ሰዋስው/@zsewasw


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Лингвистика


ሰዋስው

# ሰዋስው ማለት መሰላል ነው።
መሰላል የማይደርሱበት ነገር ተጠቅመው እንዲቻል እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህም ቻናል ችግር የሚባል ነገርን አስወግዳችሁ ወደ መልካም ነገር የምትወጡበትን ትምህርት ታገኛላችሁ።
እኔን ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ
+251934636523

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Лингвистика
Статистика
Фильтр публикаций


➕የማርታ ጸሎት➕

ማርያም: ትእዛዙን ሰሚ
ማርታ: የማይታዘዘውን አምላክ አዛዥ፣ "ንገራት" ባይ። (ሉቃ 10፥40)

➕እኛስ የእርሱን ትእዛዝ በትሕትና እንሰማለን ወይስ እንደ ማርታ "እንዲህ አድርግ? እንዲህ ተናገር?" ብለን የምንፈልገውን እናዘዋለን?

እስኪ ጸሎታችንን እናስተውል!

➕ዘሰዋስው


⏺ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ ፤
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማያት
እንኳን ፡ አደረሳችሁ🔴


❗️ንጽሕና

✔️በንጽሕና ለመኖር እየታገለ የሚወድቅን እግዚአብሔር አያዝንበትም። ድካሙን እና ያልተቋረጠ ጥረቱን አይቶ ድል የሚነሣበትን መንፈሳዊ ጸጋ ይሰጠዋል እንጂ።

✔️ እንድትኖር በታዘዝከው ልክ ለመኖር ሞክረህ ስላልሆነልህ በራስህ ተስፋ አትቁረጥ።

✔️መሆንህን ብቻ ሳይሆን ፈልገህ መሞከርህን እግዚአብሔር ይጽፍልሃል። ሰይጣን አቁስሎህ ስለሻረው ጠባሳህ አትቆጭ።

✔️ ብዙ ጠባሳ እኮ  ለሚዋደቅ ጀግና ወታደር የክብር ምልክቱ ነው። አፈ ወርቅ ዮሐንስ እንደሚለው የማይቆስለው የማይዋጋ ብቻ ነው።

#ዘሰዋስው

@zsewasw


⭐ፍቅር እንደሞት የጸናች ናት

⏺አጥብቆ የወደደ ሰው በትንሽ ነገርም አጥብቆ ሊጠላ ይችላል
መጠንቀቅ አለብን!

⏺ለፍቅሩ ዋጋ ካልተሰጠው ፍቅር መች ነው የሚከፍለው ከተባለ ለፍቅሩ ዋጋ ሳይሰጠው ሲቀር ነው።

⏺ፍቅር ክብር ካልተሰጠው ይጠፋል።
⏺ፍቅር ክብርን መንካት የለበት።

⏺ክብርም ፍቅር ማስቀረት የለበትም።

⏺በመዋደድ የሚጠፋ ክብር መኖር የለበትም።

⏺እግዚአብሔር ያን ያህል የከበረ አምላክ ሲሆን ዝቅ ብሎ ነው የሚወደን።

⏺ከድሃ ቤት የሚገባ፣ እኛን የመሰለ፣የእኛን ስጋ ለበሰ፣በእኛ ቃል የተናገረ፣በእኛ የተመላለሰ የእኛን ውሃ የለመነ።

⏺ዝቅ ብሎ ነው የሚወደን።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

#ዘሰዋስው

@Zsewasw


ሰው ራሱን ሳያውቅ የሚቀረው ስላልቻለ ብቻ አይደለም፡፡ ራሱን ማወቅ ስለማይፈልግም ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ‹ራስን ማወቅ› ይዞ የሚያመጣው ጊዜያዊ ሕመም ወይም ትንሽ ስቃይ አለ፡፡ ወደ ራሳችን መመልከት ስንጀምር የማንፈልገውን ‹‹እኛነት›› በውስጣችን ልናገኘው እንችላለን፡፡ በዚህም መረበሽ፣ መቆጨት፣ ኃፍረት ይሰማን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ስሜት ለማምለጥ ብለን ወደ ቅዠታዊ ዓለም ይሄድ ዘንድ ለራሳችን ልንፈቅድለት አይገባም፡፡ ለእኛ ከማንም በላይ ጠላት የሚሆንብን ይህ በውስጣችን የተደበቀውና ማወቅ የማንፈልገው ‹‹ስውር እኛነታችን›› ነው፡፡ ስለዚህም በጊዜ ራስን መርምሮ አፋጣኝ መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡


