የዮጋ ንፅህና
ምንጭ ፦የጣፋጭ ህይወት ሳይንሳዊ ጥበብ(ኦሾ)
ትርጉም ፦ አስክንድር
በእርግጥ ይህ ነገር እንግዳና አመክኗዊ ያልሆነ (illogical) ይመስላል፡፡ ይሁንና ተፈጥሮ ራሷ እንግዳና አመክኗዊ ናት፡፡ ለምሳሌ ሰማዩ ወሰን የሌለውና ሊደረስበት የማይችል (infinite) ቢሆንም፣ ነፀብራቁን ግን በአንዲት ትንሽዬ ኩሬ ውስጥ እናስተውለዋለን። በእርግጥ ሙሉ በሙሉ በዚች ትንሽዬ ኩሬ አሊያም በፊት መስተዋት ላይ አይንፀባረቅም፡፡ ይሁንና በራሷ ሙሉ የሆነችው የተወሰነችዋ ክፍልም የአጠቃላዩ አካል ናት፡፡
የሰው ልጅ አእምሮም ልክ እንደ ፊት መስተዋት ነው፡፡ ንፁህ ከሆነ፣ ይህ የማይደረስበት ወይም ወሰን የሌለው (infinite) ያልነው ነገር እላዩ ላይ ይንፀባረቅበታል፡፡ በእርግጥ ይህ ነፀብራቅ ግን ወሰን የሌለው (infinite) አይሆንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የሱ አካል ወይም የሱ ክፋይ ይሆናል፡፡
የዚህ ወሰን የሌለው (infinite) ክስተት አካል የሆነው ክፍል ከአጠቃላዩ ጋር እኩል ነው፡፡ ምክንያቱም ይህን ወሰን የሌለውን ነገር መከፋፈል አንችልም። ክፍልፋይ ናቸው ብለን የምናስባቸው ነገሮች በሙሉ ስህተት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ህንድ ውስጥ ያለውን ሰማይ የህንድ ሰማይ፣ እንግሊዝ ውስጥ ያለውን ደግሞ የእንግሊዝ እያልን ልንከፋፍል አንችልም፡፡ ሰማይ የትም አይጀመርም፤ የትም ደግሞ አያልቅም፡፡
አእምሮአችሁንም በተመለከተ የሆነው ነገር የዚህ ተመሳሳይ ነው፡፡ 'አእምሮአችሁ' የሚለው ራሱ ስህተት ነው፡፡ አእምሮም ሆነ ነፍስ የማይደርስበትና ወሰን የሌለው (infinite) ያልነው አካል ናቸው፡፡ ውስን (finite) መስለው መታየታቸው ግን እውነት ሳይሆን ቅዠት ነው፡፡ ይህ የሆነው ራሳችንን እንደዛ አድርገን ስለምናስብ ብቻ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ደግሞ የምናስበውን ነገር ነው የምንሆነው፡፡ ቡድሀም “የምታስቡትን ሁሉ ትሆናላችሁ" እያለ ለረጅም አመታት እየደጋገመ ያስተምር ነበር፡፡ እናም ይህን በራሳችሁ ላይ ያስቀመጣችሁትን ውስንነትና ገደብ ጥሳችሁ በማለፍ ወሰን የለሽ (infinite) ለመሆን ጣሩ፡፡
ዮጋ በአጠቃላይ የሚያስተምረንም ይህን ወሰን፣ ይህን ገደብ እንዴት አልፈን መሄድ እንደምንችል ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ገደብ ወይም ወሰን እኛው እራሳችን የፈጠርነው እንጂ በእርግጥ ያለ አይደለም፤ ዝም ብሎ ሃሳብ ነው። ለዚህም ነው በአእምሮአችን ሃሳብ ከሌለ፣ ወሰን ወይም ገደብ የለሽ የምንሆነው፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ መለኮታዊ ሃይል ወደ እኛ ይወርዳል፡፡ ማሰብ ሰው ሲያደርግ፣ ከማሰብ በላይ ደግሞ መለኮታዊ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በታች ግን እንሰሳ ያደርጋል።
በአጠቃላይ ሃሳብ የሌለበትን ሁኔታ (non-thought) ለጥቂት ጊዜያት እንኳን ማሳካት ከቻልን፣ ያበጀነው ወሰንና ገደብ ሲናድ ማስተዋል እንጀምራለን፡፡ ለዚህም ነው የዮጋውን ሊቅ ፓታንጃሊን ሳይንሳዊ ነው የምንለው፡፡ ምንም አይነት ሃይማኖትም ሆነ እምነት አይጠይቀንም፡፡ ሙከራውን ለመስራት ጥረት እንዲኖረን ብቻ ነው የሚጠይቀን፡፡ መንገዶቹም የተጠላለፉና የተጠማዘዙ ሳይሆኑ አጭርና ግልጽ ናቸው፡፡ እናም እያንዳንዷን ዝርዝር በጥንቃቄ መከተል ይገባቸኋል። ከመስመሩ ከወጣችሁ ግን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ልትጓዙ ትችላላችሁ።
