"መሪ አስመሳይና አታላይ መሆን አለበት"
ማኪያቬሊ
ወደ ላይ መውጣት ከፈለግክ የግድ የበታቾችህን መጨፍለቅ ይኖርብሃልን? ስኬት የሚመጣው ሰዎችን በማታለል እና በክፋት ውስጥ ብቻ ነውን? ስለምንድን ነው በአብዛኛው ዘርፍ ላይ ከላይ የሚሆኑ ባለ ስልጣናት ወይም ፖለቲከኞች የእብደት ጠባይ ያላቸው?
የዲፕሎማቱ እና ፈላስፋው ማኪያቬሊ መጽሐፍ የሆነው The Prince ለዚህ መልስ አለው፡፡ ይህ አጭር መጽሐፍ እንዴት አንድ መሪ የራሱን የስልጣን ዘመን ማራዘም እንደሚችል ያሳያል።ምርጥ መሪ ማለት መልካም መሪ የሚል ቀጥተኛ ትርጓሜ የለውም፡፡ ምርጥ መሪ በምንም አይነት መንገድ ስልጣኑን የሚያስጠብቅ መሪ ነው ይለናል። ይህ መሪ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ያጭበረብራል፣ ይሰርቃል፣ ህዝቡን ያታልላል።
በመፅሀፍ ውስጥ እነዚህ ሀሳቦች ይንፀባረቃሉ።
1.መሪ ሥነ - ምግባርን አሽቀንጥሮ መጣል
አለበት፡፡
ህዝቡ በከፋበት ዘመን ከመሪ መልካምነት ሊጠበቅ አይገባም ይላል ማኪያቬሊ ።መሪው በባህሪው መጥፎነት ኖሮበት ሣይሆን መጥፎ ህዝብ መጥፎ መሪን ስለሚያመጣ ነው፡፡ ህዝቡ ሥነ ምግባር የጉደለውና ሥርዓት የሚያውቅ ከሆነ በዚህ ሁኔታ አንድ መሪ የራሱን ደህንነት መጠበቅ ግዴታ ውስጥ ይገባል፡፡ ለዚህ ያለው ብቸኛ አማራጭ ኃይልን በመጠቀም ጨካኝነቱን ማሳየት ነው፡፡ ህዝቡ ገልበጥባጣ በመሆኑ መሪ ህዝቡን ማመን የለበትም፤ ህዝቡን ከማመን ይልቅ የራሱን ማንነት እንደሁኔታው እየቀያየረ መኖር ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ማካቬሌ ፖለቲካን ከሥነ - ምግባር የሚነጥል ፍልስፍናን አቀረበ፡፡
2.መሪ የሐይማኖተኛና የቅድስና ህይወት ሊኖር አይገባም፡፡
ማኪያቬሊ ሲናገር ሐይማኖትን ህዝብ ይከተለው እንጅ መሪ ሊከተለውና ሊኖርበት አይገባም፡፡ መሪ ሐይማኖተኛ ከሆነ ትሑት ይሆናል፤ ትህትና ደግሞ ደካማ ያደርጋል፡፡ መሪ ደካማ ከሆነ በዙሪያው ያሉት ጠላቶቹ ሰለባ ይሆናል::
3. መሪ ለስልጣኑ ሕጋዊነት መጨነቅ የለበትም፡፡
ለማኪያቪሊ ህጋዊ መንግስት የሚያስፈልገው መረጋጋት ባለበት ሀገር ውስጥ ነው፡፡ መረጋጋት ከሌለ ህግም ቢኖር ተግባራዊ አይሆንም፤ ህግ አልባነትንም በህግ መመለስ አይቻልም፡፡ ህግ በጠፋበት ዘመን ህጋዊ ሥርዓት መፍጠር የሚቻለው ጸጥ - ለጥ አድርጐ በጉልበት መግዛት ሲቻል ነው፡፡ “መልካም ህግ ያለመልካም ክንድ ሊኖር ስለማይችል ከህግ ይልቅ የበረታች ክንድን እመርጣለሁ” ይላል ማኪያቬሊ፡፡
"Since there can not be good laws with out good arms, I will not consider laws but speak of arms.”
መጥፎ ህዝብ የመንግስት ቅጣት ስለሚፈራ ሣይወድ በግድ ሥርዓት ይይዛል፤ ስለዚህ መሪ ለመወደድ ከመጣር ይልቅ ለመፈራት ቢጥር የተሻለ ነው፡፡መሪ ይላል ማኪያቬሊ የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ ህጋዊ መንገድ ከመጠበቅ ይልቅ በራሱ ኃይል መተማመን ይገባዋል፡፡
ማኪያቬሊ በዚህ አመለካከቱ የመንግስት ሥልጣንና ህጋዊ ሥርዓት የተሳሰሩበትን ገመድ በጥሶ ጣለው፡፡
4.መሪ አስመሳይና አታላይ መሆን አለበት
ያልተረጋጋን የፖለቲካ ሁኔታ ማለፍ የሚችሉት ተንኮለኛ ሰዎች ናቸው ብሎ ማኪያቬሊ ያምናል፡፡ ተንኮለኛነቱ ለደህንነቱ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ተንኮለኛነቱ የሚገለፀው ደግሞ ህዝቡን ለማሳሳት አስመሳይ ሁኖ ስለሚቀርብ ነው፡፡ መሪ ጥሩ ሰው ሳይሆን ነገር ግን ጥሩ ሰው መስሎ ህዝቡን መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ አስመሳይነቱን ህዝቡ እንዳያውቅበት መጠንቀቅ አለበት፤ ለህዝቡ ሐቀኛ መስሎ ነው መታየት ያለበት፡፡ የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ደግ መስሎ መታየት፤ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለሰባዊነት የቆመ መስሎ መታየት አለበት፡፡ ነገር ግን በተግባር ከእነዚህ እሴቶች በተቃራኒ ሁኖ መኖር አለበት፡፡ ተቀናቃኞቹንና ደጋፊ መስለው በዙሪያው እየኖሩ ደባ የሚሠሩበትን ምቹ ሁኔታ ባገኘ ቁጥር ያለምንም ርህራሄ ማጥፋት አለበት፡፡ መሪ እንደ ተኩላ የራሱን እኩይነት በማይነቃ መልኩ ሸፍኖ መያዝ አለበት፡፡ ሊያጠቃቸው የሚፈልጋቸውንም የዋህ፣ ደካማና በእነርሱ ላይ ክፋት የማያስብ መስሎ በመታየት ሊያዘናጋቸውና ባላሰቡት ጊዜ ሊያጠቃቸው ይገባል ይለናል፡፡
___
መሪዎቻችን ይህን የማኪያቬሊን ፍልስፍና አብዝተው የሚጠቀሙት ይመስላል የሚያዋጣቸው ይመስላችኋልን?
ተወያዩቡት💬
@zephilosophy