ይቅርታህን እንካ፣ ይቅርታህን አምጣ!!
ሜርቭ ከተማ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የኻያምን በከተማው መገኘት የተቃወመው ዋና ቃዲ ተነሳና፣ ጣቱን ቀስሮ፣
በእግዚአብሔር የማያምን ፈላስፋ፣ ስለሃይማኖት ጥያቄ አስተያየት መሰንዘር የሚገባው አይመስለኝም» አለ፡፡
ዑመር የመታከት ፈገግታ አሳየውና፣
በእግዚአብሔር የማያምን ብለህ እንድትኮንነኝ ማ መብት ሠጠህ? የተናገርኩትን ካዳመጥህ በኋላ እንኳን ቢሆን ባማረብህ፡፡»
«የምትለውን መስማት አያሻኝም!» በኃይለ ቃል ተቃወመው:: «ይኽን ግጥም የተቀኘኸው አንተ አይደለህም ? ፦
ሠራህና አዳምን ከተልካሻ ጭቃ፣
አቆምህና እባብን ለሄዋን ጠበቃ፣
አንተ ባጠፋኸው እሱን ልትቀጣ?
ይልቅ፣ ይቅርታህን እንካ፣ ይቅርታህን አምጣ! -
እንዲህ ያሉ ቃላትን የሚሰነዝር ባለቅኔ ከሀዲ እንጅ አማኝ ይባላል?»
ዑመር ራሱን ነቀነቀ።
«ባላምንበት እኮ፣ እግዜር መኖሩን ባላቅ እኮ፣ አላናግረውም፡፡»
«ታዲያ እንደዚህ እየዘረጠጥክ ነው የምታናግረው ?» ቃዲው አፈጠጠበት።
«ለናንተ ቃዲዎችና፣ ለሡልጣኖች ነው የሽቁጥቁጥ ቋንቋ የሚያስፈልገው። ለፈጣሪ አይደለም። አላህ ታላቅ ነው! እንደሰው ይሉኝታና ግብዝነት የለበትም። ማሰብ እንድችል አርጎ ነው የፈጠረኝ። ስለዚህም አስባለሁ፡፡ የሀሳቤንም ፍሬ ነገር ሳላሞካሽ አቀርብለታለሁ።
የተሰበስበው ሁሉ በአድናቆት አጉረመረመ። ቃዲው ተቆናጥሮ ተነሳና፣ በሆዱ እየዛተ ምንም ሳይናገር ተቀመጠ፡፡ ልዑሉ ከልቡ ፈንድቆ ከሳቀ በኋላ የሃይማኖት ሰዎችን ደሞ እንዳያስቀይም ሰጋ። ወዲያው ገፁን አኮሳትሮ ፀጥ አለ። ሊቃውንቱ ነገሩ አለማማሩን ሲመለከቱ፣ አንድ ባንድ እጅ እየነሱ ወጡ፡፡
__
መፅሀፍ- ዑመር ኻያም ልበወለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብአያቶች
ትርጉም ፦ በተስፋዬ ገሠሠ
ገጽ 138/139
@zephilosophy