ፓታንጃሊ ከሳይንሳዊነቱ ባሻገርም ተጠየቃዊ (logical) አካሄድን የሚከተል ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የሚጀመረው አጠቃላይ ከሰውነታችን ነው፡፡ ከዛም የህይወታችን ሁለተኛው ደረጃ (ayer) ወደ ሆነው የአተነፋፈስ ስርአት (breathing) ይሻገራል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ሃሳቦቻችን (thoughts) ይመለከታል፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ዘዴ በቅድሚያ መጀመር ያለበት ከሰውነታችን ነው፡፡ ሰውነታችን ሲቀየር የአተነፋፈስ ስርዓታችን ይቀየራል፡፡ የአተነፋፈስ ስርዓታችን ደግሞ ሲቀየር አስተሳሰባችን ይቀየራል፡፡ አስተሳሰባችን ሲቀየር ደግሞ እኛ እንቀየራለን።
የቲቤት ነዋሪዎች ከተናደድክ ሩጥ ይላሉ፡፡ የግቢህን ዙሪያ ሁለቴ በሶምሶማ ሩጥ፡፡ ከዚህ በኋላ ንዴትህ የት እንደገባ ለራስህም ይገርምሃል፡፡ ይህ የሚሆነው ስንሮጥ የአተነፋፈስ ስርዓታችን ስለሚቀየር ነው፡፡ የአተነፋፈስ ስርዓታችን ሲቀየር ደግሞ የአስተሳሰባችን ሁኔታም እንደ ነበረው አይሆንም ይቀየራል፡፡
በእርግጥ መሮጡ የግድ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡ ዝም ብለን አንድ አምስት ጊዜ ያክል በጥልቀት ተንፍሰን ...አየር ወደ ውስጥ አስገብተንና ወደ ውጭ አስወጥተን ንዴታችን የት እንደ ሄደ ማየት እንችላላለን፡፡ ንዴታችንን በቀጥታ ማስወገድ ይከብደናል፡፡ ነገር ግን ስሜታችን፣ አካላዊ ሁኔታችንን መቀየር፣ ከዛም በመጨረሻም ንዴታችን ይቀየራል፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ ነው፡፡ ለዚህም ነው ፓታንጃሊ ሳይንሳዊ ነው የምለው፡፡
ወደ ቡድሃ ዘንድ ብትሄድ ግን ‹‹ንዴትህን ወዲያ ጣለው!›› ነው የሚልህ። ፓታንጃሊ ግን ይህን አይልም፣ በቀላሉ ነው የሚያስረዳህ፡፡ ተናደድክ ማለት ለዚህ ንዴትህ አመቺ የሆነ የአተነፋፈስ ስርዓት አለህ፡፡ እናም ይህን የአተነፋፈስ ስርዓት እስካልወጥክ ድረስ፣ ንዴትህ አያባራም ይልሃል፡፡ በእርግጥ በሌላ በራሳችን መንገድ ታግለን ንዴትን ልናሸንፈው እንችል ይሆናል፡፡ ያ ግን አድካሚና አላስፈላጊ መስዋትነት ነው፡፡
እዚህ ላይ ግዙፉ አካላችን ሲሆን ትንሹ ደግሞ አእምሮአችን ነው፡፡ ስለዚህ ከትንሹና ከረቂቁ ከመጀመር ከአጠቃላይ ከአካላችን መጀመሩ የተሻለ ነው በሚል ነው፡፡ ለመጨበጡ የሚረዳውም ይኸው በመሆኑ ፓታንጃሊም ከሰውነት አቋም (posture) ይጀምራል፡፡
በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ብዙም ባናስተውለው አእምሮአችን አንድ የተለየ ባህሪ እያሳየ ከሆነ፣ ሰውነታችን በበኩሉ ከዚህ ባህሪ ጋር ተያያዥ የሆነ ሁኔታ (posture) ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ከተናደደ፣ ዘና ብሎና ተረጋግቶ አይቀመጥም፡፡ ከንዴት ባህሪው ጋር የሚሄድ የፊት መለዋወጥ፣ የደም ስር መገታተር ወዘተ ባህርያትን ያሳያል፡፡
በአንፃሩ አንድ ሰው በፀጥታ ከተቀመጠ፣ የሰውነቱ አቋምና የጡንቻዎቹ ባህሪ የተለየ ነው የሚሆነው፡፡ ለምሳሌ ሙሉ በሙሉ ፀጥ ካልክ፣ እንደ ቡድሃ በአርምሞ ትቀመጣለህ፣ አሊያም በዝግታ ትጓዛለህ፡፡ ይህን ስታደርግም ደስ የሚል ፀጥታ ወደ ልብህ ሲገባ ይሰማሃል፡፡ ወይም ደግሞ እንደ ቡድሃ በአንድ ዛፍ ስር አረፍ በልና በፀጥታ ተቀመጥ። የአተነፋፈስ ስርዓትህ ሲቀየር ይሰማሃል፡፡ የተረጋጋና ሰላማዊ አተነፋፈስ፡፡ አተነፋፈስህ ደግሞ የተረጋጋና ሰላማዊ ሲሆን፣ አእምሮህ ፈታ ዘና ማለት ይጀምራል፡፡ ጭንቀትና ሃሳብ ጥለውህ ሄደው ደስ የሚል ፀጥታ ወደ ሰውነትህ ሲገባና ሲወጣ ይሰማሃል።
በመሆኑም ፓታንጃሊ ሳይንሳዊ ነው። ከዚህም አልፎ ፓታንጃሊ የሰውነታችንን ሁኔታ (posture) ለመለወጥ ከፈለግን፣ አመጋገባችንን እንድንቀይር ይመክረናል፡፡ ለምሳሌ ስጋ ተመጋቢዎች ከሆናችሁ፣ እንደ ቡድሃ ልትቀመጡ አትችሉም ይለናል፡፡ በአንፃሩ አትክልት ተመጋቢዎች ከሆንም፣ አንደዛው የተለየ የሰውነት ሁኔታ ይኖረናል። ወደ ሰውነታችን የሚገባ ነገር ሁሉ በአካላችንና በባህሪያችን ላይ ይንፀባረቃልና፡፡
@zephilosophy