#ዘሰዋስው

@Zsewasw


ፈቃደ እግዚአብሔር



ፈቃዱ ነገሮችን ሁሉ የመቆጣጠር አቅም አለው:- ፈቃዱ በአስር፣ በበሽታ፣ በምርኮ፣ በስደት ማለፍ ቢሆን እንኳ ይህን የመቆጣጠር _ አቅም አለው:: ችግሮችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይቆጣጠር ኖሮ ማንም አይኖርም ነበር፡፡ የሰው ፈቃድ ግን ፈቅዶ አንድ ነገር ማድረግ ቢችልም የነገሩን ሂደት ግን መቆጣጠር አይችልም፡፡ ነገሩ ራሱ ሰውዬውን መቆጣጠር ይጀምራል፡፡

ፈቃዱ በመጨረሻ ይፀናል፡- ጠቢባን በጥበባቸው፣ ኃያላን በኃይላቸው ይጓዛሉ፡፡

በመጨረሻ የምታሸንፈው የእግዚአብሔር ፈቃድ ናት፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የምንኖረው እንደምንፈልገው ሳይሆን እንደ ተፈቀደልን ነው፡፡ እንደ ፈቃዳችን እዚህ አገር፣ በዚህ የኑሮ ደረጃ አልነበርንም፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ግን ትገድባናለች፡፡ ይህ መልካም ነው፡፡

እግዚአብሔር ከፈቀደው ውስጥ ምንም ክፉ የለም፡፡ «የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን» (የሐዋ.ሥራ 21÷14)። ምንም አስተያየት ሳንሰጥ እንዲህና እንዲያ የሚሉ ግምቶችን ሳንሰነዝር በፈቃዱ ተስማምተን ማረፍ ይገባናል፡፡ «ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው» (ሰቆ.ኤር 3፣26):

#ዘሰዋሰው


@zsewasw
@zsewasw




ወዳጄ ሆይ!
ላይህ እያለቀሰ ውስጥህ የሚጽናና ከሆነ እግዚአብሔር እየደገፈህ ነው። ማልቀስህ ሩኅሩኅነትህን፣ መጽናናትህ መንፈስ ቅዱስ ካንተ ጋር መሆኑን ያሳያል።

✍ዘሰዋስው


19

እንኳን ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ዘሰዋስው


ወዳጄ ሆይ!
ትዕግሥት ልብን ከመድማት ይጠብቃል፣ የደማ ልብም በትዕግሥት ይፈወሳል። ነገርን በልኩ፣ ምድርን በማለፉ ለካው፣ የሚያስጨንቅህን አንሶ ታገኘዋለህ።

ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ሆይ!
በሁለት ዓይንህ ካለቀስህ መንገዱ ይጨልምብሃል፣ በአንድ ዓይንህ ስታለቅስ በአንድ ዓይንህ ክርስቶስን ተመልከት። ሁለት እጅህን ካጠፍህ ሚዛንህን መጠበቅ ያቅትሃል፣ አንዱ እጅህ ሲታጠፍ በአንዱ መሥራት ቀጥል። ልብህ መንታ ሁኖ ሲያስቸግርህ ነፍስህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ።

ዲን ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ኃጢአት ጸሎት የማቋረጥ ውጤት ነው። እውነተኛ ጸሎት ኃጢአትን የማቆም ምልክት ነው። ሰው ኃጢአትን ልምዱ ካላደረገ በቀር እየጸለየ የሚበድል፣ ከአምላኩ ጋር እየተነጋገረ የሚያምጽ የለም። አዳም እጸ በለስን የቆረጠው ከአምላኩ ጋር የነበረውን ንግግር (ጸሎቱን) በማቋረጡ ነው። ይኸውም አዳምን ጠርቶ "ወዴት ነህ?" ባለው በፈላጊው ድምጽ ተረጋግጧል።

