አብዮት- ፔን
ተደጋጋሚ እና ለውጥ አልባ በሆነ መንገድ ላይ መጓዝ በራሱ አደገኛ ይሆናል። ለውጥንም ከማምጣት ይልቅ፣ “ሁሌም የምናደርገው በእንደዚህ አይነት መንገድ ነው” ማለት ይቀለናል፡፡ እውነተኛ የአብዮት ሰው ለመሆን ትልቅ ጥረት እና መስዋእትነት ይጠይቃል፤ ራሳችንንም ከማህበረሰቡ ነጥለን በአዲስ እይታ እና መንገድ መጓዝ ይጠበቅብናል፡፡
አሜሪካዊው የፖለቲካ ፈላስፋ የሆነው ቶማስ ፔን፤ “ለረዥም ጊዜ ከማህበረሰቡ ጋር የቆዩ ልማዶች፣ መጥፎ እና ስህተት ቢሆኑ እንኳ ሳንመረምር ልክ እንደሆኑ እንቀበላቸዋለን” ይለናል፡፡ ምን ያህል ኢ-ፍትሃዊነቶችን፣ በደሎችን ... መጥፎ ቢሆኑም እንኳ ልማድ ስለሆኑ ብቻ አሜን ብለን ተቀብለናል?
ለፔን ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚያገኟቸው መብቶች አሏቸው፡፡ ለምሳሌ በሕይወት የመኖር፣ የነጻነት፣ የመናገር እና የፈለጉትን የማመን መብት አላቸው፡፡
በተጨማሪም እንደየሁኔታው ህግ (መንግስት) የሚሰጠን አልያም የሚነሳን መብቶች አሉን፡፡
ሆኖም ባለስልጣናት ባህል በሚል ካባ የማህበረሰቡን መብቶች መጣስ ቀላል ይሆንላቸዋል። ባህል ወግ ውስጥ ሲደበቁ፣ ልማዶች የማህበረሰቡን አይኖች ይጋርዱታል፤ አምጾም አምባገነን መንግስቱን እንዳይጥል ይሆናል፡፡ እኛ ከመወለዳችን በፊት አያቶቻችን ሲመሩባቸው የነበሩ ወግ እና ልማዶች ዛሬ ላይ ሊያስሩን አይገባም። እያንዳንዱ ትውልድ እንደ ራሱ ነጻ ሁኖ መንቀሳቀስ አለበት... ባህል የአምባገነኖች መጫወቻ ያደርገናል።' አዎ... ከአያቶቻችን የምንወርሰው ጥበብ ይኖራል፤ ሆኖም ግን በእነርሱ ህጎች ዛሬ ላይ መመራት የለብንም፡፡
ፔን መንግስታትን አይወዳቸውም ነበር፤ እንደውም ከስር መሰረታቸው መጥፎ ናቸው ይለናል፡፡
መንግስታት አለቃ እና መሪም
ከመሆን ይልቅ የህዝቡ ባሪያ እና አገልጋይ መሆን አለባቸው፡፡ ይህ ሃሳብ ነው ፔንን ህዝቦች መንግስታቸው ፍትሃዊ እና መልካም ካልሆነ መገልበጥ አለባቸው ወደሚል ድምዳሜ ያደረሰው፡፡
ኢየሱስ በአይሁድ አለቆች ላይ አመጸ፤ ማርከስ አዲስ የሆነ አብዮታዊ ስርዓት ቀረጸ፤ ጋንዲ እና ማንዴላ በእንግሊዞች ላይ አመጹ... የሁሉም ጥያቄ የነበረው እና ሁሉም ሲሰብኩ የነበረው፣ የሰውን ልጅ ክቡርነት ነው፡፡ ሰው ሰብዓዊ መብቶቹ ሊጠበቁለት የተገባ ነው፡፡
እናም ምንም ያህል ባህል እና ስርዓታችንን የምናከብር ቢሆንም እንኳ የሰውን ክብር የሚነካ ከሆነ ማመጽ ይኖርብናል። ይህን ካላደረግን አምባገነኖች በባህል እና በብሄር ስም ይጨቁኑናል።
አመጽ እና አብዮት ለማስነሳት የሚያስችል ወኔ በውስጣችን አለን? ፔን እንደጻፈው “ዓለምን አፍርሶ እንደ አዲስ መገንባት የሚያስችል ኃይል አለን”
ልማዶች በራሳቸው መጥፎ አይደሉም፤ ሆኖም መጠቃትን እና መጨቆንን በጸጋ እንድንቀበል ምክንያት ይሆኑናል።
አዘጋጅ-ፍሉይ አለም
@Zephilosophy