አሳዛኝ ታሪክ ትማሩበታላችሁ
ይህ አሜሪካዊ ስሙ ኢሳያስ ማቴዎስ ይባላል።
አሜሪካን አይዶል ላይ ቀርቦ እንዲህ አለ...
"ልጅ እያለሁ እንደንማኛውም ልጅ ብዙ ምኞትና ተስፋ ነበረኝ። አድጌ፣ ተመርቄ፣ ስራ ይዠ፣ ሚስት አግብቸ፣ ልጆችን ወልጀ፣ በቤተክርስቲያን በዘማሪነት እያገለገልኩ በደስታና በስኬት የመኖር ትልቅ ህልምና ተስፋ ነበረኝ። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አንዱም አልተሳካልኝም። ምክንያቱም 18 ዓመት ሲሆነኝ በአንድ በተረገመች ዕለት ምንም በማላውቀው ጉዳይ ፖሊሶች በዘረፋ ተጠርጥረሀል አሉና ያዙኝ። ኧረ ንፁህ ነኝ ብልም የሚሰማኝ ጠፋና ተዘርፈዋል የተባሉት ሰዎች ይመስላል ስላሉ ብቻ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደብኝ። ያለ ጠያቂ ለ54 ዓመታት በአንድ ክፍል ውስጥ ተቆለፈብኝ።
መጀመሪያ አካባቢ ተስፋ ቆረጥኩ። ቆየት ብዬ ግን ይህ ነገር የእግዚአብሔር አላማ ይሆናል ብዬ በፀጋ መቀበል ጀመርኩ። ከዚያም ያለ አጃቢ ባንድ፣ ያለ ምንም ሙዚቃ መሳሪያ፣ በባዶ ክፍል ውስጥ በየቀኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር ማመስገን ጀመርኩ። ብዙ አመታት ያለምንም ለውጥ ነጎዱ...
ከ54 ዓመታት በኃላ መዝገቤን በአጋጣሚ ሲያየው አላግባብ እንደተፈረደብኝ የተገነዘበ አንድ ወጣት የህግ ባለሙያ ወደእኔ መጣና ጉዳዬ እንደገና እንዲታይ(Judicial review) ሊያደርግ እንደሆነ ነገረኝ። ተስፋ ባላደርግበትም ይቅናህ አልኩት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን እንደገና አሳይቶ በ72 ዓመቴ በነፃ እንድለቀቅ አደረገኝ።
ስወጣ ግን ምንም ነገር አላገኘሁም። ቢሆንም እግዚአብሔር ይመስገን እዚያ እያለሁ በነፃነት በመኖራቸው እቀናባቸው የነበሩት ብዙዎች በህይወት የሉም። እኔ ግን ዛሬ ላይ ንፁህ አየር እየተነፈስኩ የማለዳ ፀሀይ በነፃነት እየሞቅኩ በህይወት አለሁ። በህይወት መኖር ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን በህዝብ ፊት እዘምራለሁ ብዬ ስመኘው የኖርኩት ምኞቴ እውን ሆኖልኝ ይሄው በእናንተ ፊት ቆሜ እግዚአብሔርን ላመሰግን ስለሆነ ደስተኛ ነኝ" አለና በለስላሳ ድምፁ....
"በሀሰት በከሰሱኝ ጊዜ፣ የሚሰማኝ አጥቸ በተፈረደብኝ ጊዜ፣ ከ50 ዓመታት በላይ ያለበቂ ምግብና ልብስ፣ ያለጠያቂ ወገን በአንድ ክፍል ውስጥ በተዘጋብኝ ጊዜ፣ አለም ሁሉ በረሳኝ ጊዜ፣ አበቃልኝ ብዬ ተስፋ ቆርጨ ቀኑም ሌቱም በጨለመብኝ ጊዜ ከጎኔ ያልተለየኸው አባቴና አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ከልቤ አመሰግንሀለሁ!" እያለ በእንባ ታጅቦ መዝሙሩን ያንቆረቁረው ጀመር።
ይህኔ ከአወዳዳሪዎች እስከመድረክ አስተናባሪዎች፣ ከታዳሚዎች እስከጥበቃዎች አዳራሹ በሙሉ በለቅሶ ተናጋ።
በእርግጥ እንኳን እነሱ እኔም ሳየው አልቅሻለሁ።
(መዝሙሩን በዚሁ ገፅ እለጥፈዋለሁ)
ጎበዝ እምነት ማለት ሲደላን የምናጠነክረውና የምንጠብቀው ስንጣል ደግሞ የምንጥለው አይደለም። እግዚአብሔርን በመሸ በነጋ እንደኢሳያስ ከልብ ለማመስገን ምንም ባይኖር በእስር ቤትም ቢሆን ያለምንም ነገር መኖር ብቻ በቂ ነው!!!
መልካም ጊዜ!
Joye