ማንነት
ልጅ ሳለህ የተነሳኸውን ፎቶ ተመልክተኸው ታውቃላህ ? ምን ትዝ ይልሀል? ምንስ ታስታውሳለህ? ትንሹ አካልህ በግዙፍ አካል ተቀይሯል። የምታስባቸው ነገሮች ፣የምትመርጣቸው ነገሮች ልጅ ከነበርክበት ጊዜ በእጅጉ ተቀይሯል።ሰለዚህ ማንነትህ ተቀይሯል ማለት እንችላለን ? በእርግጥ ስለባለፈው ማንነትህ ትውስታ ይኖርሀል። ትውሰታህን በሙሉ አትጠተህ ማንነትህ በሌላ ማንነት ቢቀየርስ አንተ አለህ ማለት እንችላለን?
የፍልሰፍና ማዕድ መፅሀፍ ውስጥ ይሄን ፁሁፍ አገኘሁ
"ፊሊፕ ዲክ የተባለ ደራሲ በጻፈው We can remember it for you wholesale በተሰኘ የአጭር ልቦለድ ታሪክ ውስጥ አርኖልድ ኮነን የተባለ ገጸ ባህሪ እናገኛለን፡፡ ኮነን አንድ ቀን ደስ የማይል ነገርን አገኘ፡፡ ኮነን በጭራሽ አርኖልድ ኮነን አይደለም፡፡ ወይም በሌላ አነጋገር የቀድሞ ማንነቱ ሌላ ነበር። ግራ ተጋባ።
ታሪኩን ሲመረምርም ስለቀድሞ ማንነቱ ያውቃል። ሲወለድ የተሰጠው ስም አለን ውድ ነበር፡፡ ውድ መልካም ሰው አይደለም። ራስ ወዳድ፣ ጨካኝ እና ምህረት አልባ ነበር፡፡ ከሁለት አመት በፊትም ከወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር ጥልቅ የሆነ ችግር ውስጥ ገባ። እሱም ሁለት አማራጭ አቀረቡለት፤ ጭንቅላቱ ውስጥ ያሉት መረጃዎች በሙሉ ተደምስሰው በሌላ እና ልቦለዳዊ በሆነ የውሸት ሰው እንዲተኩ አልያም ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት እና ስቃይ ባለው እስር ቤት ውስጥ እድሜውን ሙሉ እንዲያሳልፍ፡፡
ትውስታዎቹ እንዲደመሰሱለት መረጠ፡፡ እናም አለን ውድ ጥልቅ የሆነ መደንዘዝ ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ ትውስታዎቹ በአዳዲስ እና በውሸት ትውስታዎች ተተኩለት፡፡ ሲነቃም እስከዛሬ የነበሩትን የሕይወት ትውስታዎች ሁሉ ዘንግቷል፡፡ እሱም የሚያውቀው ኮነንን እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
አሁን ላይ ኮነን፣ በቀድሞ ሕይወቱ አለን ውድ'ን እንደነበር አውቋል፡፡ እናም ይህ ሰው ማን ነው? ውድ ወይስ ኮነን?
የኮነን/ውድ የማንነት ቀውስን ለመፍታት ቀላል የሚመስል ችግር ቢሆንም፤ መልሱ ግን እንደምናስበው ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች የኮነን እውነተኛ ማንነቱ የቀድሞ ማንነቱ እንደሆነ ይደመድማሉ። የአብዛኞቻችን ማንነት ከአዕምሮ እና ከሰውነት እድገታችን ጋር የተቆራኘ ነውና እንዲህም ማሰባችን ተገቢነት ይኖረዋል። እስከ ዛሬ ሁለት አመት ድረስም ይሄ ሰው ወንጀለኛው አለን ውድ ነበር፤ አሁን አለን ውድ የለም የምንል ከሆነ፣ አስክሬኑ የታል፣ የታልስ የሞተው? ማንም የሞተ ሰው የለም፤ እና አለን ውድ የት ሄደ? ይሄ ሰውስ ማን ነው?
አርኖልድ ኮነን (በውሸት የተፈጠረው ማንነት) የአዕምሮ ጤና ሃኪም ነው፡፡ ስለ ልጅነቱም ሆነ ስለ ጉርምስናው የሚያስታውሰው አንዳችም ነገር እውነት አይደለም፡፡ ውድ የእውነት እንደሆነ ሁሉ ኮነን የውሸት ነው፡፡ አሁንስ ላይ ኮነን የውሸት ነው ብለን መደምደም እንችላለን?
ለምሳሌ ኮነን፣ ወንጀለኛው ውድን መሆን ይፈልጋል? ከመልካም ሰውነትስ ጭራቅ የሆነውን ውድ'ን መምረጥ ይፈልጋልን?"
መምረጥ ቢችል የትኛውን ማንነት መምረጥ ይኖርበታል ውድን ወይስ ኮነን?
@zephilosophy