ዘሰዋስው


https://t.me/ZSewasw


ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት

ሰው ብቻውን አይሆንም ። ወይ ከእግዚአብሔር አሊያም ከራሱ ጋር ያወጋል ። ሰው ካገኘም ከሰው ጋር ያወራል ። ትዝታም እንደ አሁን ትኩስና ወቅታዊ ሁኖ ያነጋግረዋል ። የመምህር ቃልም ከሚኖረው ኑሮ ጋር ሲገጣጠም እንደ ገና አዲስ ፍንዳታ ሁኖ በውስጡ ይጮኻል ። መስፈርት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ የነገረኝን ከኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጋር ማነጻጸር የጀመርኩት አሁን ነው ። ቤተ ክርስቲያን በእምነት የምትቀበል ፣ በፈሪሀ እግዚአብሔር መስፈርት የምትሾም ናት ። የአገልግሎት የመጀመሪያው መስፈርት ፍላጎት ነው ። አገልግሎት ጊዜን ሳይሆን ሕይወትን ሰጥተው የሚገቡበት ነው ። አገልግሎት የፍትፍት ሰደቃ ሳይሆን የመስቀል ጉዞ  ነው ። ገሀነምን ከሚያህል የእሳት ዓለም ነፍስ ሲያወጡ ወላፈኑ አይንካኝ ማለት ሞኝነት ነው ። የአገልግሎት ጉዞ ራስን መካድ ያለበት ነው ። ራሴን ከዛሬ ጀምሮ ያለ ክርስቶስ አላውቀውም ብሎ መማል ይጠይቃል ። ይልቁንም ኦርቶዶክሳዊው/ቀጥተኛው ጎዳና ብዙ እንግልት ከውስጥና ከውጭ ያለበት ነው ። ከክርስቶስ ጋር ያልሞተ ፣ ገና ውዳሴና ክብርን ነቅዐ ሐሰት ከሆነው ከሰው ልጅ የሚናፍቅ ጉዞው ይከብደዋል ። ኦርቶዶክሳዊው አገልግሎት በመከራ እድናለሁ ሳይሆን በመከራ የድኅነት ጉዞዬን እፈጽማለሁ ብሎ የሚያምን ነው ።


https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ....ዲቁና

መጨረሻ

ዲያቆን የሚያሰክር መጠጥ  አይጠጣም ። እንደ ውኃ እናት ከውኃ አይለይም ፣ ከውኃ ውጭ አይደፍርም ። አለልክ መብላትም የመስከር ያህል ነው ። ዲያቆን መጥኖ የሚበላ ፣ በምግብ ብዛት ዕድሜውን የማይጐዳ ነው ። ዲያቆን ከብዙ ሴቶች ጋር ወዳጅ የሚሆን ፣ የቆነጃጅት አጃቢና አጫዋች አይደለም ። መፍራት ገደሉን ሳይሆን የሚያዳልጠውን ስፍራ ነው ። አርቆ ማጠር የዲያቆን መገለጫ ነው ። አንድ ዲያቆን እውቀት ፣ ምሥጢር ጠባቂነት ፣ ጠንቃቃነት ያስፈልገዋል ። እንደ ወታደር የሚዘምት ፣ እንደ ሰላይ ለቤተ ክርስቲያት ጆሮ የሆነ ነው ። መጠጥና ሴት የሚወድድ ወታደርም ደኅንነትም መሆን አይችሉም ። ሁለቱም ጎበዙን ሁሉ ወንፊት ያደርጉታልና ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። ብሉይ ሐዲስን ነገር መለኮትን ላላወቀ አይሰጥም ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። ምእመናን ሊያከብሩት ይገባል ። ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ ዲያቆን ነበረ።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ...ዲቁና👑

ዲያቆናት ጭምት መሆን አለባቸው ። እኮ  ጭምት ማለት ምን ማለት ነው ? ጭምት ማለት ጣፋጭ ዝምታ ፣ ጣፋጭ ዝግታ ፣ ጣፋጭ ዕይታ ያለው ማለት ነው ። ጭምት ዱዳ አይደለም፣ ጭምት ለፍላፊ አይደለም ፤ ጭምት በቦታው ተገቢ ነገርን የሚናገር ነው ። የበደለ ሲያይ “የእኔን መጨረሻ አሳምርልኝ” ብሎ እያለቀስ የሚመክር ነው ። ድምፁ  እንደ አዋጅ ድምፅ አይደለም ። ያልሰማህ ስማ ፣ የሰማህን ላልሰማ አሰማ አይልም ። ዲያቆን የበላዩም የበታቹም ሲሳሳት በጭምትነት ይጸልያል ፣ በወዳጅነት ይመክራል። የቤተ ልሔም ምሥጢር ጠባቂ ነው ። የቤተ ልሔም ድንግል ሁሉን ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር ። ዲያቆንም ብዙ የማይደነቅ ፣ ብዙ የማይደነግጥ ነው ። ጭምት ለነገው የሚያስብ ፣ መጨረሻው እንዲያምር የሚጸልይ ነው ። ጭምት የሁል ጊዜ ተማሪ ነው ። ጆሮው እንደ ዝኆን ጆሮ ሁሉን የሚያደምጥ ፣ መልካሙን የሚቀበል ነው ። ጭምት ጊዜ ሰጠኝ ብሎ ማንንም ድጦ የማያልፍ ነው ። ጭምት ባይርበውም ለራበው ያዝናል። ራሱን ብቻ ሳይሆን ዙሪያውን ያያል።

