸጎጥ አርጎ እየሞቀ እሳቱን ፣
እንዲ እያዘናጋ ያልፈዋል ክረምቱን ፣
እጀ ጉርዱ ቀረ መልበስ የለም ቁምጣ ፣
ብርድ ነው ምግቡ ሳይደርብ ለወጣ ፣
ደረብ ደረብረብ ቁምሳጥን አስንቆ ፣
ክረምት እንዲህ ያልፋል በሀበሻ ደምቆ ።
#በረከትዘውዱ
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch