"የማህበረሰብ ኮንትራት"
ሆብስ
ራስህን በዋሻ የሚኖር የጥንት ስው አድርገህ አስበው፡፡ በየለቱ ሚዳቋ በማደንህም ፊትህ በደስታ ተሞልቶ ወደ ልጆችህ እና ወደ ሚስትህ ትመለሳለህ፡፡ ሕይወትህን በእንዲህ አይነት ሁኔታ እየመራህ ሳለ፤ አንድ ቀን በመንገድህ ላይ ካንተ የገዘፈ ሰው ያጋጥምሃል፡፡
"ርቦኛል ካደንካት ሚዳቋ ጥቂት አምጣ" ይልሃል... ትደነግጣለህ፤ ፍዳህን አይተህ ነው ይህቺን ሚዳቋ ያደንካት።
"ለምን?" አልከው፡፡
"አንተን እና ቤተሰቦችህን ከሌላ ጉልበተኞች እጠብቃለሁ አንተም ምግብ ትሰጠኛለህ"
ሆብስ ይህን "#የማህበረሰብ_ኮንትራት" ሲል ይጠራዋል፡፡ አሁን ላይም መንግስት ብለን የምንጠራው ተቋም የተወለደው በዚህ መንገድ ነው፡፡
መንግስታት ከመመስረቱ በፊት ያለው የሰው ልጆች ሕይወት እጅግ አስፈሪ እና አዳጋች ነበር፡፡ ሰውም ከመጥፎነት የሚጋርደው ኃይል ከሌለው እና ያሻውን እንዲያደርግ ከተለቀቀ፣ ለፍቶ ከመብላት መስረቅን ያስቀድማል፡፡
ደህንነቱ ባልተጠበቀ ቦታ ላይ መኖር አስቸጋሪ ነውና፣ ሰዎች እንደ ማህበር የሚጠብቃቸውን እና ከግለሰቦች በላይ ኃይል ያለውን አካል ከመሃላቸው ይሾማሉ፡፡ አዎን መንግስት ካለ፣ ልክ እንደ ሌሎች እንስሳዎች ሁሉ ደስ እንዳለን የመስረቅም ሆነ የመገዳደል ነጻነት አይኖረንም፤ ሆኖም ንብረታችን እና ደህንነታችን እንዲጠበቅ ያደርግልናል። ሆብስ ይህ ነጻነት እና ምቾትን ይሰጠናል ይለናል ለምሳሌ ስራ መስራት ስንፈልግ ቤታችንን ዘግተን መውጣት እንችላለን፤ ለሰራነው ስራም በእርግጠኝነት ደሞዝ እንደምንቀበል እናምናለን፡፡ ይህም እንድናድግ ይረዳናል፡፡
“የማህበረሰብ ኮንትራት” በማህበሩ አካል በሆኑ ሰዎች መሃል የሚፈረም ስምምነት ነው፡፡ በፊርማችንም ከነጻነታችን እንደምንሰጥ ቃል እንገባለን፤ በሰጠነውም ነጻነት ልክ ደህንነትን እና ምቾትን እናገኛለን፡፡ የብዙሃን ድምጽም ከግለሰቦች ድምጽ በላይ ይሰማል።
የመንግስት የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ ከልማት፣ከዲሞክራሲ እና ከሁሉም ጥያቄዎች ቅድሚያ የሚሰጠው መሰረታዊ ጉዳይ ነው።
ሆብስ መንግስት ቢያስከፋንም ትዕዛዙን አልቀበልም ብለን ማመጽ አንችልም ይለናል፡፡ ምክንያቱም ለእኛ ባይመቸን እንኳ ለብዙዎች ልክ ነውና፤ ይህንን ኮንትራት መቅደድ የለብንም፡፡ በአንጻሩ ጆን ሎክ እና ዣን ዣክ ሩሶ ይህን የማህበረሰብ ኮንትራት ቀድሞውኑ መንግስት ካፈረሰው ህዝቦች አመጻን ማስነሳት አለባቸው ይሉናል፡፡
አንተ እና መንግስትህ ስለምን ነገሮች ተፈራርማችኋል? መቼ ነው መንግስትህ ቃሉን የሚያፈርሰው? መቼስ ነው ማመጽ ያለብህ?
✍️ፍሉይ አለም
@zephilosophy