#ziz
👉አንድ ጊዜ ይባላል... የሆነች አይጥ የድመት ጓደኛ ነበራት። ድመቷና አይጧ በጣም ይዋደዳሉ። ሁለቱም ቤተሰብ ያላቸው ሲሆን ተጠልለው የሚኖሩት በአንድ ቤት ውስጥ ነበር። እናትና አባቶቻቸው ሁለቱ ባላንጣዎች ጓደኛ መሆናቸውን አያውቁም። ትንሿ ድመት በበኩሏ #አይጥ ለድመቶች ጣፋጭና ልዩ ምግብ መሆኗን የማታውቅ ሲሆን አይጧም #ድመት አስፈሪ እና ዋና የአይጥ ጠላት መሆኗን አታውቅም
በእንዲህ ጓደኝነታቸው ብዙ ግዜን ይቆያሉ። ከእለት ወደ እለትም ፍቅራቸው እየጨመረ ሄደ።
ከእለታት አንድ ቀን የድመት #እናት ትንሿ ድመት ከውሎ ስትመለስ "የት ውለሽ ነው የመጣሽው?" ስትል ጠየቀቻት። ትንሿ ድመትም "እኔማ ከውዷ ጓደኛዬ አይጥ ጋር ተጫውቼ እየመጣሁ ነው" ብላ ለእናቷ መለሰች። እናትም በቁጭትና በእልህ መንፈስ ...."አይጥ ማለት እኮ የእኛ ጣፋጭ ምግብ ናት። እሷ ጓደኛ ሳትሆን የምትበላ ምግብ ናት። ከዚህ በኋላ ካገኘሻት ቀስ ብለሽ ተመገቢያት" በማለት ልጇ ን አስጠነቀቀች።
አይጧም ከውሎዋ ወደ #እናቷ ጋር ስትመለስ ትንሿ ድመት የተነገራትን ንግግር የመሰለ ለአይጧ ነገረቻት። እንዲህ አለቻት.."ድመት ማለት የእኛ ጠላት፣አስፈሪ አውሬ ናት። እሷ እኛን ለመመገብ የተፈጠረች ፍጡር በመሆኗ ከዚህ በኋላ እንዳትቀርቢያት። በስህተት ብትቀርቢያት እንኳ በፍጥነት ከአጠገቧ አምልጪ"... በማለት ለትንሿ አይጥ መከረቻት።
እንደተለመደው ትንሿ ድመት ወደሚጫወቱበት ቦታ ሃዳ አይጧን ብትጠብቃት ልትመጣ አልቻለችም። ድመት ብዙ ጠበቀች አይጧ ግን አልመጣችም። በስተመጨረሻ ትንሿ ድመት "እናቴ የነገረችኝ እውነት ነው። ይቺን ሚጢጢ አይጥ ሳልበላ መመለስ የለብኝም በማለት ወደ አይጧ ቤት ትጓዛለች። የአይጧ ባት አቅራቢያ በመቆምም ጮክ ብላ አይጧን ጠራቻት።
አይጧም" አባት ድመት ለምን ፈልገሽኝ ነው?" በማለት በትዝብት መልክ ጠየቀቻት። ድመቷም "ነይ ጠጋ በይና የድሮ ጫወታችንን እንጫወት" ትላታለች። አይጧም ... "እኔም አራዳ አንቺም አራዳ፣ እናትሽ ላንቺ የነገረችሽን የኔም እናት ለእኔ ነግራኛለች" በማለት መለሰቻት። ከዚህ በኃሏም ሁለቱ እንስሳ ሲገናኙ፣ ድመት ስታሯርጥ አይጥ ደግሞ በመሸሽ ታመልጣለች።
#አስተምህሮ...
ወላጆች ልጆቻችን የት እንደሚውሉ ልናውቅ ይገባል። የአይጧ እናት ደርሳ ለልጇ ባትመክር ኖሮ ፣እናት ልጇን ታጣ ነበር። እኛም ልጆቻችን የትና ከማን ጋር እንደሚውሉ በማወቅ ከአልባሌ እና ብልሹ ስነ ምግባር ልንጠብቃቸው ይገባል።
"ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ። ከምትጠብቁትም ትጠየቃላችሁ። ሰውየው በቤቱ ውስጥ ጠባቂ ነው። ከሚጠብቀውም ነገር ይጠየቃል..." #ረሱል ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም
@zizuman