~~~~~ ምኒሊክ ሰው ነበሩ! ~~~~~
በአድዋ ሰሞን ከተጻፉ ወጎች
«ዘውድአለም ታደሰ»
አድዋ በተነሳ ቁጥር ምኒሊክ ጅቡቲን ሸጧል ፣ እንትንን ሸጧል ፣ ገለመሌ የሚሉ አዝግ ሰዎች ትቢያቸውን አራግፈው ከች ይላሉ! ቆይ እኔ ምለው ... ምኒሊክ መሬት እየቸበቸበ የሚኖር ንጉስ ቢሆን ለነፍሱና ለስልጣኑ ሳይሳሳ በጦርነት ዳር ድንበሩን ያስከበረው ከጣሊያን ጋር ዋጋ ስላልተስማማ ነው ማለት ነው?
ዘመዴ .. ምኒሊክን የምናከብራቸው ከመላእክት ጋር አወዳድረናቸው አይደለም። ቅድስናን ከሳቸው ከጠበቅክ ሞኝ ነህ ማለት ነው። ሰው ናቸው! ስታያቸው መነፅርህን ለውጠህ በሰው ልክ ተመልከታቸው! ያኔ ከመከሰስ በላይ የሆኑ ንጉስ እንደሆኑ ይገባሃል! እስቲ አደረጉት የምትለውን ክፉ ነገር ሁሉ ፅፈህ ፅፈህ ፅፈህ አምጣና ከአድዋ ጎን አቁመው። ያኔ የአድዋ ግዝፈት ይገለጥልሃል! ያኔ ሃገር ሻጭ ያልከውን ንጉስ እንደተራራ ገዝፎ ታየዋለህ! እኔ በበኩሌ ምኒሊክ አይደለም መሬቴን ኩላሊቴን ቢሸጡ እንኳ ቀና ብዬ አላያቸውም! (አራት ነጥብ)
@Zerusoutlying
@wegoch