ለዲያቆን... ወንድሞች #share

#ዘሰዋስው


https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ...ዲቁና

ዲያቆንን የማይወድ ማን አለ ? እግዚአብሔርን የሚወድድ ሁሉ ይወደዋል ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። የልጅነት ጨዋታን ለጌታው የሠዋ ፣ ከአብሮ አደጎቹ ይልቅ በዕድሜ የገፉትን አባቶች የመረጠ ፣ በየዕለቱ በአበው የሚመረቅ ፣ የየዋሃን የጸሎተኞች ቱፍታ ያረፈበት ነው ። ዲያቆን ቢያዜም ያምርበታል ፣ አንድ ልብ ነውና የኑሮ ሸክም አልመጣበትምና እውቀት ይጠልቅበታል ። የቄስ ፣ የጳጳስ ፣ የፓትርያርክ መሠረት ነው ። ሁሉም ዲያቆን ጳጳስ አይሆንም ፣ ሁሉም ጳጳስ ግን ዲያቆን ነበረ ። ዲቁናን ሁሉ ሊያከብረው ይገባል ። ዲያቆናት ሠልጣኝ ወታደር ፣ ተማሪ ደቀ መዛሙርት ፣ ወራሽ  ልጆች ናቸው ። የነገዋ ቤተ ክርስቲያን በዛሬዎቹ ዲያቆናት ትታያለች ። ዲያቆናት አበባ ናቸውና እንክብካቤ ይፈልጋሉ ፤ የከተማ መናኝ ናቸውና ጥበቃ ይሻሉ፣ ቆብ አልባ መነኮስ ናቸውና ከሴት ርቀው ንጽሕ ጠብቀው መኖር ይገባቸዋል ። ዲቁና መሠረት ነውና መሠረቱ የጸና መሆን አለበት ። ዲቁና ከተበላሸ ሁሉም ነገር እየተበላሸ ይመጣል።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw




ወዳጄ...

ዲያቆን ማለት የዋህ ፣ ትሑት ፣ የልጅ አዋቂ ፣ ክንፉ የቀለለው ፣ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት “ወዴት?” ባይ ፣ የመለኮት ልዑክ ፣ የመላእክት አምሳል ፣ የካህኑ የመቅደስ ልጅ ፣ ማዕረግ ያለው ተላላኪ ፣ እውቀት ያለው እውቀት ፈላጊ ፣ የሕፃን ምሥጢረኛ ፣ የጳጳስ ምርኩዝ ፣ የኤጲስ ቆጶስ ሰነድ ጠባቂ ፣ በንጹሕ ልብ እግዚአብሔርን አምላኪ ፣ ድንግል ፣ ቤተ ክርስቲያን እናቱ የሆነች ፣ እናትን በእናት የለወጠ ፣ የምሥጢራት አገልጋይ ፣ የቤቴል በር ከፋች ፣ ቢያዜም የሚያምርበት ፣ ቢስቅ የሚያስደንቅ ፣ ቢናገር የሚኮላተፍ አፈ ማር ፣ የገባሬ ሠናዩ ቄስ አዋጅ ነጋሪ ፣ ሰግዶ የሚያሰግድ ፣ የሊቁ አዳሪ ተማሪ ፣ የነገው ቄስ ፣ የነገው መነኰስ ፣ የነገው ጳጳስ ፣ ሁሉ የሚወደው ፣ ለመማር ማልዶ የወጣ ፣ አእይንተ እግዚአብሔር ካህናት የሚጠነቀቁለት ፣ ብዙ መካሪ ያለው ፣ የሚገሥጹት ልጅ ፣ የሚገርፉት ሹም ፣ በዓይን በጆሮ የሚማር ፣ የልብ አውቃ ፣ የወንጌል አክባሪ ፣ ዘመኑን ያተረፈ ፣ የአዲስ ኪዳን ነቢይ ሳሙኤል ፣ የዓመተ ምሕረት ነቢይ ኤርምያስ ፣ ታናሽነቱ የማይናቅ ፣ መሥዋዕት ቀማሚ ፣ በዕርፈ መስቀል ደመ ኢየሱስን አቀባይ ፣ የሥልጣን መሠረት ፣ ዕደግ ተብሎ የሚመረቅ ፣ ቢረግጡት ምንጣፍ ፣ ቢደገፉት መከዳ የሆነ ፣ እያፈረ የሚቀድስ ፣ እየፈራ የሚያስተምር ፣ የትምህርት ሱሰኛ ፣ በልጅነት የዘመተ ፣ የአባቱን ቤት ለጽድቅ የመነነ ፤ የእናቱን ጓዳ በልመና እንጀራ የለወጠ ፣ ተንቀሳቃሽ ተማሪ ፣ የብሉይ ጓደኛ ፣ የሐዲስ መሽራ ነው።

#ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


Репост из: Sewasw Tech
በትንሽ ኢንቨስትመንት በወር 500- 1000 ዶላር በላይ የምትሰሩበት
ከ2500-5000 ብር

ዝግጁ የሆነ ሰው ሊያናግረኝ ይችላል
@aklil24

መክፈል የማትችሉም አናግሩኝ ለእናንተም ስራ አለኝ።


ወዳጄ

በማለዳ ለመነሣት የሚያግዝህ በጊዜ መተኛት ነው ። እንቅልፍህን ሊጋፉ የሚችሉ ስልኮችና ሰው ሠራሽ ዕይታዎችን በጊዜ አቁም ። የምግብ ሰዓትህን ካላከበርህ ብትበላም እንደምትታመም ፣ የእንቅልፍ ሰዓትህን አለማክበርህ ብትተኛም ጤነኛ አያደርግህም ። በማለዳ ተነሣ ። ይህች ቀን ከዛሬ በፊት አይተሃት አታውቅምና አዲስ ቀን ናት ። ፀሐይ በምሥራቅ ስትወጣ ይህን ውበት ለማድነቅ በጠዋት ተነሣ ። የማለዳ ጸሎት አለና ያንን ለማድረስ በጠዋት ተነሣ ። እንቅልፍ የሞት ፣ መንቃትም የትንሣኤ ምልክት ነውና በማለዳ ተነሣ ።

ቅዱሳን አባቶች ሁሉ በማለዳ የሚነቁ ነበሩ ። በዓለም ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጡ ሰዎች የማለዳ ሰዎች ናቸው ። ከእንቅልፍ ለመነሣት ስንፍና ሲጫጫንህ ድሀ ለመሆን ወስነሃል ማለት ነው ። ደግሞም ሌሊቱን በሙሉ ሲያመሰግኑ ያደሩ ካህናትን አስታውስና በማለዳ ተነሣ ። ሌሊት በሙሉ ሲጠብቁ ያደሩ ሠራዊትን አስብና በማለዳ ተነሣ ። ሌሊት በሙሉ ሲጓዙ ያደሩ ፣ ሲያመርቱ ያነጉ መንገደኞችና ሠራተኞችን አስብና በማለዳ ተነሣ ። ይህች ቀን አይተሃት የማታውቃት ብቻ ሳትሆን ላትደገም የምታልፍ ቀን ናት ። ስለዚህ ቀኑን ዋልበት እንጂ አይዋልብህ ። በማለዳ ተነሣ ብዙ ትርፍ ታገኛለህ ። ሱሰኞች ማለዳቸውን ይበላሉ ። በጉልበት ለመነሣት ይቸገራሉ ። ማለዳን ክፉ ባልንጀርነቶች ያበላሹታል ። ማለዳህ እንደ ማታህ ነውና በጊዜ ተሰብሰብ ፣ በጊዜ ንቃ ! ዶሮ ራሱ ሳይነቃ ሌላውን አያነቃምና የበታች ሠራተኞችህን ለማበረታታት በማለዳ ተነሣ ።

እግዚአብሔር ያግዘን

#ዘሰዋስው


https://t.me/ZSewasw

Показано 20 последних публикаций.